Quantcast
Channel: አስተያየት
Viewing all 665 articles
Browse latest View live

ኢትዮጵያ ያልተጠቀመችበት የማር ምርት

$
0
0

በኢትዮጵያ ከሚመረተው የማር ምርት ውስጥ ከ80 በመቶ በላይ የሚሆነው ለጠጅ መጣያነት አለያም ለቤት ውስጥ ፍጆታ ብቻ እንደሚውል መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ከዚህም ውስጥ አብዛኛው ማር ማስገኘት የሚጠበቅበትን ያህል ጥቅምና ውጤት ሳያስገኝ እንደሚገባክን ሲነገር ቆይቷል፡፡

አገሪቱ በየዓመቱ የምታገኘው የማር ምርት በውጭ ገበያዎች ተወዳዳሪ እንድትሆን የሚያስችላት ቢሆንም፣ አብዛኛው ለጠጅ መጣያነት እኩሌታውም እንዲሁ ለቤት ውስጥ ፍጆታ እየዋለ እንደሚገኝ ያስታወቁት፣ የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የኢትዮጵያ የሥጋ፣ የማር እንዲሁም የመኖ አቅርቦት አስተባባሪው ዶክተር ተቀባ እሸቴ ናቸው፡፡

ዶ/ር ተቀባ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በኢትዮጵያ በየዓመቱ እስከ 500 ሺሕ ቶን የማር ምርት የምታመርት ሲሆን፣ በአገሪቱ አብዛኛው አካባቢዎችም ማር በቀላሉ ማምረት ይቻላል፡፡ ለምሳሌ በትግራይና በአማራ ክልሎች ነጭ ማር በብዛት ማምረት የሚቻልባቸው አመቺ ተፈጥሯዊ ይዘቶች አሉ፡፡

በደቡብና በኦሮሚያ ክልሎች በተለይ ቡና በሚበቅልባቸው አካባቢዎች ማር እንደልብ የሚገኝ ሲሆን፣ በተለይ በማር አምራችነት ቀለበት ውስጥ እንደሚካተቱ ከሚነገርላቸው የወለጋ-ኤሊባቡር፣ የጅማ-ቦንጋ መዳረሻዎች ውስጥ ማር በብዛት ማግኘት እንደሚቻል ዶ/ር ተቀባ አብራርተዋል፡፡ እነዚህ አካባቢያዎች ሁሌም እርጥበታማ በመሆናቸውና ዕፅዋቶችንም ከዓመት ዓመት ስለሚያበቅሉ፣ ንቦች እንደልብ መቅሰም የሚችሉበት ዕድል አላቸው፡፡ ንቦቹ በእነዚህ አካባቢዎች ከሚያገኙት የተክል አበባ ንፁህ የተፈጥሮ ማር ስለሚያመርቱ፣ የኢትዮጵያን ማር ከሌላው ዓለም ልዩ እንደሚያደርገው ዶ/ር ተቀባ ይናገራሉ፡፡

 ማሩ ብቻም ሳይሆን ሰምን ጨምሮ ከውስጡ የሚወጡ ስድስት ዓይነት ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች የሚውሉና ዋጋቸውም ከማር ይልቅ እጥፍ ዋጋ የሚያወጡ ምርቶች እንደሚመረቱ ያብራሩት ዶ/ር ተቀባ፣ በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት እየተመረተ ያለው ማር በብዛት በኋላ ቀር ቀፎች ውስጥ በመሆኑ ከምርቱ መባከን ባሻገር የሚመረተውም ያለ አግባብ ጥቅም ላይ እየዋለ በመሆኑ የማር ምርት በአግባቡ ተይዟል ለማለት እንደሚያስቸግር ገልጸዋል፡፡ ‹‹ለምሳሌ ደኅንነቱ ያልተጠበቀ ማር በአዝዋሪዎች እጅ እየገባ፣ ከባዕድ ነገሮች ጋር እየተቀላቀለ በየመንገዱ ሲሸጥ ማየት የተለመደ ነው፤›› በማለት ዶ/ር ተቀባ አደገኛ የንግድ እንቅስቃሴዎችም የሚስተዋሉበት ምርት ስለመሆኑም አብራርተዋል፡፡

ከልማዳዊው የማር ማነብ ሥራ ባሻገር፣ በአሁኑ ወቅት 20 ድርጅቶች ንፁህ ማር አጣርተው ወደ ውጭ የሚልኩ ሲሆን፣ ሌሎች 11 ያህል ኩባንያዎች ደግሞ የማር ተረፈ ምርት የሆነውን ሰም የሚልኩ ስለመሆናቸው ታውቋል፡፡ ይህ ግን ዓባይን በጭልፋ የመቅዳት ያህል እንደሆነ ይታያል፡፡ በአገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች የተለያዩና ልዩ ልዩ ጣዕም ያላቸው የማር ዓይነቶች የሚመረቱ ሲሆን፣ እነዚህን በማጥናት የትኛው ለምን አገልግሎት እንደሚውል፣ እንዴት መሸጥ እንዳለበት፣ ደረጃውስ ምን መሆን ይገባዋል የሚለውን ጉዳይ የሚደነግግ ሕግ ባለመኖሩ ዘርፉ በተገቢው መንገድ እንዳያድግ እንቅፋት መሆኑን ዶ/ር ተቀባ አብራርተዋል፡፡ ‹‹ሕግ ባለመኖሩ ግብይቱን ሥርዓት አልባ አድርጎታል፤ ለመቆጣጠርም አስቸጋሪ ሆኗል፤›› ያሉት ኃላፊው፣ ይህን ለማስተካከል የሚያግዝ የሕግ ረቂቅ ተዘጋጅቶ ለሕዝብ ተወካዮች ሊቀርብ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ማር በቀላሉ ማምረት የሚቻልባቸው በርካታ ዕድሎች እንዳሉ ሲገለጽ፣ ወደ ኢንዱስትሪዎች በማምጣት ፕሮሰስ አድርጎ ገበያ ላይ ለማዋል በሚደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ ግን ከፍተኛ ክፍተት ይታያል፡፡ እስካሁን በኢትዮጵያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱና በዓለም አቀፍ ገበያ ውስጥ ገብተው ለመሥራት የጥራትና የብቃት ማረጋገጫ አግኝተው እየሠሩ የሚገኙ ኩባንያዎች ሦስት ብቻ መሆናቸው ይነገራል፡፡

ማርን ወደ ውጭ ከመላክ የሚያግድ ምንም ዓይነት የገበያ ችግር እንደሌለ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ የአሜሪካ፣ የአውሮፓ፣ የመካከለኛው ምሥራቅ፣ በቅርቡም የቻይና ገበያዎች በዋቢነት ይጠቀሳሉ፡፡ ይሁንና አገሮች የሚያስቀምጡት የጥራትና የደረጃ ማረጋገጫ ጥያቄዎች የማር ዘርፉን ውጤታማነት ይፈታተናሉ፡፡ የማር ጥራትና ደኅንነቱን ለማስፈተሽ እስከ 60 ሺሕ ዶላር ለላቦራቶሪዎች ወጭ ማድረግ የሚጠይቅ መሆኑም ፈታኝ ያደርገዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በአገሪቱ ከሚታየው አሠራር አኳያ ባህላዊ ቀፎዎች አብዛኛውን ድርሻ ይዘው መገኘታቸውም ለጥራቱ መጓደል ትልቁን ድርሻ ይወስዳሉ፡፡

ከእነዚህ ቀፎዎች በአንድ የምርት ዘመን ከአራት እስከ አምስት ኪሎ ግራም ማር የሚገኝ ሲሆን፣ በአንፃሩ ከዘመናዊው የንብ ቀፎ በአማካይ ከ25 እስከ 30 ኪሎ ግራም ማር ማግኘት እንደሚቻል ዶ/ር ተቀባ ያብራራሉ፡፡ በአንድ የንብ ቀፎ አማካይነት   ከ500 ሺሕ ኪሎ ግራም በላይ ማምረት ቢቻልም፣ እስካሁን የሚመረተው መጠን ግን አሥር በመቶው ብቻ ነው፡፡ ‹‹ይህ መሆኑ ደግሞ በዓለም አቀፍ ገበያ ያለን ድርሻ ያሳንሰዋል፤›› ብለዋል፡፡

በዓለም ገበያ አንድ ኪሎ ግራም ማር ከሦስት እስከ አራት ዶላር የሚሸጥ ሲሆን፣ ሰም ግን አሥር ዶላር ያወጣል፡፡ ይሁንና ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት ማርና የማር ተረፈ ምርቶችን ወደ ውጭ በመላክ ያገኘችው ገቢ ስድስት ሚሊዮን ዶላር ብቻ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ከሆለታ የማር ምርምር ማዕከል የተገኙ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት፣ አብዛኛው ማር አናቢ አነስተኛው ገበሬ ነው፡፡ ማር በአብዛኛው በልማዳዊ አመራረት ዘዴ ተመርቶም ቢሆን ለገበያ የሚውል ምርት መሆኑን የሚያብራራው የሆለታ ምርምር ማዕከል፣ ከሚመረተው ማር ውስጥ 90 ከመቶው ለገበያ የሚውል ነው፡፡ እ.ኤ.አ. ከ2008 ጀምሮ በአውሮፓ ኅብረት ማረጋገጫ የተሰጠው አገሪቱ የሰም ምርት ለወጪ ገበያ እንዲበቃ ማስቻሉም በጥሩ ጅምሩ ይጠቀሳል፡፡

በኢትዮጵያ ከ10 ሚሊዮን በላይ የንብ ዝርያዎች እንዳሉ ይታመናል፡፡ ከእዚህ ውስጥ 7.5 ሚሊዮኖቹ በንብ አናቢዎች እጅ እንደሚገኙ ሲገመት የተቀሩት ግን እንዲሁ በየጫካው የሚኖሩ እንደሆኑ የምርምር ማዕከሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

 

 

Standard (Image)

ኢትስዊችና ዘመናዊ የክፍያ ሥርዓቱ ጉዞ

$
0
0

የአገሪቱን የክፍያ ሥርዓት ለማዘመን ያስችላሉ ተብለው ወደ ሥራ ከተገባባቸው አገልግሎቶች መካከል አንዱ በባንኮች ትብብር በተቋቋመ ኢትስዊች አክሲዮን ኩባንያ በኩል የተጀመረው ሥራ ይጠቀሳል፡፡ ኩባንያው ብሔራዊ ባንክን ጨምሮ ሁሉም ባንኮች በማሳተፍና የአክሲዮን ድርሻ ኖሯቸው የተቋቋመ ነው፡፡ ኩባንያው በባንኮች መካከል  በኤሌክትሮኒክ ዘዴዎች የሚተላለፉ አነስተኛ ክፍያዎችን የሚያስተላልፍ ብሔራዊ ስዊች፣ የሒሳብ ማጣሪያና ማወራረጃ መሠረተ ልማትን በመገንባት ሥራ የጀመረ ሲሆን፣ ይህም በሁሉም ባንኮች የክፍያ ሥርዓቶች መካከል ተነባቢነት እንዲኖር ያስቻለ ነው፡፡ አክሲዮን ኩባንያው የተመሠረተው በ2003 ዓ.ም. ቢሆንም አገልግሎቱን ለመጀመር የሚያስችለውን መሠረተ ልማት ግንባታ አጠናቆ አገልግሎት መስጠት የጀመረው ባለፈው ግንቦት 2008 ዓ.ም. ነው፡፡

ቀዳሚ ሥራው አድርጎ ወደ አገልግሎት የገባው ደግሞ የሁሉንም ባንኮች የኤቲኤም ካርዶች በሁሉም ባንኮች ይዞታ ሥር ባሉ ኤቲኤሞች እንዲጠቀሙ በማድረግ እንደሆነም ይታወሳል፡፡

ባንኮች ተወዳዳሪዎች ቢሆኑም በኢትስዊች ኩባንያው ውስጥ የሚያደርጉት ትብብር ለባንኮቹም ሆነ ለአገሪቱ የክፍያ ሥርዓት ማደግ የተፈለገውን ውጤት እንደሚያመጣ የማድረግ ዓላማ ጭምር የያዘ ስለመሆኑም የኩባንያው ኃላፊዎች ይገልጻሉ፡፡ የየትኛውንም ባንክ ኤቲኤም ካርድ የያዘ የባንክ ደንበኛ በየትኛውም ባንክ ኤቲኤሞች ላይ በመጠቀም ገንዘብ ማንቀሳቀስ ከመቻሉም በላይ፣ ሌሎች ዘርፈ ብዙ ዘመናዊ የክፍያ አገልግሎቶችን መጠቀም ይችላል፡፡

የኢትስዊች ባለአክሲዮኖች ባለፈው ሐሙስ ባደረጉት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ የኩባንያው የ2008 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸሙን የተመለከተ ሪፖርቱም ይፋ ሆኗል፡፡

ኢትስዊችና 2008

ኢትስዊች ባለፈው ሐሙስ ባከናወነው ጠቅላላ ጉባዔ ላይ በኩባንያው ዳይሬክተሮች ቦርድ የቀረበው ሪፖርት የ2008 ዋነኛ ስኬቱ ኩባንያው ወደ አገልግሎት መግባቱ ነው፡፡

 የመሠረተ ልማት፣ የሲስተም፣ የደንብና የአሠራር ሥርዓት ዝርጋታ ሥራዎችን አከናውኖ የብሔራዊ የኤሌክትሮኒክ ክፍያ ስዊች መሠረተ ልማቱ አገልግሎት መስጠት እንዲጀምር ማድረጉ ዋና ክዋኔው መሆኑን ጠቅሷል፡፡ በብሔራዊ ስዊቹ አማካይነት በባንኮች መካከል የሚተላለፉ የገንዘብ ዝውውሮችን በተገቢው መንገድ ለመምራት የሚያስችል ደረጃ፣ ደንብ፣ የችግር አፈታት መመርያና የዋጋ ተመን በማውጣት ወደ ሥራ መገባቱ፣ በበጀት ዓመቱ ከተከናወኑ ዋና ዋና ሥራዎች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው ተብሏል፡፡ ከዚህም ሌላ ኢትዮ ፔይ በሚል የንግድ ስምና ምልክት የሚታወቀውን የብሔራዊ ስዊች መሠረተ ልማት ዓለም አቀፍ ደረጃ በጠበቀ መልኩ ማዘጋጀቱንና አገራዊ የክፍያ ካርድን መተግበር መጀመሩም በበጀት ዓመቱ ዋና ዋና ክንዋኔዎች ውስጥ አንዱ ሆኖ ተጠቅሷል፡፡ ከኢትዮ ፔይ ካርድ አገልግሎት መጀመር ጋር ተያይዞ የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ብዙነህ በቀለ በሪፖርቱ እንደገለጹት፣ ኢትዮ ፔይ የተባለውን ብሔራዊ ካርድ አምስት ባንኮች ወስደው ጥቅም ላይ እያዋሉትና ለማዋል እየተዘጋጁ መሆኑን ነው፡፡ ይህ ካርድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ካርድ ጭምር በመሆን የሚያገለግል ሲሆን፣ ባንኮች አሁን በየግል ከሚጠቀሙበት ካርድ ጎን ለጎን ሥራ ላይ የሚውልና ወደፊት ግን ለአገልግሎት አመቺነት ሲባል በተነጣጠለ መንገድ ያሉትን ካርዶች እንደ አንድ ብሔራዊ ካርድ አገልግሎት ውስጥ እንዲገባ የሚፈለግ ነው ተብሏል፡፡

የኢትስዊች ተገልጋዮችና ያለፉት አምስት ወራት

በአሁኑ ወቅት በመላ አገሪቱ ከ2,000 ሺሕ በላይ የሚሆኑ ኤቲኤሞች በባንኮች ተተክለው አገልግሎት እየሰጡ ነው፡፡ ከፕሪምየም ስዊች ሶሉሽን ተጨማሪ ባንኮች ውጭ ያሉት ኤቲኤሞች ለየባንኮቹ ደንበኞች ብቻ አገልግሎት ሲሰጡ የቆዩ ናቸው፡፡ ካለፈው ግንቦት 2008 ወዲህ ግን ከማንኛውም የኤቲኤም ካርድ ከየትኛውም ባንክ ኤቲኤም ገንዘብ ማውጣት ተችሏል፡፡ እንደ ኢትስዊች ዓመታዊ ሪፖርት የ2008 በጀት ዓመት የመጨረሻዎቹ ሁለት ወራት (ግንቦትና ሰኔ 2008 ዓ.ም.) ድረስ ብቻ  71,235 በሆኑ የክፍያ ካርድ ተጠቃሚ የባንክ ደንበኞች፣ ደንበኛ ከሆኑበት ባንክ ውጭ ካሉ ኤቲኤሞች አገልግሎት አግኝተዋል፡፡ በዚሁ ወቅት 173,228 የሆኑ ክፍያዎችን በኢትስዊች በኩል እንዲፈጸም ማስቻሉንም ሪፖርቱ ያሳያል፡፡ እነዚህ ደንበኞች  በሁለት ወራት 101,054 ሚሊዮን ብር ካልተመዘገቡበት ባንክ ኤቲኤሞች በማውጣት አገልግሎት እንዲያገኙ አስችሏል፡፡ ከሐምሌ እስከ ኅዳር 2009 ባለው ጊዜ ውስጥ ደግሞ የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ቁጥር እየጨመረ ስለመምጣቱ የሚጠቅሱት አቶ ብዙነህ፣ ባለፉት ጥቂት ወራት የታየው እንቅስቃሴ አበረታች መሆኑን ያመለክታል የሚል እምነት አላቸው፡፡

ሪፖርቱ 427,732 የሚሆኑ የካርድ ተጠቃሚዎች አገልግሎቱን ለማግኘት ሙከራ ማድረጋቸውን ይገልጻል፡፡ ከነዚህ አገልግሎት ፈላጊዎች ውስጥ 352,920 የሚሆኑት ወይም 82.5 በመቶዎቹ 1.17 ቢሊዮን ብር ከተለያዩ ኤቲኤሞች ማውጣት ችለዋል፡፡

በእስካሁኑ የኢትስዊች አክሲዮን ማኅበር ጉዞ የብሔራዊ ስዊቹ ሥራን ለማስጀመር ወሳኝ የነበረውን የፕሮጀክቱ ምዕራፍ አንድን ሥራ በስኬት ስለመጠናቀቁ አመላካች ስለመሆኑም የኩባንያው ሪፖርት ያሳያል፡፡ ሆኖም በየትኛውም ቦታ በማንኛውም ጊዜ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል አንድ ወጥ የሆነ የኢትዮጵያ የፋይናንስ ተቋማት የኤሌክትሮኒክ ክፍያ መሠረተ ልማት መደላደል የሚለውን የኩባንያውን ራዕይ ለማሳካት ረዥም ጉዞ ይጠብቀዋል ይላል፡፡  

የወደፊቱ ጉዞ

እንደ ሪፖርቱ ከሆነ የክፍያ ሥርዓቱን ከማዘመን አንፃር ይሠራሉ ተብለው ከተያዙት ውስጥ አዳዲስ አገልግሎቶችን ማስጀመር ነው፡፡ ብሔራዊ ስዊች ፕሮጀክቱ ውስጥ የተካተቱ አገልግሎቶችን ዓይነት፣ ብዛትና ውስብስብነትን ከግምት ባስገባ መንገድ ቀሪ የፕሮጀክቱን ሥራዎች በምዕራፍ ከፋፍሎ ለማከናወን መታቀዱን ያመለክታል፡፡ ለዚህም ከብሔራዊ ስዊች አቅራቢው ጋር በተደረገው የኮንትራት ማሻሻያ መሠረት  ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በተሰጠው መመርያ በግዴታ ሊተገበሩ የሚገቡ አገልግሎቶች ጥናትና በፍላጎት ሊተገበሩ የሚችሉ አገልግሎቶችን ለይቶ የፕሮጀክቱን ማከናወን የሚለው ሥራ ቀዳሚ ሆኖ ተቀምጧል፡፡ ይህ ማለት ዘመናዊ የክፍያ ሥርዓቱን ለማስፋት በብሔራዊ ስዊቹ በኩል የሚሰጡ አገልግሎቶች ግዴታ የሚሆኑበትን አሠራር የሚጠቀም ነው፡፡

ከዚህ ሌላ ኩባንያው በቀጣይ እተገብራቸዋለሁ ብሎ ከያዛቸው ዕቅዶች መካከል በብሔራዊ ስዊቹና በአባል ባንኮቹ መሠረተ ልማት ላይ ዓለም አቀፍ ደረጃዎች  እንዲተገበሩ ማድረግ የሚለው ይገኝበታል፡፡ ይህም ሁሉም ባንኮች አንድ ወጥ የሆነ ደረጃውን የጠበቀ ካርድ እንዲኖራቸው ከማድረግ ጀምሮ፣ ተመሳሳይ በሆነ ቴክኖሎጂና ሲስተም እንዲጠቀሙ ወደማድረግ የሚገባበት ነው፡፡  

በአገሪቱ ያሉ የባንክ ደንበኞች ፍላጎትንና አቅምን መሠረት ያደረጉ፣ የአገሪቱን የንግድ አሠራር ለማቀላጠፍ ምቹ የሆኑ፣ እንዲሁም ወጪ ቆጣቢ የሆኑ የኤሌክትሮኒክ ዘዴ የክፍያ አገልግሎቶችን በኢትዮ ፔይ የንግድ ስምና ምልክት እንዲስፋፋ ማድረግም የኩባንያው ቀጣይ ዕቅድ ነው ተብሏል፡፡

በኢትዮ ፔይ የንግድ ስምና ምልክት የሚታተሙ የክፍያ ካርዶችን፣ ከዓለም አቀፍ የካርድ ኩባንያዎች ጋር በጥምር የንግድ ምልክት በማቀናጀት በዓለም አቀፍ ሐዋላ አማካይነት ወደ አገር ውስጥ በሚገባ የውጭ ምንዛሪ ማሳደግ የሚልም ዕቅድ አለኝ ብሏል፡፡

ባንኮች በኤሌክትሮኒክ ክፍያ ዘዴ የታገዙ የፋይናንስ አገልግሎቶችን ለደንበኞቻቸው በስፋትና በዓይነት እንዲያቀርቡ በማገዝ፣ የተለያዩ የመንግሥት ተቋማት፣ የንግድ ድርጅቶችና ግለሰቦች በኤሌክትሮኒክ የክፍያ ሥርዓት ታግዘው ገቢዎቻቸውን እንዲሰበስቡና ክፍያዎቻቸውን እንዲፈጽሙ ለማድረግም እንደሚሠራ ተገልጿል፡፡

የፋይናንስ ተቋማትን ማስገባት

ኢትስዊች ብሔራዊ ባንክን ጨምሮ በሁሉም የአገሪቱ ባንኮች የአክሲዮን ባለቤትነት የተቋቋመ ቢሆንም፣ ከባንኮች ውጭ ያሉ የገንዘብ ተቋማትን ወደ አክሲዮን ኩባንያው የማስገባት ውጥን አለው፡፡ ይህንን ውጥኑን ለማሳካት አነስተኛ የቁጠባና የብድር ተቋማት ሲስተሞቻቸውን ከብሔራዊ ስዊቹ ጋር እንዲያቀናጁና የፋይናንስ አገልግሎትን ለማዘመንና ተደራሽነቱን ለማስፋት ይፈለጋል፡፡ በክፍያ ሥርዓቱ ውስጥ በሦስተኛ አካል የፋይናንስ ቴክኖሎጂ አገልግሎት ሰጪነት የተሰማሩ ኩባንያዎችም ሲስተሞቻቸውን ከብሔራዊ ስዊቹ ጋር በማቀናጀት አገልግሎቶቻቸውን በባንኮች በኩል ተደራሽ እንደሚያደርጉ የሚጠበቅ ስለመሆኑ የሚገልጸው ሪፖርቱ፣ ለዚህም ተፈጻሚነት የተለያዩ ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን ገልጿል፡፡ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች፣ ኮርፖሬሽኖችና ሌሎች ተቋማት የሚሰበስቧቸውን ገቢዎችም ሆነ ክፍያዎቻቸውን ወደ ኤሌክትሮኒክ ዘዴ በመለወጥና ከባንኮችና ከብሔራዊ ስዊቹ ጋር በማስተሳሰር የገቢ አሰባሰባቸውንና ክፍያ አፈጻጸማቸውን እንዲተገብሩ ለማድረግም የተጀመሩ ሥራዎች አሉ ተብሏል፡፡ አቶ ብዙነህ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የክፍያ ሥርዓታቸውን በኤሌክትሮኒክ የክፍያ ሥርዓት ከኩባንያቸው ጋር ለማስተሳሰር ወደ ሥራ ይገባል ተብሎ ከሚጠበቁት ተቋማት ውስጥ አንዱ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ነው፡፡

ግብር ከፋዮች በቀጥታ በዚህ ሥርዓት ውስጥ ክፍያ እንዲፈጽሙ ለማድረግ የመሠረተ ልማት ግንባታ ሥራዎች እየተሠሩ ሲሆን፣ ይህ ሲጠናቀቅ በተለይ ከፍተኛ የግብር ከፋዮች ያሉበት ቦታ ሆነው ክፍያ እንዲፈጽሙ ያስችላል ብለዋል፡፡ እንደ ኤሌክትሪክ፣ ውኃና የመሳሰሉ ክፍያዎችም በዚህ ሥርዓት ውስጥ እንዲገቡ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡  

በኤሌክትሮኒክ ዘዴ የሚደረገው የክፍያ ሥርዓት መስፋፋት የፋይናንስ አገልግሎቱ እንዲስፋፋና ለኢኮኖሚ ዕድገቱም ትርጉም ያለው አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ያግዛል፡፡ ከዚህም ሌላ በገበያው ውስጥ የሚዘዋወረው የጥሬ ገንዘብ መጠንን በመቀነስ በገንዘብ ማሳተም፣ ማጓጓዝ፣ መቁጠር፣ መጠበቅና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የሚወጣውን ከፍተኛ ወጪ በመቀነስ ተጨባጭ የሆነ አገራዊ ጥቅም የሚያስገኝ ይሆናል የሚል እምነት ተይዟል፡፡

አገልግሎቱና የደንበኞች ቅሬታ

የኢትስዊች ወደ ሥራ መግባት ማንኛውም የኤቲኤም ተጠቃሚ በፈለገበት ቦታ በቀረበው የየትኛውም ባንክ ኤቲኤም እንዲጠቀም ማስቻል ነው፡፡ ባለፈው ስድስት ወራት የባንክ ደንበኞች በዚህ አገልግሎት እየተጠቀሙ ነው፡፡

ኢትስዊችም ቢሆን ከዚህ አገልግሎት በተጨማሪ ሌሎች በርካታ አገልግሎቶችን እንደሚጀምር አስታውቋል፡፡ ይሁንና ከዚህ አገልግሎት ጋር በተያያዘ እየቀረቡ ያሉ ቅሬታዎች ግን በየዕለቱ ይሰማሉ፡፡ ወደ አንድ የባንክ ኤቲኤም ማሽን ሄደው ገንዘብ ለማውጣት ሲሞክሩ የማያገኙበት አጋጠሚ አለ፡፡ የጠየቁት ገንዘብ እንደተከፈላቸው ሪፖርት ቢደረግላቸውም፣ ገንዘቡን ሳይወስዱ የሚቀሩበት አጋጣሚ ስለሚፈጠር ወደ ተለያዩ ኤቲኤሞች በመሄድ መሞከር ግድ ሲላቸውም ይታያል፡፡

በአንዴ የሚፈልጉትን ክፍያ አላገኘንም የሚል ቅሬታ ይቀርባሉ፡፡ ገንዘብ ለማስመለስ፣ ቀናት የሚወስድ መሆኑም ከአገልግሎት አሰጣጡ ጋር በተገናኘ የሚቀርብ ቅሬታ ነው፡፡

አቶ ብዙነህም እንዲህ ያለው ቅሬታ ስለመኖሩ አልሸሸጉም፡፡ ነገር ግን ከጠቅላላ ተገልጋዮች የተወሰኑት የገጠማቸው ችግር ብዙ ምክንያት ያለው ነው ይላሉ፡፡ ከተጠቃሚው፣ ከባንኩ ሲስተም ወይም ከራሱ ከኢትስዊች ጋር የተያዘ ክፍተት ይሆናል ያሉት አቶ ብዙነህ፣ በኢትስዊች በኩል ያለውን ወዲያው እንዲታረም ይደረጋል ብለዋል፡፡ የአገልግሎቱ መስተጓጎል ከባንኮች ሲስተም ጋር በተገናኘ በሚሆንበት ጊዜ ችግሩን በመግለጽ እንዲያስተካክሉ እንደሚደረግ ገልጸዋል፡፡ ሌሎች ምክንያቶች ቢኖሩም እነዚህን ክፍተቶች እየደፈኑ እንዲሄዱ በማድረግ ቅሬታው መፍትሔ እንዲያገኝ ከባንኮች ጋር እየሠሩ ስለመሆኑም ገልጸዋል፡፡

ነገር ግን በአንድ አጋጣሚ በአንድ ኤቲኤም ገንዘብ  ማግኘት ያልቻለ ደንበኛ ወደ ሌላ ኤቲኤም ቢሄድ ያገኛል፡፡ ያላግባብ ከተቆረጠበትም ገንዘቡ የትም ሳይሄድ እንዲከፈለው ይደረጋል ብለዋል፡፡

ያላግባብ እንደተቆረጠ የሚደረገውን ገንዘብ ለማስመለስ የስምንት ቀናት ጊዜ ስለመሰጠቱ የጠቀሱት አቶ ብዙነህ፣ ገንዘቤ ከአካውንቴ ተቆርጧል ያለ ደንበኛ ለባንኩ ባመለከተ በሳምንት ቀን ውስጥ ገንዘቡን ማግኘት አለበት ብለዋል፡፡ ‹‹ገንዘቡን ወስዶም ከሆነ መረጃ ስለሚቀርብ ይህንን ገንዘብ አውጥተሃል ተብሎ ይገለጽለታል እንጂ የሚቀር ገንዘብ አይደለም፡፡ አጠቃላይ ሲስተሙም ቢሆን በአግባቡ ይሠራል፤›› የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ኢትስዊች ምን አገኘ?

በኤቲኤም የሚፈጸሙ ክፍያዎችን በማዕከል በመሆን ለሚሰጠው አገልግሎት የራሱ የሆነ ክፍያ አለው፡፡ በ100 ብር 25 ሳንቲም ያገኛል፡፡ እስካለፈው ወር መጨረሻ ድረስም 207 ሚሊዮን ብር ገቢ ማግኘት ስለመቻሉ ተጠቅሷል፡፡

በአሁኑ ወቅት ባንኮች የኤቲኤሞቻቸውን ቁጥር እያሳደጉ በመመጣታቸውና የተገልጋዩ ቁጥርም እየጨመረ ስለመጣ፣ ገቢውም የዚያኑ ያህል ያድጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ገቢውም ለአገልግሎቱ ማስፋፊያ በማዋል ዘመናዊ የክፍያ ሥርዓቱ እንዲያድግ ያደርጋል ተብሏል፡፡ 

Standard (Image)

የንግድ ምክር ቤት አጣሪ ግብረ ኃይል በመጪው ጥር ወር ምርጫ እንዲካሄድ ውሳኔ አሳለፈ

$
0
0

የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ስምንተኛ ጠቅላላ ጉባዔውን ለማካሄድ ችግር እንዳጋጠመው በመግለጹ ምክንያት ችግሩን ለመፍታትና ተፈጠሩ የተባሉትን አለመግባባቶች ለመቅረፍ የተቋቋመው አጣሪ ግብረ ኃይል ሪፖርቱን ይፋ አደረገ፡፡ ስምንተኛ ጠቅላላ ጉባዔውን ለማካሄድ ያስችላሉ ተብለው በግብረ ኃይሉ የቀረቡትን የውሳኔ ሐሳቦችም 18ቱ አባል የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤቶች ረጅም ጊዜ ከፈጀ ክርክር በኋላ በመቀበላቸው ተፈጻሚ እንዲሆኑ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡

አጣሪ ግብረ ኃይሉ ሰኞ፣ ታኅሳስ 24 ቀን 2009 ዓ.ም. ይፋ ባደረገው ሪፖርት ላይ የመከሩት 18ቱ አባል ምክር ቤቶች፣ የአገር አቀፉን ንግድ ምክር ቤት ስምንተኛ ጠቅላላ ጉባዔን ማካሄድ ያስቻላል በማለት ግብረ ኃይሉ ባቀረበው ሐሳብ መሠረት ጠቅላላ ጉባዔውና ምርጫው ጥር 30 ቀን 2009 ዓ.ም. እንዲካሄድ ተስማምተዋል፡፡

የአገር አቀፉ የንግድና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ጠቅላላ ጉባዔና ምርጫ የሚካሄደው ግን በግብረ ኃይሉ ውሳኔ መሠረት ተጨማሪ ማጣራት ተደርጎ ከሚገኘው ውጤት በመነሳት ተጨማሪ ውሳኔ ተካቶበት እንደሆነ ታውቋል፡፡ ግብረ ኃይሉ ለውሳኔ ካቀረባቸውና ስምምነት ላይ ከተደረሰባቸው አንኳር ጉዳዮች መካከል 18ቱ አባል ምክር ቤቶች እያንዳንዳቸው በሁለት አባላት እንዲወከሉ በማድረግ ምርጫው እንደሚካሄድ የተባለው የስምምነቶቹ አንዱ አካል መሆኑን የግብረ ኃይሉ ሰበሳቢ አቶ አሰፋ ገብረሥላሴ አስታውቀዋል፡፡  

ግብረ ኃይሉ ያቀረባቸው የውሳኔ ሐሳቦች ሙሉ ቀን ሲያከራክሩ ቢውሉም፣ ሁለት ጉዳዮች ብቻ በድምፅ ብልጫ ውሳኔ ተሰጥቶባቸው ቀሪዎቹ የግብረ ኃይሉ ሐሳቦች ግን ተቀባይነት በማግኘታቸው ስምምነት ተደርሶባቸዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በተካሄደው ምርጫ ወቅት በርካታ ግድፈቶችን ማግኘቱን ያረጋገጠው ግብረ ኃይሉ፣ ቀጣዩን ምርጫ ለማካሄድ ያስችላሉ ያላቸውን ጉዳዮች ብቻ ከሕግ አንፃር በመለየት እንዲፈጸሙ ማድረጉን አስታውቋል፡፡ አባል ምክር ቤቶች ከሥር ምርጫ ሳያካሂዱ ወደ ላይኛው የአመራር እርከን ላይ የወጡ አመራሮቻቸውን በሚመለከት በሕጉ መሠረት መረጃ ማቅረብ ካልቻሉ እንዲሰረዙ በማለት ውሳኔ አሳልፏል፡፡ በዚህም መሠረት እስከ ምርጫው ዋዜማ ድረስ ተጣርቶ ዕርምጃ እንዲወሰድበት ለማስቻል ኃላፊነቱን ቦርዱና ጽሕፈት ቤቱ እንዲወስዱ ተደርጓል፡፡

ሕጋዊ የምዝገባ ሰርተፍኬት የሌላቸው አባላትም እንዲሰረዙ ጭምር በማድረግ ጠቅላላ ጉባዔውን ለማካሄድ ስምምነት የተደረሰ ሲሆን፣ ሕጋዊ የምዝገባ ሰርተፍኬት ሳይኖረው ለዓመታት ሲመርጡና ሲመረጡ የነበሩ የንግድ ምክር ቤት አመራር አባላትም እንደተገኙ ግብረ ኃይሉ ባቀረው ሪፖርት ጠቅሷል፡፡ የምርጫ ሒደቱም እንደ ቀድሞው በአስመራጭ ኮሚቴ በኩል ሳይሆን በጽሕፈት ቤቱ አማካይነት እንዲካሄድ ወስኗል፡፡ ወደዚህ ውሳኔ የደረሰውም አስመራጭ ኮሚቴ ለንግድ ምክር ቤቱ ውዝግብ መባባስ ግንባር ቀደም ሚና እንደነበረው በማረጋገጡ መሆኑን ግብረ ኃይሉ አስታውቋል፡፡  የተባለው የአባልነት መዋጮ ከፍተኛ በመሆኑ እንዲቀንስ ማለት የተሻሻለው መተዳደሪያ ደንብ በድጋሚ እንዲፈተሽ የሚል ውሳኔም አሳልፏል፡፡

በዕለቱ በርካታ ክርክር ያስነሱ ጉዳዮች ቢደመጡም ጠቅላላ ጉባዔውን ለማካሄድ ሲባል ስምምነት የተደረሰባቸው ጉዳዮችን ተቀብሎ ምርጫው እንዲካሄድ ለማድረግ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡ የአባላት ቁጥርን በተመለከተ መረጃ አቅርቡ የተባሉ የንግድ ምክር ቤቶች ከዚህ ቀደም እንዳላቸው ባስታወቁት የአባላት ቁጥር ብዛት ልክ መረጃ ሊያቀርቡ ባለመቻላቸው፣ ያስመዘገቧቸው አባላት ቁጥር ከመተዘገበው በታች በእጁ እንዳሽቆለቆለ ለማወቅ ተችሏል፡፡

                   

Standard (Image)

ዘንድሮ በአማራና በትግራይ ከ150 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የሰብል ምርት ይጠበቃል

$
0
0

- አትክልት ያመረቱ ገበሬዎች በገበያ እጦት ተቸግረዋል

በዚህ ዓመት በአማራና በትግራይ ክልሎች ከ150 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የግብር ምርት እንደሚገኝ ይጠበቃል፡፡ ይህ የተገለጸው ዓምና በተለያዩ የክልሎቹ ዞኖች ውስጥ ተከስቶ በነበረው ድርቅ ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው የነበሩ፣ በዘንድሮው የምርት ዘመን በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ለመገምገም በተደረገ የመስክ ቅኝት ወቅት ነው፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ከድርቁ አገግመዋል ተብለው ከተለዩት መካከል በሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ወረዳ፣ በረኸት ወረዳ፣ ደብረ ብርሃን ከተማ ይጠቀሳሉ፡፡ በሰሜን ወሎ ዞን፣ አበሩ ወረዳ፣ ጉባ ላፍቶ ወረዳ፣ ራያ ቆቦ፣ እንዲሁም የአላማጣ አካባቢዎች ሙሉ በሙሉና በከፊል ጉዳት ደርሶባቸው ነበር፡፡

አቶ ደረሰ ሀብቴ በምንጃር ወረዳ ኮርማ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ነዋሪ ናቸው፡፡ አቶ ደረሰ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ዓምና ከነቤተሰባቸው የሚተዳደሩበትን ሁለት ጥማድ መሬት አርሰው ከዘሩት ማሽላ ምንም ምርት አላገኙም ነበር፡፡ ዘንድሮው ዝናቡ ጥሩ በመጣሉና በመስኖ ማልማት በመቻላቸውም፣ ማሽላ ሦስት ቆርጥ፣ ጤፍ ሦስት ቀርጥ እንዲሁም ሽንብራ አንድ ቀርጥ መዝራት በመቻላቸው ምርት ሰብስበዋል፡፡ ከማሽላው ብቻ አሥር ኩንታል እንዳገኙ፣ የዘንድሮው ከዓምናው የተሻለ እንደሆነም ገዋጸዋል፡፡

አቶ ተስፋ ባንተሁንም በዚሁ አካባቢ ነዋሪ ናቸው፡፡ እሳቸው እንደሚገልጹት በዞኑ ውስጥ ካሉት 15 ወረዳዎች 12ቱ የገጠር ቀበሌዎች ናቸው፡፡ በእነዚህ ቀበሌዎች ውስጥ ይኖሩ ከነበሩ 1.4 ሚሊዮን ነዋሪዎች ውስጥ 969 ሺዎቹ በድርቁ በመጎዳታቸው ምክንያት ለተረጂነት ተጋልጠው ነበር፡፡ ከ2007 እስከ 2008 በነበሩት ሁለት ዓመታት ውስጥ ከመኸር ወቅት 402 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማግኘት ቢታቀድም፣ ከዚህ ውስጥ 40 በመቶ ብቻ እንደተሳካ ያብራሩት አቶ ተስፋ፣ በዘንድሮው የመኸር ዘመን  5.4 ሚሊዮን ኩንታል እንደሚገኝ ቢጠበቅም ከዚህ ውስጥ 78 በመቶ ብቻ ሊገኝ መቻሉን አብራርዋል፡፡ ቀሪው ምርት በክልሉ አካባቢዎች በተከሰተው ውርጭ፣ የአፍሪካ አንበጣ በሚባለው ተባይ እንዲሁም በተምች ወረርሽኝ ምክንያት የተዘራው እህል በመውደሙ ሊገኝ አልቻለም ብለዋል፡፡ የአፋር ክልል አዋኝ በሆኑ አካባቢዎችም ዝናቡ ቀድሞ በመውጣቱ የታቀደውም የምርት መጠን ሙሉ በሙሉ መሳካት እንዳልተቻለ፤ በእነዚህ አካባቢዎች የሚኖሩ 98 ሺሕ ሰዎችም በዕርዳታ እየታገዙ ለመቆየት እንደሚገደዱ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ባለፈው ዓመት በክልሉ ከ2.3 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ተረጂ ሆኖ እንደቆየ ነገር ግን በዘንድሮው ዓመት የተረገጂው ቁጥር ከግማሽ በታች በመቀነስ 650 ሺሕ ብቻ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የአማራ ክልል የእርሻና የተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ተሾመ ዋለ ናቸው፡፡

 በዘንድሮው መኸር በክልሉ 4.3 ሚሊዮን ሔክታር መሬት በእርሻ ማሳዎች ተሸፍኖ እንደነበርና ከዚህ ውስጥ 93 በመቶው ሰብል እንደተሰበሰበ ዶ/ር ተሾመ ተናግረዋል፡፡ በመስኖ አማካይነት ከዓመት ዓመት ለማምረት የሚያችል 980 ሺሕ ሔክታር መሬት ተዘጋጅቶ፣ ከዚህ ውስጥ 460 ሺሕ ሔክታሩ እየተዘራበትና ሰብል እየለማበት እንደሚገኝ፤ ቀሪውም የእርሻ መሬት በቅርቡ እንደሚታረስ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ዓምና በኤልኒኖ (የውቅያኖሶች መሞቅ ያከተለው የአየር ፀባይ ለውጥ) ምክንያት በተከሰተው ድርቅ ከተጎዱ የኢትዮጵያ ክፍሎች አንዱ የትግራይ ብሔራዊ ክልል ነበር፡፡ በክልሉ በ2008 በጀት ዓመት ይገኛል ተብሎ ከታሰበውና በ1.3 ሚሊዮን ሔክታር ከተዘራው ሰብል ውስጥ 18 ሚሊዮን ኩንታል ብቻ ነበር ማግኘት የተቻለው፡፡ ዕቅዱ ግን 22 ሚሊዮን የሰብል ምርት ለማግኘት እንደነበር የክልሉ የግብርና እና ገጠር ልማት ቢሮ የሰብልና የአፈር ለምነት ንዑስ የሥራ ሒደት ኃላፊ አቶ  በሪሁን አረጋዊ ገልጸዋል፡፡ በዘንድሮው የመኸር ወቅት በዚያው በ1.3 ሚሊዮን ሔክታር መሬት ከተዘራው ውስጥ ከ25 ሚሊዮን ኩንታል ያላነሰ ምርት እንደሚጠበቅ ገልጸው፣ እስካሁን 91 በመቶው እንደተሰበሰበ አስታውሰዋል፡፡

አቶ በሪሁን እንዳሉት፣ ዓምና የታጣውን የምርት መጠን ዘንድሮ ለማሻሻል በክልሉ ዋና ችግር የሆነው የውኃ እጥረት ትኩረት ተሰጥቶታል፡፡ የውኃ እጥረት ባለባቸው አካባቢዎች ጥልቅ የውኃ ጉድጓዶችን በመቆፈርና የክረምቱን ውኃ በማቀብ የመስኖ ሥራ በሰፊው እንዲለመድ ሲደረግ ከመቆየቱም ባሻገር ሰብሎችን በመስመር በመዝራት፣ በቂ የማዳበሪያና የፀረ አረም መድኃኒቶችን በማቅረብ ገበሬውን ማገዝ ስለተቻለ የምርቱ መጠን ሊሻሻል መቻሉን አቶ በሪሁን ገልጸዋል፡፡

በክልሉ በድርቅ ከተጎዱት አካባቢዎች መካከል ደቡባዊ ዞን ራያ አዘቦ፣ ሀውዜን፣ ጎሎ ምሀዳ ወረዳዎችና ቀበሌዎች እንዲሁም በክልሉ ምሥራቃዊ ዞን አዲግራት ወረዳ እና ጋንታ አፈሹም ካለፈው የድርቅ አደጋ እያገገሙ የሚገኙ ናቸው፡፡ ከእነዚህ ዞኖች በተያዘው የመኸር ወቅት ከዝናቡ በተጨማሪ መስኖን በመጠቀም የአካባቢው ገበሬዎች ቶሎ የሚደርሱ የጓሮ አትክልቶችን ማለትም ሽንኩርት፣ ቃሪያ፣ ቲማቲምና ሌሎችንም ጎን ለጎን በማምረት ላይ ይገኛሉ፡፡

በትግራይ የደቡባዊ ዞን የእርሻና የገጠር ደን ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ገብረ እግዚአብሔር ሀገዊ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በ2007 እና በ2008 የመኸር ወቅት በ143,300 ሔክታር ላይ ዘር ለመዝራት አቅደን በ130 ሺሕ ላይ የዘራን ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ ስድስት ሚሊዮን ኩንታል ለማግኘት ታቦ የነበረ ሲሆን፣ ባጋጠመው የዝናብ እጥረት ምክንያት እርሻዎች በመገልበጣቸው 29 በመቶ ብቻ ሊገኝ ችሏል፡፡

ድርቁን ከመቋቋም ጎን ለጎን እጥርበታማነትን በማስፋፋት ለዚሁ ሲባል ራሱን የቻለ ክላስተር በማቋቋም በ2009 ዓ.ም. 6.5 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማግኘት መታቀዱን አስታውቀዋል፡፡ በመሆኑም ከመኸር ወቅት ብቻ 5.2 ሚሊዮን ኩንታል የሰብል ምርት መገኘቱን አቶ ገብረ እግዚአብሔር በሰጡት መግለጫ ጠቅሰዋል፡፡

በእነዚህ ዞኖችና ወረዳዎች ውስጥ ሪፖርተር ተዘዋውሮ እንደቃኘው ከሆነ ገበሬዎች ሽንኩርት በብዛት ቢተክሉም የገበያ ችግር እያጋጠማቸው ይገኛል፡፡ ሪፖርተር ያነጋገራቸው ገበሬዎች ከሰጡት አስተያየትም ይህ ችግር ጉልህ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ አንዳንድ ወረዳዎች ዝናቡ ይብሱን ለዓመታት ዘግይቶባቸዋል፡፡ በዚህ ሳቢያም ከግብርና ወጥተው ወደ ሌላ የሥራ መስክ ፊታቸውን ለማዞር የተገደዱ እንዳሉም እንዳለባቸው የግብርና ባለሙያዎች አስተያየታቸውን ለሪፖርተር ሰጥተዋል፡፡

 ለሚመረተው ምርት የገበያ ትስስር ባለመፈጠሩ ምክንያትም በደላሎች የመጠለፍ ችግር ይታያል ተብሏል፡፡ ከእርሻ ማሳዎች ወደ ዋና መንገድ የሚወስዱ መጋቢ መንገዶችም ለአምራቾቹ አስቸጋሪዎች ናቸው፡፡

ሌሎችም የእርሻ ሥራን የሚያተጓጉሉ፣ በተለይም በመስኖ ለማልማት እንቅፋት የሚፈጥሩ ልማዳዊ የአኗኗር ዘይቤዎች መቀየር እንዳለባቸው፣ ለችግር ጊዜ ብቻም ሳይሆን፣ ቀስ በቀስ ወደ ካፒታል ማከማቸት የሚያደርስ የቁጠባ ባህል መዳበር የክልሉ መንግሥት በሕዝቡ ውስጥ ማስረጽ የሚፈልጋቸው ሥራዎች መሆናቸውን ኃላፊዎቹ ይናገራሉ፡፡

በአገሪቱ በአሁኑ ወቅት የዕለት ደራሽ ዕርዳትን ጨምሮ የሴፍቲኔት ፕሮግራም የሚያካልላቸው 9.7 ሚሊዮን ሰዎች እንዳሉ የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ይፋ ያደረገው የቅርብ ጊዜ ሪፖርት ይጠቁማል፡፡ በተለይ የዕለት ተደራሽ ዕርዳታ ለማቅረብ አሁንም ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደሚያስፈልግ ሲታወቅ፣ ከምግብ እጥረቱ ባሻገር እንደ አጣዳፊ የትውከትና የተቅማጥ (አተት) በሽታ የተከሰተባቸው አካባቢዎች ገና በማገገም ላይ እንደሚገኙ የተመድ ሰብዓዊ ጉዳይ ማተባበሪያ ጽሕፈተ ቤት ሪፖርት ይጠቁማል፡፡ ከሁሉ በላይ ደግሞ አዲስ ድርቅ ሊቀሰቀስ እንደሚችል ማስታወቁም በመኸር ወቅት የታየውን መንሰራራት ሥጋት ውስጥ ሊከተው እንደሚችል ይጠበቃል፡፡

 

Standard (Image)

በአፋር ክልል በግማሽ ቢሊዮን ብር የጨው ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ሊገነባ ነው

$
0
0

- ከውጭ የሚገባውን 90 ሺሕ ቶን የገበታ ጨው ያስቀራል ተብሏል

በአፋር ክልል አፍዴራ ወረዳ በ500 ሚሊዮን ብር ወጪ የጨው ፋብሪካ ሊቋቋም ነው፡፡ ለፋብሪካው ግንባታ ሐሙስ ታኅሳስ 21ቀን 2009ዓ.ም የመሠረት ድንጋይ ተጥሏል፡፡

የአፋር ጨው ማቀነባበሪያና ማምረቻ የሚባል ስያሜ የተሰጠው አዲሱ ፋብሪካ፣ በካዳባ ጨው አቅራቢዎች አክሲዮን ማኅበርና በሰኢድ ያሲን ቢዝነስ ግሩፕ ባለቤትነት የተቋቋመ ነው፡፡ 49 በመቶ የፋብሪካው የባለቤትነት ድርሻ በካዳባ የተያዘ ሲሆን፣ 51 በመቶው ደግሞ የሰኢድ ያሲን ኩባንያ ድርሻ መሆኑ ታውቋል፡፡

በአካባቢው የሚመረተውን ጨው የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም  ከኢዮዲን ንጥረ ነገር ጋር የመቀላቀል ሥራ ቀደም ብሎም ሊሠራበት እንደነበር፣ አሠራሩ ግን አጥጋቢ ስላልነበር አዮዲን የመቀቀላቀሉን ሥራ በፋብሪካ ደረጃ የማሳደግ ሐሳብ  የተጠነሰሰው ከሁለት ዓመታት በፊት መሆኑን የሚናገሩት፣ የካዳባ ጨው አቅራቢዎች አክሲዮን ማኅበር የሥራ አመራር ቦርድ አባልና የቢዝነስ አማካሪ አቶ ሰይፉ ኪዳኔ ናቸው፡፡ በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፣ በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ በንግድ ሚኒስቴር፣ በምግብ መድኃኒትና ጤና ክብካቤ ቁጥጥርና አስተዳደር ባለሥልጣን፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና በሌሎችም ባለድርሻ አካላት የበላይ ጠባቂነት የአዋጭነት ጥናት ተደርጎበት ፋብሪካውን የማቋቋም እንቅስቃሴ እንደተጀመረ አቶ ሰይፉ ተናግረዋል፡፡

በ200,000 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የሚገነባው ፋብሪካ፣ በወር አንድ ሚሊዮን ኩንታል ጨው የማምረት አቅም እንዳለው ታውቋል፡፡ እንደ አቶ ሰይፉ ገለጻ፣ የአፍዴራ ጨው ያልተበከለ የባህር ጨው በመሆኑ ተፈላጊነቱ ከፍተኛ ነው፡፡ በተጨማሪም የጨው ይዘቱ ከፍተኛ ነው፡፡ ከቀይ ባህር የሚመረተው ጨው የሶዲየም ክሎራይድ ይዘቱ 66 በመቶ ሲሆን፣ የአፍዴራ ግን 97.99 በመቶ ነው፡፡ ከዚህ አንፃር የጨው ምርት ለውጭ ገበያ ማቅረብ ቢቻል ለአገሪቱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ማስገኘት ይቻላል ብለዋል፡፡

አዲስ የሚቋቋመው ፋብሪካም ይህንን ታሳቢ ያደረገና የአውሮፓን ቴክኖሎጂ በመጠቀም የሚዋቀር ነው፡፡ ጥራት ያለው ጨው በማምረት እንደ ደቡብ ሱዳን፣ ብሩንዲ፣ እንዲሁም እንደ ሩዋንዳ ላሉ አገሮች ለመላክ መታሰቡም ተገልጿል፡፡  ለአውሮፓና ለአሜሪካ ገበያዎች ለማቅረብም ጥናት እየተደረገ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡ አገሪቱ በየዓመቱ ከውጭ የምታስገባውን 90,000 ቶን የገበታ ጨው በአገር ውስጥ ምርት ለመተካት ታቅዷል፡፡ ለእንስሳት መኖነት የሚውለውን አሞሌ ጨው በዘመናዊ መንገድ በማምረት በአሁኑ ወቅት ከሚሸጥበት ዋጋ በግማሽ ቀንሶ ሊሰጥ እንደሚችልም ዋጋ  ተገልጿል፡፡ ለኢንደስትሪ ግብዓትነት የሚውሉ የተለያዩ ኬሚካሎችንም አዲስ በሚገነባው ፋብሪካ ውስጥ ለማምረት መታሰቡን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በሁለቱ ድርጅቶች ጥምረት የተቋቋመው አፋር ጨው ማቀነባበሪያና ማምረቻ፣ ኢዛና ጨው የተባለውን ማቀነባበሪያ ተቋም ለስድስት ወር በሊዝ በመከራየት ጨው እያቀነባበረ ይገኛል፡፡ የፋብሪካ የማምረት አቅም በወር 300,000 ኩንታል ነው፡፡ የአገሪቱ ወርሀዊ የገበታ ጨው ፍላጎት ከ380,000 በላይ ሲሆን፣ ለኢንዱስትሪ ግብዓትነት ከሚያስፈልገው ጋር ተደምሮ በወር ከ450,000 እስከ 500,000 ኩንታል ይፈለጋል፡፡ ይህ በመሆኑም የፋብሪካውን የማምረት አቅም በወር 400,000 ለማድረስ ታቅዷል፡፡ ይህ ምርት ግን የአዲሱ ፋብሪካ ግንባታ እስኪጠናቀቅ ለስድስት ወራት ያህል የሚቆይ ነው ተብሏል፡፡

በካዳባ አክሲዮን ማኅበር የሥራ አመራር ቦርድ አባል የሆኑት አቶ ሳዲቅ መሐመድ፣ ‹‹በአፍዴራ ሐይቅ ዙሪያ በጨው ምርት ሥራ የተሰማሩ አምራቾች ድርጅቱን እንዲቀላቀሉ እንፈልጋለን፤›› በማለት ማኅበሩ የአባላቱን ቁጥር የማብዛት ፍላጎት እንዳለው ተናግረዋል፡፡  የፋብሪካው ግንባታ የመሠረተ ድንጋይ በተጣለ ማግሥት ግንባታው እንደሚጀመርና በስድስት ወራት ውስጥ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምርም አስታውቀዋል፡፡

ከካዳባ ጋር በባለቤትነት ፋብሪካውን እያቋቋመ የሚገኘው ሰኢድ ያሲን ቢዝነስ ግሩፕ፣ ካዳባ ከመፈጠሩ በፊት ከአፍዴራ አምራቾች ጨው እየገዛ ለአገሪቱ ያቀርብ የነበረ ድርጅት ነው፡፡ በ2006 ዓ.ም. ካዳባ ሲቋቋም የማከፋፈሉን ሥራ ተቀብሎት መሥራት ጀምሮ ነበር፡፡

የአፍዴራ ጨው በባለሙያ ክትትል ተደርጎለት ቢመረት ከሌሎች አካባቢዎች (ከዶቢና ከአፍቄር) ከሚመረተውም ሆነ ከውጭ ከሚገባው ጭምር በጥራቱ የተሻለ እንደሆነ ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡ የአፍዴራ ጨው ሐይቅ ከብክለት የፀዳ፣ ባዕድ ነገሮች ያልተቀላቀሉበት ንፁህ የጨው ክምችት የሚገኝበት እንደሆነ በጥናት ተረጋግጧል፡፡ ይሁን እንጂ ለአምራቾች ዘንድ ለጥራት ትኩረት ስለማይሰጥ ከማምረቻ ኩሬው መሬ እየወጣ መሬት ላይ ይከመራል፡፡ ለብዙ ጊዜም መሬት ላይ ስለመሚቀመጥ አቧራና ሌሎች ባዕዳን ነገሮች እየበከሉት፤ በምርት ሒደት ወቅትም በባለሙያ የታገዘ ክትትል ስለማይደግበት፣ ሽያጩም በኮታ ስለሚደለደልና የጥራት ውድድር ስለሌለ በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ የጨው ጥራት ችግር ተንሰራፍቶ ይኛል፡፡

 

 

 

Standard (Image)

የንግድ ምክር ቤቱ አጣሪ ግብር ኃይል የወደፊት ዕርምጃ

$
0
0

የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤትን በፕሬዚዳንትነት፣ በምክትል ፕሬዚዳንትና በቦርድ አባልነት ለማገልገል የሚችሉ ኃለፊዎችን ለመሰየም በየሁለት ዓመቱ ምርጫ ይካሄዳል፡፡ ይሁን እንጂ ምርጫው በሚካሄድባቸው ጊዜዎች የሚነሳው ውዝግብ እየተለመደ ከመጣ ከጀመረ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ ያለጭቅጭቅና ትርምስ የተካሄደ ምርጫ ማየት ዘበት እየሆነ መጥቷል፡፡

ንግድ ምክር ቤቶች በየጊዜው ተተኪና ጠንካራ አመራር ለምን አይኖራቸውም? የሚል ትችት እንዲነሳባቸው ምክንያቶች ከሆኑት አንዱ በውዝግብ መሃል ወደ አመራር ቦታው ደጋግመው የሚጡ ግለሰቦች ሳይወጡ ለዓመታት የሚጥኝ ብለው መንበራቸውን በመያዛቸው ነው፡፡  ለዚህ ወቀሳ ተጋላጭ አነጋጋሪ የሆነው ኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ነው፡፡ 

አመራሮቹ አንዴ የክልል ወይም የከተማ ንግድና ዘርፍ ምክር ቤት አመራር ቦታውን ይዘው ቆይተው ሲበቃጨው ደግም በሌላ የምርጫ ዘመን ወደ አገር አቀፉ ምክር ቤት በመምጣት ለዓመታት እየተፈራረቁ ቦታውን ይዘዋል መባሉ፣ በንግድ ምክር ቤቱ ይሄ ነው የሚባል የአመራሮች ለውጥ እንዳይታይ አድርጓል፡፡ ይህ መሆኑም ውዝግብ ውስጥ እንዲዘፈቅ እንዳስገደደው ሲተች ቢቆይም፣ አሁንም ከገባበት አዙሪት ሊወጣ አልቻለም፡፡ ይህንን ገጽታ ለመለወጥ የሚደረጉ ጥረቶችም ቢሆኑ፣ እክል ሲገጥማቸው መታየቱ ንግድ ምክር ቤቱ ላይ አሉታዊ ገጽታ አሳድሯል፡፡

በአሁኑ ወቅት በአመራር ቦታ ላይ ያለው የንግድ ምክር ቤቱ ቦርድም የሁለት ዓመት የሥልጣን ዘመኑ አብቅቷል፡፡ ይሁንና ጠቅላላ ጉባዔ ጠርቶ ምርጫ በማካሄድ ኃላፊነቱን ለማስረከብ እንዳልቻለ መግለጹ፣ የንግድ ምክር ቤቱን ችግር አሳይቷል፡፡ በሕግና በመተዳደርያ ደንብ በተቀመጠው አግባብ መሠረት፣ ጠቅላላ ጉባዔ ጠርቶ ወቅቱን ጠብቆ ምርጫ ያለማካሄዱ ዋነኛ ምክንያትም ከምርጫ ሥርዓት የሚነሱ ውዝግቦች ያሳደሩትና ለዓመታት ያልተፈታ ችግር ነው፡፡ የንግድ ምክር ቤቱ ቦርድ ጠቅላላ ጉባዔ አካሂዶ ኃላፊነቱን ማስረከብ ሲገባው፣ ለወራት የዘገየው ሕጋዊ አካሄዶችን ጥያቄ ውስጥ የሚከቱ ችግሮች እንደገጠሙት እንደሆነ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡ ማሳወቅ ብቻም ሳይሆን ስምንተኛውን ጠቅላላ ጉባዔ ለማካሄድ እንዳልችል እክል ሆነዋል ያላቸውችግሮች ለመፍታት 18ቱን አባል ንግድ ምክር ቤቶች ለመፍትሔ ውይይት ለመጥራት ተገዷል፡፡ አባል ምክር ቤቶቹ አጋጥመዋል የተባሉትን ችግሮች የሚፈትሽና ውሳኔ የሚሰጥ እንዲሁም፤ የዘገየውን ጠቅላላ ጉባዔ ለመጥራትና ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችል ሰባት አባላት የተካተቱበት ግብረ ኃይል አቋቁመዋል፡፡ ግብረ ኃይሉም ለሁለት ወራት ጉዳዩን ሲመረምር ቆይቶ፣ የደረሰበትን ድምዳሜና የውሳኔ ሐሳብ ለ18ቱም የምክር ቤቶች መሪዎች፣ ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ይፋ አድርጓል፡፡

ምክር ቤቱን ያጋጠሙት ችግሮች

የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ቦርድ አመራር፣ ጠቅላላ ጉባዔውን እንዳያካሂድ እንቅፋት ሆነዋል በማለት ካቀረባቸው ችግሮች መካከል ከንግድ ምክር ቤቶች የማቋቋሚያ አዋጅ ውጭ አባል ምክር ቤቶች ምርጫ አካሂደዋል መባሉ ነው፡፡ ምክር ቤቶቹ በአግባቡ ምርጫ ሳያካሂዱ ወደ ላይኛው እርከን ተወካይ አመራሮችን ከላኩ የሕግ ጥሰት ስለሚያስከትል፣ ጉዳዩ እንዲጣራለት በመፈለጉ ነው፡፡ ይህንኑ የተመለከቱ ቅሬታዎች ከተለያዩ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤቶች መቅረባቸውንም አስረድቷል፡፡ የሥር ንግድ ምክር ቤቶች ሳይወክሏቸው ወደ ላይኛው እርከን የመጡ አመራሮች መኖራቸውን የሚያሳዩ ቅሬታዎች በመቅረባቸው፣ ይህ ቅሬታ ሳይፈታ የብሔራዊ ንግድ ምክር ቤቱን ጠቅላላ ጉባዔ ማካሄድ ችግር ሆኖብኛል ማለቱ ተጠቅሷል፡፡ ይህንና ሌሎችም ችግሮችን እንዲያጣራ የተሰየመው አጣሪ ኮሚቴ፣ ለሁለት ወራት ያደረገውን የማጣራት ሥራ አጠናቆ ሰኞ ዕለት፣ ታኅሳስ 23 ቀን 2009 ዓ.ም. ውሳኔ አዘል ሪፖርቱን አሰምቷል፡፡

የግብረ ኃይሉ ሪፖርት

የግብረ ኃይሉ ሰብሳቢና የትግራይ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ አሰፋ ገብረሥላሴ በሪፖርታቸው እንደጠቆሙት፣ ውሳኔ ሊሰጥባቸው ይገባል ተብለው የታመነባቸውን ጉዳዮች በመለየት በሰባት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ተላልፏል፡፡ በተለይ ስምንተኛውን ጠቅላላ ጉባዔ ለመጥራት የሚያስችልና ወደፊት የሚመረተው አዲስ አመራርም ኃላፊነቱን ከተረከበ በኋላ ሊተገብራቸው ይገባል የተባሉ ሐሳቦችም የተካተቱበት ነው፡፡ ለንግድ ምክር ቤቱ የውዝግብ ምንጭ የሆኑ ጉዳዮች ላይ የደረሰበትን ውሳኔም ግብረ ኃይሉን ለሰየሙት ለ18ቱ አባል ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤቶች አሰምቷል፡፡

 በአባል ምክር ቤቶች ቀረቡ የተባሉ ቅሬታዎችን በዝርዝር እንደፈተሸ የጠቀሰው ግብረ ኃይሉ፣ የቀረቡት ቅሬታዎች ሙሉ በሙሉ የሕግ ጥሰት ተፈጽሟል የሚል ክስ ያስተናገዱ ክሶች ሆነ ተገኝተዋል፡፡ አብዛኞቹም የምርጫ ሥነ ሥርዓት ግድፈት፣ የአወካከልና የደንብ ጥሰት ቅሬታዎች እንደነበሩ ተጠቅሷል፡፡ ግብረ ኃይሉ የቀሩበለትን ቅሬታዎች ለመፍታት የሚያችሉ መረጃዎችን ሰብስቦ ለማጣራት ረዥም ጊዜ የሚጠይቅና የሕግ ምክርም የሚያሻው ሥራ ቢሆንምበትም፣ ከሕግ አኳያ ባሉ ጉዳዮች ላይ ተንተርሶ ፍተሻ በማድረግ ከውሳኔ ላይ እንደደረሰ ይፋ አድርጓል፡፡

እያንዳንዱ አባል ምክር ቤት በአዋጁ መሠረት በዓመት አንድ ጊዜ ጠቅላላ ጉባዔውን፣ በየሁለት ዓመቱም ምርጫ ማካሄድና ለጠቅላላ ጉባዔ የኦዲት ሪፖርት ማቅረቡ ተረጋግጦ ለኢትዮጵያ ምክር ቤት ጉባዔ ዕጩ ማቅረብ አለበት የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሷል፡፡ አባል ምክር ቤቶች ከታች እስከ ላይ አባሎቻቸውን ያሳተፈ ጉባዔ ማካሄዳቸው ተረጋግጦ፣ ለጠቅላላ ጉባዔ እንዲቀርቡና ምክር ቤቶቹም ለሕግ ተገዥ በመሆን ግዴታቸውን እንዲወጡ በማለት ወስኗል፡፡

በሚደረገው የማጣራት ሒደት ሕጉን ያሟሉ ብቻ ለጠቅላላ ጉባዔ እንዲቀርቡ፣ በተለይም ከታች ጀምሮ አሳታፊ በሆነ የምርጫ ሥነ ሥርዓት እንዲካሄድ ያሳሰበው ግብረ ኃይሉ፣ ከታች ምክር ቤት ሳይወከሉ ለላይኛው ምክር ቤት ውክልና የቀረቡ አባላት ካሉ የሕግ ጥሰት እየፈጸሙ መሆናቸውን አውቀው እንዲያስተካክሉ በማድረግ የአገር አቀፉ ምክር ምርጫ መካሄድ እንደሚችል ውሳኔውን አሳውቋል፡፡

በአጠቃላይ ሕግ መመርያና ደንብ የጣሰ የምርጫ ሒደት ካለ የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት የማጣራት ኃላፊነቱን ወስዶ ለጉባዔ ዝግጁ እንዲያደርግ በማለት ግብረ ኃይሉ ያቀረበው የውሳኔ ሐሳብ በ18ቱ ንግድ ምክር ቤቶች ተቀባይነት አግኝቷል፡፡ በዚሁ መሠረት ኃላፊነቱ አሁን ያለው ቦርድ ወስዶ በማጣራት ውሳኔ እንዲሰጥበት ተወስኗል፡፡

በዝርዝር ከቀረቡት የግብረ ኃይሉ ውሳኔዎች ውስጥ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ የሌለው ነጋዴ ከአባልነት እንዲሰረዝ፣ ሕጋዊ ሠርተፍኬት የሌለው ከተማ፣ ወረዳና ክልልም እንዲሁ ከአባልነት እንዲሰረዝ የሚሉት ይገኙበታል፡፡ ይህ የግብረ ኃይሉ ውሳኔ አባል የንግድና የዘርፍ ምክር ቤቶች በአባልነት የሚያቀርቧቸውን የአባላት ቁጥር ለማጥራት እንደሚያስችል ታምኖበታል፡፡   

አቶ አሰፋ እንደጠቀሱትም፣ ግብረ ኃይሉ በዚህ ጉዳይ ላይ ያሳለፈው ውሳኔ አዋጁን መሠረት በማድረግ፣ ጉባዔው እንዲካሄድና የሕግ ልዕልናን በማረጋገጥ ፍትሐዊ ምርጫ ይካሄዳል በሚል እምነት ነው፡፡ በንግድ ምክር ቤቱ አዋጅ መሠረት ሊያሟሉ ይገባቸዋል ተብለው የተቀመጡ መሥፈርቶችን ስለማሟላታቸው በተደረገ  የማጣራት ሥራም የአንድ ክልል ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት እስከ ቅርብ ጊዜ የምዝገባ ሠርተፍኬት ሳይኖረው ሲመርጥና ሲያስመርጥ መቆየቱነ እንደረጋገጠበት ገልጸዋል፡፡ በግብረ ኃይሉ ሪፖርት መሠረት የምዝገባ ሰርተፍኬት ሳይኖረው ሲመርጥና ሲመረጥ ቆይቷል የተባለው የሶማሌ ክልል ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ነው፡፡ ለዚህ ግድፈት የኢትዮጵያ ንግድ ምክር ቤት ተጠያቂ እንደሆነ ግብረ ኃይሉ አስታውቋል፡፡

በመጪው ምርጫ ግን አባል ምክር ቤቶች የምዝገባ ሰርተፍኬታቸው ታይቶና ሕጋዊነታቸው ተረጋግጦ እንዲሳተፉ የማድረጉ አሠራር በሕጉ መሠረት እንዲፈጸም ለምክር ቤቱ ጽሕፈት ቤት መመርያ አስተላልፎ ተግባራዊ እንደተደረገ ግብረ ኃይሉ ጠቅሷል፡፡

የተሻሻለው መተዳደርያ ደንብና የሚቀርፋቸው ቅሬታዎች

በግብረ ኃይሉ ውሳኔ ከተላለፈባቸው መካከል መስከረም 6 ቀን 2008 ዓ.ም. ተሻሽሎ የፀደቀው የንግድ ምክር ቤቱን መተዳደርያ ደንብን የሚመለከተው ይገኝበታል፡፡ ተሻሻለ የተባለው መተዳደርያ ደንብ በአባል ምክር ቤቶች በኩል በርካታ ቅሬታዎችን ያስነሳ በመሆኑ፣ በምክር ቤቶች በኩል ለመተባበር የሚያስችል ተጨባጭ ሁኔታ   አለመታየቱን የግብረ ኃይሉ ሪፖርት ይገልጻል፡፡ ለጭቅጭቅም ዋነኛ መንስዔ ሊሆን ችሏል፡፡ ከተሻሻለው መተዳደሪያ ደንብ ውስጥ ከ18 አባል ምክር ቤቶች 12ቱ በተለይ የአባልነት መዋጮን የተመለከተውን አንቀጽ አልተቀበሉትም፡፡ መተዳደርያ ደንቡ ሲፀድቅም፣ በምክር ቤቱ አባላት በቂ ውይይት እንዳልተደረገበት በተለያዩ አጋጣሚዎች በመግለጽ፣ በሥራ ላይ ያለው ቦርድም በዚህ ጉዳይ ላይ መግባባት ላይ መድረስ ስላልቻለ የመተዳደርያ ደንቡ ድጋሚ ለጠቅላላ ጉባዔ ቀርቦ እንዲሻሻል ውሳኔ አሳልፏል፡፡

አምስት ብር ሲያከራክር

በስብሰባ ወቅት የአባል ንግድ ምክር ቤቶችን አመራሮችና የግብረ ኃይሉን አባላት ካፋጩና ረጅም ጊዜ ከወሰዱ ጉዳዮች መካከል አንዱ 18ቱ አባል ምክር ቤቶች ለኢትዮጵያ ንግድ ምክር ቤት የሚየደርጉት ዓመታዊ መወጮ ምን ያህል ይሁን የሚለው ነበር፡፡

በተሻሻለው መተዳደርያ ደንብ ውስጥ 18ቱ አባል ምክር
ቤቶች በየዓመቱ በየአንዳንዱ ግለሰብ አባል 5 ብር እንዲያዋጡ ይጠይቃል፡፡ ይህ ክፍያ በዝቷል ተብሎ ወደ ሁለት ብር ዝቅ ይበል የለም ሦስት ብር ይሁን የሚለው ኃሳብ ሲያሟግት ውሏል፡፡ በአንድ ነጋዴ አባል ይህንን የአምስት ብር ዓመታዊ ክፍያ ለመክፈል አይቻለንም የሚለው ሐሳብ ረዥም ጊዜ ወስዶ ማከራከሩ አስገራሚ ነበር፡፡

ግድ የለም በአንድ አባል ሦስት ብር መዋጮ ይከፈል የሚለው የግብረ ኃይሉን ውሳኔ ለመቀበል ብዙ ማነታረኩ ብቻም ሳይሆን ይህንንም ማሟላት በማይቻልበት ወቅት በዱቤ እንድንከፍል ታሳቢ ይደረግለት ሲሉም ተደምጠዋል፡፡ በመጨረሻው ግን በእያንዳንዱ አባል ሦስት ብር መዋጮ ይደረግ በሚለው ሐሳብ ላይ ድምፅ ተሰጥቶ ተቋጭቷል፡፡ አንድ ነጋዴ በአባልነቱ በዓመት አምስት ብር እንዲያዋጣ ለማድረግ ይህንን ያህል ከባድና አከራካሪ የመሆኑ ጉዳይ እንቆቅልሽ መሆኑ ግን አልቀረም፡፡

ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ግብረ ኃይሉ 18ቱ አባል ምክር ቤቶች ባለባቸው የተጣራ አባል ልክ ተሰልቶ ለአንድ አባል ሦስት ብር፣ ለነባርና ለአዲስ ማስመዝገቢያ አምስት ብር እንዲከፍሉ ተብሎ የነበረው በሦስት ወር እንዲሻሻል የውሳኔ ሐሳብ አቅርቧል፡፡ ከዚህ ቀደም የከፈሉ ካሉም ለወደፊቱ እንዲታሰብላቸው፣ እስካሁን ያልከፈሉ ግን በተጣራ የአባል ቁጥራቸው ልክ የሦስት ብር ዕዳ ተመዝግቦባቸው በሰነድ ተፈርሞ ወደፊት እንዲከፍሉ ግብረ ኃይሉ ያቀረበው የውሳኔ ሐሳብ ድምፅ ተሰጥቶበት ተወስኗል፡፡

የምርጫ ውክልና

ግብረ ኃይሉ ከ18ቱ አባል ምክር ቤቶች በአገር አቀፉ ጠቅላላ ጉባዔ የሚወከሉ አባላት ቁጥር ስንት ይሁን በሚለው ነጥብ ላይ ያቀረበው የውሳኔ ሐሳብ ተቀባይነት አግኝቷል፡፡ በቀጥታ የሚወከሉ የዘርፍ አባላትና አነስተኛ ቁጥር ላላቸው ክልሎች በሥራ አመራር ቦርድ ምርጫ መሳተፍ እንዳለባቸው በተመለከተው አጀንዳ ውስጥ፣ አነስተኛ የአባላት ቁጥር ያላቸው ክልሎችም ይህን ጥያቄ የሚያነሱ በመሆኑ ግብረ ኃይሉ በዚህ ላይ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

እየተሠራበት ያለው የሥራ አመራር ቦርድ ዕጩ አቀራረብ ሥርዓት ፍትሐዊ ስላልሆነ፣ የዕጩ አቀራረብ ሥርዓቱ ማስተካከያ እንዲደረግበት ግብረ ኃይሉ መወሰኑን የገለጹት አቶ አሰፋ፣ ከሥራ አመራር ድልድል እስከ ፕሬዚዳንትነት ወይም ምክትል ፕሬዚዳንትነት ቦታ ያሉት ኃላፊነቶች ላይ አማራጭ ሐሳቦች የቀረቡ ቢሆንም ለምርጫ ሥርዓቱና ለዴሞክራሲያዊ ሒደቱ አሠራር አስቸጋሪ በመሆናቸው እስካሁን የነበረው የሥራ አመራር ቦርድ የዕጩ አቀራረብ ሒደት እንዲለወጥ አድርጓል፡፡ ከዚህ ቀደም እያንዳንዱ አባል ምክር ቤት 11 ዕጩዎችን የማቅረብ ዕድል ነበረው፡፡ ይህም በብዛት ዕጩ ያቀረቡ ክልሎች ብቻ ብዙ የማስመረጥ ዕድል እንዲገኙ የሚያደረግ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡  አገራዊ ምክር ቤቱ በተወሰኑ ተመራጮች ብቻ እንዳይያዝ፣ ውክልናውም ፍትሐዊ እንዲሆን በማሰብ የውክልና ቁጥሩ መቀየሩን ግብረ ኃይሉ አስታውቋል፡፡

በዚህ መሠረት የ18ቱ አባል ምክር ቤቶች የተለያየ ቁጥር የአባላት ብዛት ቢኖራቸውም በአባል ቁጥራቸው ድምፅ የመስጠት መብት እንደተጠበቀ ሆኖ ለአገራዊ ምክር ቤቱ ለምርጫ ውድድር ግን ሁሉም አባል ምክር ቤቶች ሁለት፣ ሁለት ዕጩዎችን ብቻ እንዲያቀርቡ የቀረበው የውሳኔ ሐሳብ አስተያየቶች ከተሰጠበት በኋላ እንዲተገበር ተወስኗል፡፡ የሚቀርቡት ሁለት ዕጩዎች የሚወደደሩት ለፕሬዚዳንትነት ወይም ለምክትል ፕሬዚዳንትነት አለያም በሥራ አመራር ቦርዱ ውስጥ በአባልነት ለመሳተፍ እንደሚሆን አመልክቷል፡፡

በዚህ መሠረት ለፕሬዚዳንትነት የሚወዳደር ዕጩ፣ ለምክትል ፕሬዚዳንትነት ወይም ለቦርድ አባልነት መወዳደር አይችልም፡፡ ለምክትል ፕሬዚዳንትነት የሚወዳደረውም ለፕሬዚዳንትነት ወይም ለቦርድ አመራር ሊወዳደር አይችልም፡፡ ለሥራ አመራር ቦርድ አባልነት የሚወዳደረው እንደዚሁ፡፡ በመተዳደርያ ደንብ ቁጥር 02/2008 መሠረት ማንኛውም በሥራ አመራር ቦርድ፣ በፕሬዚዳንትነትና በምክትል ፕሬዚዳንትነት ያገለገለ አመራር፣ የአገልግሎት ዘመኑ ለሁለት ተከታታይ የምርጫ ጊዜ ብቻ እንዲሆን፣ ከሁለት ጊዜ ምርጫ በኋላ በድጋሚ መመረጥ የሚችለው ቢያንስ ከአንድ ቆይታ በኋላ እንዲሆን በማለት የቀረበውም ሐሳብም ተቀባይነት አግኝቷል፡፡

የአስመራጭ ኮሚቴ ተወግዷል

ግብረ ኃይሉ ባደረገው ማጣራት፣ ለንግድ ምክር ቤቱ ውዝግቦች በተለይም በምርጫ ወቅት ለሚፈጠሩ ጭቅጭቆች አንዱ መንስዔ ምርጫውን ለማስፈጸም ሲባል የሚቋቋመው የምርጫ አስተባባሪ ኮሚቴ ነው፡፡ የጠቅላላ ጉባዔውን ሒደት፣ ውክልና ቀመርና የምርጫ አፈጻጸም ሥርዓት ለምርጫ አስተባባሪ ኮሚቴ የተሰጠው የሥራ መዘርዝርና ኃላፊነት ችግር ስለነበረበት፣ የኮሚቴ አሠራር እንዲቀር ተብሏል፡፡ ለስምንተኛው ጠቅላላ ጉባዔ ዝግጅትም የምርጫ አስተባባሪ ኮሚቴ መኖሩ ጠቀሜታ እንደማይኖረው በመታመኑ የአስመራጭ ኮሚቴ አወቃቀር ይቅር የሚለው ሐሳብ ድምፅ ተሰጥቶበት አልፏል፡፡ ስለዚህ ኮሚቴው ቀርቶ ኮሚቴው ይሠራው የነበረውን ሥራ ጽሕፈት ቤቱ ተረክቦ፣ የሚቀርቡት ዕጩዎች መመዘኛውን ማሟላታቸውን በጥንቃቄ ፈትሾ እንዲያቀርባቸው ኃላፊነት ተሰጥቶታል፡፡

የውጭ ጉዞዎች

ንግድ ምክር ቤቱ በተደጋጋሚ የሚወቀስበት አንዱ ጉዳይ በአመራር ላይ ያሉ አባላት የሚያደርጓቸው የውጭ አገር ጉዞዎችን የሚመለከተው ነው፡፡ በግብረ ኃይሉ ሪፖርትም ይህ ጉዳይ ተካቷል፡፡ በዚህ ዙሪያ ያሉትን ጉዳዮች አጣርቻለሁ ያለው ግብረ ኃይሉ፣ ‹‹አገር አቀፍ ምክር ቤቱ የተለያየ የውጭ ጉዞ ፕሮግራሞች እንዳሉት ቢታወቅም፣ በተመራጭ ቦርዱም ይሁን በአባል ምክር ቤቶች ዘንድ የቅሬታ ምንጭ በመሆን ላይ ይገኛል፤›› ብሏል፡፡ ዋናው የግልጽነት ችግር መነሻ ተብሎም ይጠቀሳል፡፡ በመሆኑም የውጭ ጉዞዎች ግልጽነት እንዲኖራቸው፣ ፕሬዚዳንቶች ወይም ጸሐፊዎች የሚያደርጉት ጉዞም ለቦርዱ በማሳወቅ ሪፖርት የማቅረብ ግዴታ እንዲጣልባቸው ውሳኔ አሳልፏል፡፡ ከአባል ምክር ቤቶቹ ወደ ውጭ የሚላኩ ተወካዮች፣ አባል መሆናቸው ተረጋግጦ፣ ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለበት የውጭ ጉዞ ፕሮግራም እንዲዘጋጅና በመተዳደሪያ በደንቡ ውስጥም እንዲካተት በማለት ግብረ ኃይሉ ያቀረበውን ሐሳብ ቤቱ ተቀብሎታል፡፡

የአገሪቱ የንግድ ምክር ቤቶች ምንም እንኳ በአዋጅ ተቋቋመው የግል ዘርፉን በማገልገል ላይ ቢገኙም የተጠበቀው ያህል እየተጓዙ አይደለም በማለት የግብረ ኃይሉ በሪፖርቱ ተችቷቸዋል፡፡ በአገሪቱ ዋነኛ የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ የሚባሉ ባለሀብቶችም ከማኅበራቱ እየራቁ መሆናቸውና ለዚህም ምክንያቱ ብዙውን ጊዜ በምርጫ ጊዜ የሚታዩ ሽኩቻዎችና በየደረጃቸው በተደጋጋሚ ለምርጫ የሚቀርቡ ተወዳዳሪዎች በመተካካት ቦታቸውን ስለማለቁ ነው በማለት ምልከታውን አስቀምጧል፡፡ ለዚህም የአደረጃጀቱ ወይም የአዋጁ በየጊዜው አለመፈተሽና የአወቃቀር ችግሮች እንደሚጠቀሱም አመላክቷል፡፡

ቀጣዩ ዕርምጃ

 የ18ቱ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤቶች በስብሰባቸው ወቅት ግብረ ኃይሉ ባቀረባቸው የውሳኔ ሐሳቦች ላይ ከስምምነት ላይ የደረሱበትን ውሳኔ እንዲያተገብር ዋነኛ ኃላፊነት የተሰጠው ለቦርዱ ነው፡፡ በዕለቱ በተላለፈው ውሳኔ መሠረት፣ በተቀመጠው የሕግ አግባብ ያልተካሄደ ምርጫና ውክልና ካለ እስከማገድ የሚደርስ ኃላፊነት ተሰጥቶታል፡፡ ግብረ ኃይሉ በወሰነው መሠረት፣ መፈጸም ያለባቸው ጉዳዮች ተጠቃለው ጥር 30 ቀን 2009 ዓ.ም. አገር አቀፍ ምርጫ እንዲካሄድ ቀነ ገደብ አስቀምጧል፡፡ 

Standard (Image)

የኮንስትራክሽን ኢንስቲትዩት የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅዱን ይፋ አደረገ

$
0
0

 -  የመንግሥት ፕሮጀክቶችን ለመቆጣጠርና አዲት ለማድረግ ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ ተደርጓል

ከተመሠረተ ሁለት ዓመት ከመንፈቅ ያስቆጠረው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ለአምስት ዓመታት የሚመራበትን ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ይፋ አደረገ፡፡ ዕቅዱ ምንም እንኳ ረቂቅ የዕቅዱ ሰነድ ባለፈው ዓመት ቢዘጋጅም ማሻሻዎች ማድረግ በማስፈልጉ ያንን በማካተት ለሚለመከታቸው ባለድርሻ አካላት የቀረበው ታኅሳስ 26 ቀን 2009 ዓ.ም. ነበር፡፡

ኢንስቲትዩቱ ለመጪዎቹ አምስት ዓመታት በኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ማኔጅመንት ዘርፍ የሚተገብራቸውን ዋና ዋና ተግባራት ያካተተበት ስትራቴጂካዊ ዕቅድ፣ ትኩረት ከሰጠባቸው መስኮች መካከል በዘርፉ ያለውን የሰው ኃይል አቅም መገንባት አንዱ ነው፡፡

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዮሴፍ ብሩ የስትራቴጂክ ዕቅዱን ረቂቅ ሰነድ፣ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ ከፈደራልና ከክልል መንግሥት ለተውጣጡ ባለድርሻዎች በማቅረብ ውይይት እንዲካሄድበት አድርገዋል፡፡

ዋና ዳይሬክትሩ ባቀረቡት ዕቅድ ውስጥ ለኢንስቲትዩቱ እንዲሰጥ ከጠየቋቸው መካከል አንዱና ዋናው አስገዳጅ የሕግ ማዕቀፍ እንዲሰጠው የሚለው ይጎላል፡፡ እንደ ዶ/ር ብሩ ማባብራሪያ ከሆነ፣ ኢንስቲትዩቱ የሕግ ሥልጣን ተሰጥቶት በአስገዳጅነት የመንግሥትን ፖሊሲ ማስፈጸም እንዳይችል የሚገድበው፣ የተቋቋመበት ደንብ እንዲሻሻልም ጠይቀዋል፡፡ ዶ/ር ዮሴፍ ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት፣ የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በተለይ የመንግሥት የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶችን የአፈጻጸም ሒደት ለመገምገምና ለመቆጣጠር እንዲሁም ኦዲት ለማድረግ የሚያስችለው የሕግ ማዕቀፍ ሊሰጠው ይገባል፡፡

ይሁንና ይህ ጥያቄ በሕግ የማፈቀድለት ከሆኑ ባሻገር የኢንስቲትዩቱ ኃላፊነት ባለመሆኑ፣ የመንግሥት ፕሮጀክቶችን የአፈጻጸም ሒደት በአስገዳጅ የሕግ ማዕቀፍ የመገምገምም ሆነ ኦዲት የማድረግ ጥያቄው በሚኒስቴሩ ተቀባይነት እንዳላገኘ ታውቋል፡፡ የኮንስትራክሽን ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ገብረመስቀል ጫላ ከሪፖርተር ተጠይቀው እንዳብራሩት፣ ኢንስቲትዩቱ በዚህ ደረጃ ለመንቀሳቀስ የሚስችለው የሕግ ማዕቀፍ ስለሌለው ጥያቄው አልተስተናገደም፡፡

በአምስት ዓመቱ የኢንስቲትዩቱ ስትራቴጂክ ዕቅድ ውስጥ በአገሪቱ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ውስጥ ከሚታዩ አንኳር አንኳር ችግሮች መካከል ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ መሆኑ፣ የጥራት ችግሮች የተበራከቱበት መሆኑ፣ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ ውስጥ የማይጠናቀቁበት መሆኑ፣ የግንባታ ፍላጎትና አቅም አለመጣጣማቸው እንዲሁም ከፍተኛ የሰለጠነ የሰው ኃይል እጥረት መኖሩ የሚጠቀሱት ናቸው፡፡ ከዚህ ባሻገር በኮንስትራክሽን ዘርፍ ውስጥ የሚታየው ሙስናም ሥር የሰደደ ከመሆኑም ባሻገር በተለይ በግዥ ሒደት የሚታየው ሕገወጥ አሠራር ኢንስቲትዩቱ መፍትሔ እንደሚፈልግላቸው ይጠበቃል፡፡

እንደ ዶ/ር ዮሴፍ ማብራሪያ ከሆነ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ማኔጀመንት ሙያ በአገሪቱ ብዙም የማይታወቅ በመሆኑ ይህንን ከመቅረፍ ጀምሮ፣ ከተመራቂ ተማሪዎች እስከ ልምድ ያካበቱት ድረስ የሙያ ምዘናና የሚደረግባች አሠራሮች እንደሚኖሩ ይጠበቃል፡፡ በመሆኑም የልቀት ማዕከል ለማቋቋም ማቀዱንና በክልሎችም ቅርንፋፍ ጽሕፈት ቤቶችን በመክፈት የቴክኒክና የክህሎት ሥልጠና ከመስጠት ባሻገር ለፕሮጀክቶች የማማከር ድጋፍና መሠል ሥራዎችን የማከናወን ተልዕኮ እንደሚኖረውም አብራርተዋል፡፡

ባለፉት ሁለት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ካከናወናቸው ተግባራት መከካል ለአዲስ አበባ ቤቶች ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ሲሰጥ የቆየው የዲዛይን፣ የግብዓት አጠቃቀምና መሰል ሥራዎች እንደሚጠቀሱለት ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ገብረ መስቀል አስታውሰዋል፡፡    

Standard (Image)

ዘቢዳር ቢራ በጣት የሚከፈት ጠርሙስ በማስተዋወቅ ገበያውን ተቀላቀለ

$
0
0

በቤልጂየሙ ቢራ ጠማቂ፣ ዩኒብራ ኩባንያና በጀማር ሁለገብ ኢንስትሪ አክሲዮን ማኅበር ባለቤትነት የተቋቋመው ዘቢዳር ቢራ፣ ከመነሻው በዓመት 350 ሺሕ ሔክቶሊትር ቢራ የሚያመርት ፋብሪካውን በደቡብ ክልል አስገንብቷል፡፡ በ150 ሺሕ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ በተገነባው ፋብሪካ የተጠመቀው ቢራ ለገበያ መቅረብ ጀምሯል፡፡

የዘቢዳር ቢራ ፋብሪካ ግንባታ፣ ዩኒብራ ከተቀላቀለው በኋላ በተለይ ባለፉት ሦስት ዓመታት ውስጥ ሲካሄድ መቆየቱ ታውቋል፡፡ በዚህ ዓመት ለገና በዓል ዋዜማም ቢራው ለገበያ ቀርቧል፡፡ ቢራው ታኅሳስ 27 ቀን 2009 ዓ.ም. ይፋ በተደረገበት ወቅት፣ ጋቨን ብራውን የዘቢዳር ቢራ ዋና ሥራ አስኪያጅ እንዳብራሩት፣ እስካሁን ከተለመደው የቢራ ጠርሙስ ለየት ያለ አዲስ አቀራረብ አስተዋውቋል፡፡ ያለ ጠርሙስ መክፈቻ በጣት የሚከፈተው የዘቢዳር ቢራ፣ የገብስ ብቅል፣ ጌሾና ውኃ ብቻ በመጠቀም እንደሚመረት ያስታወቁት ሚስተር ብራውን፣ ቢራው በጊዜያዊነት በደቡብ ክልልና በአዲስ አበባ ከገበያ እንደሚቀርብ ገልጸዋል፡፡

የቢራ ኢንዱስትሪው በርካታ የአገር ውስጥና የውጭ ኩባንያዎች የሚሳተፉበት እንደመሆኑ፣ በገበያው ውስጥ ያለው ፉክክር ያሠጋው እንደሆነ የተጠየቁት ሚነስተር ብራውን፣ ዘቢዳር ቢራ ገበያውን ያለ ችግር መቀላቀል የሚችልባቸው የገበያ ስትራቴጂዎችን ይዞ እንደመጣና የገበያ ችግር ሥጋት እንደማይሆንበት ገልጸዋል፡፡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት አገሪቱ የቢራ ገበያ በያመቱ ከ15 እስከ 20 በመቶ እያደገ ይገኛል፡፡ ይህ መሆኑም ብቻ ሳይሆን ቢራ ለመጠጣት የሚያስችል ገቢ የሚያገኙ ሰዎች ቁጥር መበራከትም በኢንዲስትሪው ለሚንቀሳቀሱ ኩባንያዎች ቁጥር መጨመር አስተዋጽኦ እንዳደረገ ይታመናል፡፡

በዩኒብራ የ60 በመቶ የባለቤትነት ድርሻ፣ ከሦስት ዓመት በፊት በተደረገ ድርድርና ስምምነት መሠረት ወደ ሥራ በመግባት ምርቱን ለገበያ ያበቃው ዘቢዳር ቢራ፣ በጀማር ሁለገብ የ40 በመቶ ባለቤነት የተዋቀረ ነው፡፡ ጀማር ሁለገብ ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማኅበር፣ ከ1100 ያላነሱ ባለአክሲዮኖች የመሠረቱት አክሲዮን ማኅበር ሲሆን፣ የባንክና የኢንሹራንስ ኃላፊዎች፣ የሆቴል ባለንብረቶችና ሌሎችም የተሳተፉበት እንደሆነ የዘቢዳር ቢራ፣ የብራንድ ማናጀር ወ/ሮ ራዕይ መሰለ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ዩኒብራ ኩባንያ እ.ኤ.አ. በ1960 የተመሠረተ የቤልጂየም ቢራ ጠማቂ ኩባንያ ሲሆን፣ በምሥረታው ማግሥት ወደ አፍሪካ በመምጣት ፋብሪካዎችን እንደተከለ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ስኮል የተሰኘውን የቢራ ብራንድ በአፍሪካ በባለቤትነት የሚያስተዳድረው ዩኒብራ፣ በቢራ ጠመቃ በቤልጂየም ከሚታወቁ ትልልቅ ኩባንያዎች መካከል ይጠቀሳል፡፡

በጉራጌ ዞን ዘቢዳር ማሲፍ ከተባለው ተራራ መጠሪያውን የተዋሰው ዘቢዳር ቢራ፣ በጉብርየ አካባቢ ለሚገኙ ከ200 በላይ ነዋሪዎች የሥራ ዕድል መፍጠሩንም የፋብሪካው ኃላፊዎች ጠቅሰዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ቢጂአይ ኢትየጵያ፣ ዳሸን ቢራ፣ ሐይኒከን ቢራ፣ ሜታ ቢራ፣ ሐበሻ ቢራ እንዲሁም ዘቢዳር ቢራ በአገሪቱ ያሉትን 11 የቢራ ፋብሪካዎች የሚያስተዳድሩ ሰባቱ ኩባንያዎች ሆነዋል፡፡ መንግሥት በቢራ ኢንዱስትሪው ውስጥ ለመግባት ፍላጎት ያላቸው አዲዲስ ኩባንያዎችን የመቀበል ፍላጎቱ እየቀነሰ መምጣቱን ባለፈው ዓመት ማስታወቁ አይዘነጋም፡፡ ይህም ለገበያው ተመጣጣኝ ምርት ማቅረብ የሚችሉ ፋብሪካዎች ከመተከላቸውና የመጠጥ ኢንዱስትሪውንም ከዚህ በላይ ማስፋፋት የሕዝቡን የጤና ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት እንደሚሆን የመንግሥት ኃላፊዎች መጥቀሳቸው ይታወሳል፡፡ 

 

 

Standard (Image)

ለማገገም የሚፍገመገመው የወጪ ንግድ

$
0
0

አገሪቱ የወጪ ንግድ በአማካይ በ36.3 በመቶ እንደሚያድግ የሚያመላክት ግብ ከተጣለ ሁለት ዓመታት አልፈዋል፡፡ ይህ ዕቅድ በአምስት ዓመቱ የዕቅድ ዘመን ውስጥ ይሳካል ተብሎ የተቀመጠ ሲሆን፣ ከ2008 በጀት ዓመት ጀምሮ ከጠቅላላው የአገሪቱ የወጪ ንግድ ይገኛል ተብሎ የተቀመጠው ትንበያ 4.8 ቢሊዮን ዶላር ነው፡፡ ይህ ትንበያ በ2007 በጀት ዓመት የተገኘውን 3.01 ቢሊዮን ዶላር ታሳቢ በማድረግ ነው፡፡ በተግባር እንደታየው ግን በ2008 በጀት ዓመት የተመዘገበው የውጭ ምንዛሪ ገቢ ከተተነበየው ከ1.7 ቢሊዮን ዶላር በላይ ዝቅ ያለ ነው፡፡

በመጀመሪያው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን የዕቅድ ዘመን መጨረሻ (2007 ዓ.ም.) ወቅት፣ ከወጪ ንግድ 6.5 ቢሊዮን ዶላር እንደሚገኝ ሲጠበቅ እንደነበር አይዘነጋም፡፡ በ2002 ዓ.ም. የተገኘውን ሁለት ቢሊዮን ዶላር መነሻ በማድረግ የተሰላው ዕቅድ በ2007 ዓ.ም. ያስገኘው ውጤት ግን ከግማሽ በላይ ያነሰ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

በመጀመሪያው የዕቅዱ አምስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ በዓመት በአማካይ የተገኘው ገቢ 3.1 ቢሊዮን ዶላር ነበር፡፡ ለወጪ ንግድ ከሚቀርቡ ሸቀጦች መካከል ከቡና 783.3 ሚሊዮን ዶላር፣ ከቅባት እህሎች 481 ሚሊዮን ዶላር፣ ከጥራጥሬ 200.3 ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት ይታሰብ ነበር፡፡ ይሁንና ከቡና የገቢ ዕቅድ ውስጥ 61 በመቶ ብቻ ተሳክቷል፡፡ ከቅባት እህሎች 64 በመቶ፣ ከጥራጥሬ 42.4 በመቶ ብቻ ውጤት ተገኝቶ ዕቅዱ ተደምድሟል፡፡ ከ2008 በጀት ዓመት ጀምሮ እስከ ዕቅዱ ማጠቃለያ 2012 ድረስ የተቀመጠውም የወጪ ንግድ ገቢ ትንበያ አገሪቱ በዘርፉ እመርታ የምታሳይበት ይሆናል ቢባልም ከጅምሩ ዕቅዱና ክንውኑ ሳይገናኙ ቀርተዋል፡፡ በዕቅድ ዘመኑ መጨረሻ (በ2012 ዓ.ም.) የወጪ ንግድ አጠቃላይ ገቢ 13.9 ቢሊዮን ዶላር ይሆናል ተብሎ ተገምቷል፡፡ እንደትንበያው ከሆነ በ2009 ዓ.ም. 6.7 ቢሊዮን ዶላር፣ በ2010 ዓ.ም. 8.7 ቢሊዮን ዶላር፣ በ2011 ዓ.ም. 11.03 ቢሊዮን ዶላር እንዲሁም በ2012 ደግሞ 13.9 ቢሊዮን ዶላር እንደሚገኝ ታሳቢ ቢደረግም፣ ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ያለውና እስከ 2009 ዓ.ም. አጋማሽ የታየው አፈጻጸም በዕቅዱ መሠረት ገቢው እያደገደ እንዳልሆነ ነው፡፡

መንፈቅ ዓመቱን ካገባደደው የ2009 በጀት ዓመት፣ ከሁለት ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ቢጠበቅም ባለፉት አምስት ወራት የተገኘው ግን 1.57 ቢሊዮን ዶላር ብቻ ነው፡፡ በአምስቱ ወራቶች ውስጥ ይገኛል የተባለው ገቢ እርግጥ 1.8 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ነው፡፡ በአምስቱ ወራት ውስጥ ከወጪ ንግድ የተገኘው ገቢ በዕቅድ ከተያዘው ግብ ጋር ሲነፃፀር አነስተኛ መሆኑ ብቻም ሳይሆን ከዓምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር በንፅፅር ሲታይ ከ50 ሚሊዮን ዶላር በላይ ቅናሽ የታየበት በመሆኑ፣ አሁንም የታሰበውን ያህል ገቢ ማስገኘት ያልቻለ ዘርፍ ሆኖ ቀጥሏል፡፡

 በሁለቱም የዕቅድ ዘመኖች ውስጥ ዋና የወጪ ንግድ ገቢ ምህዋር የሆኑት የግብርና ምርቶች ናቸው፡፡ ከግብርና ምርቶች ውስጥ ቡና፣ የቅባት እህሎች፣ ጥራጥሬ፣ አትክልትና ፍራፍሬ፣ የቀንድ ከብትና የጫት ምርቶች በቀዳሚነት የሚጠቀሱ ሲሆን፣ ከእነዚህ ምርቶች የሚገኘው የውጭ ምንዛሪ ገቢ ከ70 እስከ 80 በመቶ በላይ ድርሻ ይዟል፡፡

የ2009 በጀት ዓመት የወጪ ንግድ መረጃ የሚጠቁመው እነዚህ ምርቶች ቀዳሚ የወጪ ንግድ ገቢ ማስገኛ ቢሆኑም፣ በአፈጻጸም ደረጃ ከዕቅድ በታች እየተመዘገበባቸው በመሆኑ በበጀት ዓመቱ መጨረሻ ላይ ይገኛል ተብሎ የታቀደውን 4.8 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት ከባድ እንደሚያደርገው ከወዲሁ እየታየ ነው፡፡ በግማሽ ዓመቱ ግማሹን ገቢ ማግኘት አልተቻለም፡፡

በ2009 በጀት ዓመት ከቡና 2.9 ቢሊዮን ዶላር፣ ከቅባት እህሎች 904 ሚሊዮን ዶላር፣ ከጥራጥሬ 318 ሚሊዮን ዶላር፣ ከአትክልትና ፍራፍሬ 69 ሚሊዮን ዶላር፣ ከቀንድ ከብት 267 ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም ከጫት 324.7 ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት ታቅዷል፡፡ በግማሽ ዓመቱ ደግሞ በዓመቱ ከተያዘላቸው ግማሽ ያህሉን ያስገኛሉ ተብሎ ነበር፡፡ መረጃዎቹ የሚጠቁሙት ግን ከጫት፣ ከጥራጥሬና ከጥቂት ምርቶች በቀር በዕቅድ ወደተቀመጠለት የገቢ መጠን የተጠጋ ሸቀጥ አለመኖሩን ነው፡፡ እንደወርቅ፣ ታንታለም፣ የቀንድ ከብት፣ የኮንስትራክሽን ግብዓቶችና የመሳሰሉት ከዕቅዳቸው 50 በመቶ ያልደረሱ ናቸው፡፡ እነዚህ ምርቶች ከፍተኛ ገቢ ይገኝባቸዋል ተብለው ሲጠበቁ ነበር፡፡

በተለይ ከዋና ዋና የወጪ ንግድ ምርቶች እንደ ቅባት እህል ያሉ ምርቶች አሁንም ዝቅተኛ አፈጻጸም እያሳዩ ነው፡፡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ ከቡና ቀጥሎ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ በማስገኘት የሚጠቀሰው የቅባት እህሎች ዘርፍ በ2009 በጀት ዓመት ክዋኔው ዝቅተኛ ሆኖ መገኘቱ፣ በወጪ ንግዱ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሊያሳርፍ እንደሚችል ይገመታል፡፡ ባለፉት ስድስት ወራት ከዚህ ዘርፍ የተገኘው የውጭ ምንዛሪ ከ110 ሚሊዮን ዶላር ሲሆን፣ ይህም በግማሽ ዓመት ውስጥ ሊያስገኝ ይችላል ተብሎ ከተቀመጠው ከሁለት እጥፍ ያነሰ ነው፡፡ በበጀት ዓመቱ አጋማሽ ከቅባት እህሎች ይገኛል ተብሎ የታቀደው ከ450 ሚሊዮን ዶላር በላይ ነበር፡፡ በበጀት ዓመቱ በጠቅላላው 904.5 ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት መታቀዱ አይዘነጋም፡፡ የቅባት እህል የወጪ ንግድ በ2006 ዓ.ም. 651.9 ሚሊዮን ዶላር አስመዝግቦ ነበር፡፡ በ2007 ዓ.ም. 510.1 ሚሊዮን ዶላር ሲያስገኝ፣ በ2008 ዓ.ም. ደግሞ 447 ሚሊዮን ዶላር አስገኝቶ ነበር፡፡ ይህም ባለፉት አምስት ዓመታት ገቢው እየቀነሰ መምጣቱን የሚያሳይ ነው፡፡

የአሪቱን የ2009 ዓ.ም. የአምስት ወራት የወጪ ንግድ እንቅስቀሴ የሚያሳዩ መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ ባለፉት አምስት ወራት ውስጥ ከጫት 120 ሚሊዮን ዶላር ገቢ እንደተገኘ ነው፡፡ ይህም በግማሽ በጀት ዓመቱ ይገኛል ተብሎ በዕቅድ ከተያዘው ገቢ ጋር ተቀራራቢ ሆኗል፡፡ በ2008 በጀት ዓመት ከጫት ንግድ 220 ሚሊዮን ዶላር የተገኘ ሲሆን፣ ይህም ከቡና፣ ከጥራጥሬና ከቅባት እህሎች ቀጥሎ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ የተገኘበት እንዲሆን አስችሎታል፡፡ በ2009 መጨረሻ ላይ ደግሞ 324 ሚሊዮን ዶላር ያስገኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የወጪ ንግዱ ዘርፍ በ2006 ዓ.ም. 3.3 ቢሊዮን ዶላር፣ በ2007 ዓ.ም. 3.01 ቢሊዮን ዶላር ቢያስገኝም፣ በ2008 ግን ይብሱን 2.8 ቢሊዮን ዶላር በማስገኘት ከማደግ ይልቅ እያሽቆለቆለ መምጣቱ ታይቷል፡፡ ባለፉት አምስት ወራት የታየው ገቢም ቢሆን የወጪ ንግዱ በታሰበለት ደረጃ ያለመራመዱን የሚጠቁም ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በሰጡት መግለጫ፣ የዓለም የሸቀጥ ገበያ መዋዠቅ ያስከተለው ቅናሽ እንጂ የምርት መቀነስ በአገሪቱ እንዳልተከሰተ ተናግረዋል፡፡ 

Standard (Image)

የገልፍ አገሮችን ተቀማጭ እንዲያማትር መንግሥትን ያስገደደው የውጭ ምንዛሪ ዕጥረት

$
0
0

የኢኮኖሚ ዘርፉን በተመለለከተ በተለይ አገሪቱ የገጠማትን የውጭ ምንዛሪ ዕጥረትን የተመለከተው ጥያቄ ብዙ ሲያነጋግር ቆይቷል፡፡ ለበርታ ተከታታይ ዓመታት በአገሪቱ የውጭ ምንዛሪ ዕጥረት መታየቱ ሲነገር ቢቆይም፣ መንግሥት ሲያጣጥለው ቆይቷል፡፡ ጥር 1 ቀን 2009 ዓ.ም. በጽሕፈት ቤታቻው መግለጫ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ከብዙ ማቅማማት በኋላ ግን የውጭ ምንዛሪ ዕጥረት መኖሩን ያመኑት በገርማሜው ነበር፡፡ በተደጋጋሚ የውጭ ምንዛሪ ዕጥረት የለም፣ ችግር አልገጠመንም ሲሉ መቆየታቸው አይዘነጋም፡፡

ለምንዛሪ ዕጥረቱ ችግሮች ተብለው የሚጠቀሱ በርካታ ነጥቦች ሲኖሩ፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የአገሪቱ የወጪ ንግድ ገቢ በከፍተኛ መጠን እያሽቆለቆለ መምጣቱ አንዱ ምክንያት ነው፡፡ ባለፈው ዓመት ከወጪ ንግዱ የተገኘው ገቢ ከሦስት ቢሊዮን ዶላር ያነሰ መሆኑ ይታወሳል፡፡ ለዚህ ደካማ አፈጻጸም ድርቁ አስተዋጽኦ እንደነበረው ሲነገር ቢቆይም፣ መንግሥት እምብዛም እንዳልጎዳው ሲከራከር ቆይቷል፡፡ ዘንድሮ በተከሰተው የፖለቲካ ቀውስና በዓለም ገበያ ከሚታየው የሸቀጦች ዋጋ መቀዛቀዝ አኳያ፣ የወጪ ንግዱ ዘንድሮም መዋዠቅ ውስጥ እንደሚገባ ይገመታል፡፡

ለገቢው ማሽቆልቆል ምክንያት እየተደረጉ ከሚገኙ አንኳር ችግሮች መካከል የመገበያያ ገንዘብ የሆነው የብር የመግዛት አቅም ከኢኮኖሚው አቅም ጋር ያልተናበበና ከአቅም በላይ ዋጋ እንዲኖረው መደረጉ አንዱ ነው፡፡ ስለዚህም የምንዛሪ ለውጥ በማድረግ፣ የብር የመግዛት አቅም እንዲቀንስ ማድረግ ይገባል የሚለው ጥያቄ ይጎላል፡፡

ስለዚህ ጉዳይ ከሪፖርተር ጥያቄ የቀረበላቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚከተለውን ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ‹‹የውጭ ምንዛሪ ዕጥረት በእኛ የዕድገት ደረጃ ላይ የነበሩ አገሮች ሁሉ ያጋጥማቸው የነበረ ችግር ነው፡፡ ዛሬ በኢኮኖሚያቸው ውስጥ ትርፍ መጠባበቂያ (ሰርፕለስ) ያላቸው እነ ኮሪያ፣ እነ ጃፓን ሁሉ በእኛ ደረጃ በነበሩበት ወቅት የውጭ ምንዛሪ ዕጥረት ክፉኛ ተፈታትኗቸዋል፡፡ ሌላው ቀርቶ የሴቶቻቸውን ፀጉር ሳይቀር ቆርጠው ኤክስፖርት እስከማድረግ ተገደው ነበር፡፡  ችግሩ ተስፋ የሚያስቆርጥ አይደለም፡፡ በዚያ መነጽር ካላየነውና ለኢትዮጵያ ብቻ የመጣ ጣጣ ካደረግነው ትክክል አይመጣም፤›› ብለዋል፡፡

ይሁንና የኤክስፖርት ዘርፉ ከዓምናው አኳያ ተመሳሳይ አፈጻጸም እንዳለው ገልጸዋል፡፡ የውጭ ምንዛሪ ግኝት በፖለቲካ ቀውስ ምክንያት ሳይሆን በመዋቅራዊ የኢኮኖሚ ሁኔታና በሚዋዥቀው የግብርና ዘርፍ ምክንያት ችግር እንደሚታይበት ተናግረዋል፡፡ ከግብርና ይልቅ የኢንዱስትሪ ምርቶችን ለውጭ ገበያ የማቅረብ ዓላማ በመያዝ መንግሥት እየሠራ እንደሚገኝ፣ ለዚህም መንግሥታቸው የኢንዱስትሪ ፓርኮችን የመሳሰሉ ግንባታዎችን በማካሄድ ዘርፉን እየደገፈ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡ የግብርና ምርቶች እየጨመሩ እንደሚገኙና በ20 በመቶ ጭማሪ መታየቱን ይልቁንም ግን ዓለም አቀፍ ገበያው በመዋዠቁ ምክንያት የወጪ ንግድ ገቢ መቀነሱን ጠቅሰዋል፡፡

ላለፉት ሦስት ተከታታይ ዓመታት የአገሪቱ የግብርና ሸቀጦች የወጪ ንግድ መጠን መጨመሩን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ይሁንና ግን የዓለም ገበያ ከፍና ዝቅ ማለቱ የአገሪቱን የውጭ ምንዛሪ ገቢ እየጎዳው እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ ‹‹አንዳንዴ ያልታሰበ ገቢ ታገኛለህ፡፡ አንዳንዴ ሳታስበው መቀመቅ ትወርዳለህ፡፡ ስለዚህ እዚህ ቁማር ላይ ማተኮሩ ብዙ እንደማያዋጣ ነገር ግን በልዩነቱ ምክንያት የሚመጣውን ጫና ለመቀነስ መፍትሔው ወደ ውጭ የሚላከውን መጠን መጨመር ነው፡፡ በእኛ ቁጥጥር ሥር ያለው ይሄው ስለሆነ መፍትሔውም ይሄው ነው፤›› ብለዋል፡፡ እስከ 80 ከመቶ የሚሆነውን የአገሪቱን የወጪ ንግድ እንቅስቃሴ የተቆጣጠረው ይኸው የግብርና ዘርፍ በየጊዜው የሚላከው መጠን እየጨመረ ቢሆንም፣ የዓለም ገበያ ባሳየው መቀነስ ምክንያት የተፈጠረው ማሽቆልቆል ግን ‹‹ማሽቆልቆል ተብሎ አይወሰድም›› በማለት ተከራክረዋል፡፡

‹‹መነጻጸር ያለበት መጠኑ ነው፡፡ ዕድገትን የሚያሳየውም ይኸው በመሆኑ ነው ዋጋው ግን እንደገበያው ሁኔታ የሚወሰን ነው፤›› ያሉት አቶ ኃይለ ማርያም፣ ከግብርና ይልቅ በማኑፋክቸሪንግ ሸቀጦች መስፋፋት መትፍሔ መሆኑም ያብራራሉ፡፡ 12 የኢንዱስትሪ ፓርኮች እየተገነቡ እንደሚገኙ፣ ከእነዚህ መካከል አንድ ቢሊዮን ዶላር የኤክስፖርት ገቢ የሚጠበቅበት የሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ምሳሌ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡

ሌላኛው ስትራቴጂ ከኢትዮጵያ ግንኙነት ያላቸው ወዳጅ አገሮች በተለይም የባህረ ሰላጤው አገሮች ተቀማጭ ሒሳባቸውን በውጭ ምንዛሪ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲያስቀምጡ ማድረግ ሲሆን፣ ዓምና ይሄ እንደተሞከረና ዘንድሮ ተጠናቅሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡ የወጪ ንግዱ አፈጻጸምም ሆነ የውጭ ምንዛሪ ክምችት ችግር በመኖሩ ምክንያት ባንኮች በወረፋ የማዳረስ አሠራራቸው ተገቢ እንደሆነ ሞግተዋል፡፡ ‹‹ዕጥረት ካለ ወረፋ ጠብቀህ መውሰድ የማይቀር ነው፡፡ ዕጥረት ካለ ወረፋ ይኖራል፡፡ ከዚህ በፊት የግል ባንኮች ለንግድ ዘርፉ ብቻ ይሰጡ የነበረውን አሠራር ቅድሚያ ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ እንዲሰጡ የብሔራዊ ባንክ መመርያ በማውጣቱ የፖሊሲ አቅጣጫ ነው፤›› ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ከውጭ ምንዛሪ ግኝቱ ማሽቆልቆሉ ብቻም ሳይሆን የውጭ ምንዛሪ ተመን ለውጥ ይደረግ የሚለው ጥያቄም እውነታ እንዳለው አምነዋል፡፡ የተመን ማሻሻያ በማድረግ ወጪን ማዳን እንደሚቻልና የተወሰነ ገቢ ለማግኘትም እንደሚያስችል ጥሪ እየቀረበ ቢሆንም፣ ይህንን ጥሪ ግን አደጋ የሚያስከትል ሲሉ ገልጸውታል፡፡

‹‹የውጭ ምንዛሪ ተመን እንዲቀንስ የሚጠይቁ ባለሙያዎች የሚያቀርቡት ጥያቄ መሠረት አለው፡፡ ነገር ግን የምንዛሪ ተመን ለውጥ ሲደረግ የሚመጣ አደጋ አለ፡፡ እንደ ታዳጊ አገር በርካታ ኢንቨስትመንቶችን እያካሒድን ነው፡፡ የውጭ ምንዛሪ ተመን እንዲቀንስ ሲደረግ [ከውጭ የሚገባው ዕቃ] በአገር ውስጥ የሚሸጥበት ዋጋ ከፍተኛ ይሆናል፡፡ ይህ ከሆነ ከውጭ የሚገባው ዕቃ በከፍተኛ መጠን እንዲገታ ስለሚያደርግ አገራዊው ባለሀብት በከፍተኛ ደረጃ እንዲመታ ያደርጋል፤›› በማለት የማሻሻያ ጥያቄውን ከሁለት ሰይጣኖች አንዱን ለመምረጥ እንደሚያስገድድ በምሳሌ በማስገደፍ የውጭ ምንዛሪ ለውጥ ከማድረግ ከሚገኘው ጥቅም ይልቅ ጉዳቱ የሚያመዝን በመሆኑ፣ የምንዛሪ ለውጥ ማድረጉ ለጊዜው የመንግሥት ምርጫ እንደማይሆን አስታውቀዋል፡፡

እነ ባህሬን፣ ኩዌት፣ ኦማን፣ ኳታር፣ ሳዑዲ ዓረቢያና የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች የባህረ ሰላጤው አውራ አገሮች ከኢትዮጵያ ጋር የንግድና የኢንቨስትመንት ሸሪክ የመሆን ፍላጎት እንዳላቸው ሲገልጹ ቆይተዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥትም ከእነዚህ አገሮች ጋር ቀና የኢኮኖሚ ትስስር ለመመሥረት ደፋ ቀና ሲል ቆይቷል፡፡ ከአንዳንዶቹ አገሮች ጋር በፖለቲካዊ ቅራኔ ውስጥ ቢገባም ወደ ባህረ ሰላጤው አገሮች ከሚላከው ሸቀጥ ከ300 ሚሊዮን ዶላር በላይ ማግኘት ጀምሯል፡፡ ከሦስት ዓመት በፊት የነበረው የኢትዮጵያ የወጪ ንግድ ከ180 ሚሊዮን ዶላር ጥቂት ፈቅ ያለ ነበር፡፡

እነዚህ አገሮች የምግብ ሸቀጦችን ለማሟላት እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች ላይ ዓይናቸውን መጣላቸው ዕሙን ነው፡፡ የምግብ ሸቀጥ ብቻም ሳይሆን የመጠጥ ውኃ አቅርቦት ለማግኘት የሚያስችላቸውን ስምምንት እስከማድረግ መድረሳቸው የቅርብ ጊዜ ክስተት ነው፡፡ ከእነዚህ አገሮች መካከል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወዳጆቻችን ካሏቸው ጋር ባለው የንግድና የኢንቨስትመንት ግንኙነት ባሻገር አገሮቹ ገንዘባቸውን በኢትዮጵያ እንዲያስቀምጡ ጥያቄ ቢያቀርቡም፣ አገሮቹ ለኢንቨስትመንት የሚመች ከባቢ ሁኔታዎች ፍጠሩ ማለታቸውና የኢስላሚክ ባንክ አግልግሎት ፍቀዱልን የሚለው ጥያቄያቸው የሚያገኘው ምላሽ ቀርፋፋ መሆኑ እየታየ ነው፡፡

መንግሥት ከወጪ ንግድ ባሻገር የገልፍ አገሮችን፣ የውጭ ሐዋላንና የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉን ገቢዎች እያማተረ ይገኛል፡፡ በየዓመቱ በ30 ከመቶ ጭማሪ እያሳየ እንደሚገኝ የተጠቀሰለት የውጭ የሐዋላ ገቢ ትልቅ ሚና እንዳለው የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ጥቂት በጥቂቱ ማሻሻያ የሚደረግበት የውጭ ምንዛሪ ተመን ለውጥ እንደሚኖር ሳይገልጹ አላለፉም፡፡

Standard (Image)

በንግድ ሚኒስቴር የ‹‹ጥልቅ ተሃድሶ›› ስብሰባ ምክንያት ሥራ ለሳምንት በመቋረጡ ተገልጋዮች እያማረሩ ነው

$
0
0

 

- የንግድ ፈቃድ ዕድሳትና ሌሎች አገልግሎቶች ተቋርጠዋል

ንግድ ሚኒስቴር ድንገት በጠራውና ለሳምንት በሚቆየው ‹‹የጥልቅ ተሃድሶ›› ስብሰባ ምክንያት ተገልጋዮች አማረሩ፡፡ በርካታ አገልግሎት ፈላጊ ባለጉዳዮች በስብሰባ ምክንያት አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ በመቋረጡ ሳቢያ ከጥበቃ ሠራተኞችና ከበታች ኃላፊዎች ጋር አተካራ ሲገጥሙና ችግሮቻቸውን ሲያሰሙ ታይተዋል፡፡

‹‹ለክቡራን ደንበኞቻችን ከዛሬ ማክሰኞ ጥር 2 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ሰኞ ጥር 7 ቀን 2009 ዓ.ም. በጥልቅ ተሃድሶ ውይይት ምክንያት በንግድ ሚኒስቴር ስብሰባ የምናደርግ ስለሆነ ማንኛውንም አገልግሎት የማንሰጥ መሆኑን እንገልጻለን!!›› ተብሎ የተጻፈውና በንግድ ምዝገባና ፈቃድ ቅርንጫፍ ቁጥር 1 ጽሕፈት ቤት ተጠባባቂ ኃላፊ ፊርማ ወጥቶ የተለጠፈው ማስታወቂያ፣ ምንም ዓይነት አገልግሎት አንሰጥም ማለቱ በርካቶች የሚኒስቴሩን አገልግሎት ፈላጊዎች አስቆጥቷል፡፡ አገልግሎት ፈልገው ወደ ሚኒስቴሩ የሄዱ ተገልጋዮችና ጥቂት ሠራተኞች ሲነታረኩም ታይተዋል፡፡

ይህ ማስታወቂያ ተግባራዊ መሆን በጀመረበት ዕለት በርካታ ባለጉዳዮች፣ ሒልተን ሆቴል ጀርባ፣ ካዛንቺስ ሱፐርማርኬት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ወደሚገኘው የንግድ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት አቅንተዋል፡፡ ሆኖም ግን ምንም ዓይነት አገልግሎት አታገኙም በመባላቸው ከጥበቃ ሠራተኞችና ከበታች ኃላፊዎች ጋር ክርክር ሲገጥሙ ሪፖርተር ታዝቧል፡፡ ባለጉዳዮቹ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ ማስረጃዎችን፣ የክሊራንስ ማረጋገጫ ሰነዶችንና ሌሎችም አገልግሎቶችን ለማግኘት እንዳልቻሉ፣ በዚህም ሳቢያ በየቀኑ ለቅጣት እየተደረጉ እንደሚገኙ ከወዲሁ ቢገልጹም አጥጋሚ ምላሽ ማግኘት ሳይችሉ ለመመለስ ሲገደዱ ታይተዋል፡፡

ቅሬታ ሲያቀርቡ ከተደመጡ ባጉዳዮች መካከል አራት ሚሊዮን ብር የሚያወጡና በቻርተር አውሮፕላን እንዲጫኑ የታዘዙ ምርቶችን ወደ ውጭ ለመላክ የተዘጋጁ ባለሀብት አንዱ ነበሩ፡፡ ሚኒስቴሩ ለሚላከው ምርት የንግድ ፈቃድ ማረጋገጫ መስጠት ይጠበቅ በነበረበት ወቅት ስብሰባ ተብሎ አገልግሎት በመቋረጡ፣ ኪሳራቸውን ማን እንደሚሸፍንና ኃላፊነቱን ማን እንደሚወስድ ባለሀብቱ ሲጠይቁ ተደምጠዋል፡፡

አገልግሎት በሚሰጥበት የሥራ ሰዓትን በመሻማት ሚኒስቴሩ ስብሰባ ጠቅልሎ መግባቱ ሕዝብን ለማገለግል የተሰጠውን ኃላፊነት ወደ ጎን መተው ነው የሚሉ ትችቶችን ያሰሙ ተገልጋዮች፣ የሕዝብ ተቋማት እንታደሳለን በማለት የስብሰባ ክተት ማወጃቸውን እንደማይቀበሉት ሲገልጹ ተደምጠዋል፡፡ አንዳንዶቹም እንዲህ ያሉ ሥራን በመዝጋት ስብሰባ የሚጠራባቸው ሁኔታዎች ከሕግ አኳያ መጠየቅ እንደሚያስልጋቸውም ሲሞግቱ ተደምጠዋል፡፡

ለሚኒስቴሩ አዲስ የተሾሙት ዶ/ር በቀለ ቡላዶን ጨምሮ ሚኒስትር ዴኤታዎችና የበታች ሹማንምንትን ጨምሮ ተራ ሠራተኞች ሳይቀሩ ክተት በጠሩበት ‹‹የጥልቅ ተሃድሶ›› ስብሰባ ወቅት፣ በርካታ ባለጉዳዮች የሚያስተናግዳቸው አጥተው ላይ ታች ሲሉ ተስተውሏል፡፡ አልፎ አልፎም የሚኒስቴሩ ሠራተኞች ከስብሰባው እየወጡ አጣዳፊና አስቸኳይ ለሆኑ ጉዳዮች ብቻ መፍትሔ እየሰጡ ወደ ስብሰባው ተመልሰው ይገባሉ፡፡ ይሁንና ይህም ቢሆንም ስብሰባው ከመጀመሩ በፊት ባሉት ደቂቃዎችና በምሳ ሰዓት ወቅት ባለው የዕረፍት ጊዜ ላይ መሆኑም፣ ስብሰባው ምን ዓይነት ተዓምር እንደሚያመጣ ከወዲሁ በጉጉት እንዲጠበቅ አድርጎታል፡፡

ተገልጋዮች ግን ለሕዝብ አገልግሎት ከመስጠት ይልቅ በስብሰባ ምክንያት ሙሉ በሙሉ በር ዘግቶ በመሰንበት ለውጥ መምጣት ስለመቻሉ እምነት እንደሌላቸው ገልጸዋል፡፡ ተገልጋዮቹም ማግኘት ባልቻሉት አገልግሎት ምክንያት እየደረሰባቸው ያለውን መጉላላት ሲያሰሙ ቢታዩም፣ ከሚኒስቴሩ ይህ ነው የሚባል ምላሽ ማግኘት እንዳልቻሉ ሲገልጹ ታይተዋል፡፡

 ስለዚህ ጉዳይ ሪፖርተር የሚኒስቴሩን ኃላፊዎች ለማነጋገር ያደረገው ሙከራ አልተሳካም፡፡ ከአዲሱ የሚኒስቴሩ ኃላፊዎች ምደባ ቀደም ብሎ በተደረገ ሽግሽግ ምክንያት ከሚኒስቴሩ የተነሱ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊዎችን የተኩ ሰዎችን ማግኘትና መረጃ እንዲሰጡ ማድረግ ያልተቻለ ሲሆን፣ ስለተሃድሶው ስብሰባና ስለሚኖረው ውጤት፣ ስለሚያስከትለው ለውጥ መረጃ የሚሰጥ አካል ማግኘት አልተቻለም፡፡

በአገሪቱ የተነሳው ሕዝባዊ ተቃውሞ መንግሥት ጥልቅ ተሃድሶ ብሎ እንዲነሳና በየመሥሪያ ቤቶቹም ስብሰባ እንዲያካሂድ አስገድዶታል፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የሚመራው የኢሕአዴግ መንግሥት የ2007 አገር አቀፍ ምርጫን መቶ በመቶ ባሸነፈ በሁተኛው ዓመቱ ሹም ሽር በማካሄድ ለሁለተኛ ጊዜ አዲስ ካቢኔ እንዲያዋቅር የተገደደበት ፖለቲካዊ ውጥረት በአሁኑ ወቅት እየረገበ መጥቷል፡፡ ይሁንና በሕዝቡ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት በማለት የሚካሄዱ ስብሰባዎች ግን እንደ ንግድ ሚኒስቴሩ ያሉት አካሄዶች ከወዲሁ አገልግሎት እያቋረጡ መካሄዳቸው ቅሬታ ማስነሳታቸው አልቀረም፡፡ ይህም ቢባል ግን ሚኒስቴሩ ያቋረጣቸውን አገልግሎቶች እንደሚካክስ ይጠበቃል፡፡ 

Standard (Image)

ስምንቱ የ6.5 ቢሊዮን ብር መንገዶች

$
0
0

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ለበጀት ዓመቱ ሁለተኛ የሆነውን የስምንት የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶችን ኮንትራት ስምምነት ተፈራረመ፡፡ ጥር 4 ቀን 2009 ዓ.ም. ስምምነት የተደረገባቸው ስምንቱ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች ከ6.5 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚጠይቁ ሲሆኑ፣ 374 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ አላቸው፡፡

የግንባታ ወጪያቸው ሙሉ በሙሉ በመንግሥት የሚሸፈኑትን የእነዚህን ስምንት ፕሮጀክቶች ግንባታ ለማካሄድ በጨረታ አሸንፈው የኮንትራት ስምምነቱን የፈረሙት ሁለት የቻይና እና አራት አገር በቀል ተቋራጮች ናቸው፡፡

በአገሪቱ መንገድ ግንባታ ሒደት ለሦስተኛ ጊዜ በሲሚንቶ ኮንክሪት ጭምር የሚገነቡ ፕሮጀክቶችን ያካተተው ይህ የመንገድ ፕሮጀክት ስምምነት፣ በመንገድ ግንባታ ለመጀመሪያ ጊዜ ተሳታፊ የሆኑ ተቋራጮችንም አስተናግዷል፡፡

ሐሙስ ጥር 4 ቀን የግንባታ ስምምነቶቹ በተፈረሙበት ወቅት እንደተገለጸው፣ በመንገድ ግንባታ ሥራ ከባለሥልጣኑ ጋር ውለታ ሲገቡ የመጀመሪያቸው ነው ከተባሉት ሁለት ተቋራጮች አንደኛው ዮቴክ ኮንስትራክሽን የተባለው አገር በቀል ተቋራጭ ነው፡፡ ዮቴክ ኮንስትራክሽን በዕለቱ ከተፈረሙት ስምንት ፕሮጀክቶች ውስጥ የሁለቱን ሥራ በጨረታ አሸንፎ በመውሰድ ወደ መንገድ ግንባታው ዘርፍ ለመቀላቀል በቅቷል፡፡

በኮንስትራክሽን ኢዱንስትሪው መስክ ከአሥር ዓመት በላይ ዕድሜ ያለው ዮቴክ ኮንስትራክሽን፣ የእስካሁኑ ታሪኩ እንደሚያሳየው በሕንፃና በሪል ስቴት ግንባታ ውስጥ ሲሳተፍ መቆየቱን ነው፡፡ ኩባንያው በዚህ ዓመት የመንገድ ግንባታ ሥራ ውስጥ ገብቷል፡፡ የኮንትራት ስምምነቱን በተፈራረመት ወቅት እንደተገለጸው፣ ዮቴክ አሸናፊ ሆኖ ከተረከባቸው ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ ከባሌ - ፊቅ ኮንትራት ሁለት የተባለው መንገድ ፕሮጀክት ነው፡፡ 30 ኪሎ ሜትር የሚረዝመውን ይህንን ፕሮጀክት ለመገንባት ዮቴክ በጨረታ ያሸነፈበት የግንባታ ዋጋ 451.2 ሚሊዮን ብር ነው፡፡ ዮቴክ አሸናፊ የሆነበት ሁለተኛው ፕሮጀክት ደግሞ ከባቢሌ - ፊቅ ኮንትራት ሦስት የተባለው የመንገድ ፕሮጀክት ነው፡፡ 27 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነውን ይህንን መንገድ ለመገንባት 400.9 ሚሊዮን ብር ዋጋ በመስጠትና የኮንትራት ውሉን ፈርሟል፡፡ በአጠቃላይ 852 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸውን ሁለት የመንገድ ሥራዎች በመጀመሪያው ተሳትፎ አግኝቷል፡፡

ከባለሥልጣኑ ለመጀመሪያ ጊዜ የመንገድ ሥራ የተረከበው ሌላኛው ተቋራጭ የቻይና ኩባንያ ነው፡፡ ቻይና ዉይ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የተባለው  ይህ ተቋራጭ፣ በጨረታ አሸንፎ የተረከበው የመንገድ ፕሮጀክት በአፋር ክልል የሚገኘውና የአፍዴራ-አረብቲ 48 ኪሎ ሜትር እየተባለ የሚጠራውን ፕሮጀክት ነው፡፡ ይህ ፕሮጀክት 79 ኪሎ ሜትር ይሸፍናል፡፡ ለዚህ ፕሮጀክት ሥራ ቻይና ዉይ አሸናፊ የሆነበት ዋጋ 1.36 ቢሊዮን ብር ነው፡፡

በዕለቱ ከተፈረሙት ስምምነቶች ውስጥ ከፍተኛ ዋጋ የተሰጠበትን የመንገድ ግንባታ ሥራ የተረከበው መከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ነው፡፡ ቻይና ዉይ ከሚገነባው መንገድ ጋር ተያያዥ የሆነውንና 48 ኤርታሌ መገንጠያ አህመድ ኤላ (ኮንትራት ሁለት) የተባለው ፕሮጀክት 54.8 ኪሎ ሜትር ይሸፍናል፡፡ የዚህን መንገድ የመንገድ ግንባታ ለማካሄድ መከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ጨረታ አሸናፊ የሆነበት ዋጋ 1.7 ቢሊዮን ብር ነው፡፡

ይህ ፕሮጀክት በኢትዮጵያ በሲሚንቶ ኮንክሪት የሚገነባ ሦስተኛው መንገድ ይሆናል፡፡ ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ሁኔታ የተገነባውን መንገድ ልምድ በመቀመር ዲዛይኑ በደንብ ተጠንቶ የተሠራ በመሆኑ ፕሮጀክቱ በተሳካ መንገድ ይጠናቀቃል የሚል እምነት እንዳላቸው የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ አርዓያ ግርማይ ገልጸዋል፡፡ የዚህ መንገድ የግንባታ ዘይቤ የመጀመሪያ የግንባታ ወጪው ከአስፋልት ኮንክሪት አንፃር ከፍ ያለ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡ ነገር ግን ለጥገና የሚያስወጣው ወጪ ዝቅተኛነትና የ40 ዓመት የአገልግሎት ዘመን ያለው መሆኑ እንዲሁም አስተማማኝ የመንገድ መሠረተ ልማት ከማቅረብ አንፃር ወሳኝ ሚና እንደሚኖረው ታምኖበታል፡፡ ይህ የመንገድ ንጣፍ ዓይነት ለየፕሮጀክቱ ያለው ተስማሚነት እየታየ ወደፊት የሚተገበር እንደሆነም በሲሚንቶ ኮንክሪት ስለሚሠራው መንገድ አቶ አርዓያ በሰጡት ማብራሪያ ገልጸዋል፡፡

ለመንገዱ ግንባታ ከአንድ ሚሊዮን ኩንታል በላይ ሲሚንቶ የሚያስፈልግ ሲሆን፣ ይህም ለአገሪቱ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ሰፊ የገበያ ዕድል ያስገኛል፡፡ በሌላ በኩል መንገዱ በሲሚንቶ ኮንክሪት በመሠራቱ ምክንያት ከ30 ሺሕ ቶን በላይ ለግንባታው ያስፈልግ የነበረውን አስፓልት በማስቀረት የውጭ ምንዛሪን ማዳን ያስችላል ተብሏል፡፡

 በአፋር ክልል የሚነገቡት መንገዶች የፖታሽ ማዕድን አውጪ ኩባንያዎች ምርቶቻቸውን በከፍተኛ የጭነት ተሽከርካሪዎች ለማመላስ ከኢትዮ-ጂቡቲ ድንበር የፖታሽ ምርቱ እስከሚወጣበት ቦታ ድረስ 439 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ የሚሸፍኑ ናቸው፡፡ ከተጠቀሰው የመንገድ ክፍል ውስጥ በአጠቃላይ 121 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያላቸው የዲቺቶ-ጋላፊ መገንጠያ - አሊዳር በለሆና የሙስሊ ባዳ የአዳዲስ መንገዶች ግንባታ በ3.9 ቢሊዮን ብር በመከናወን ላይ እንደሚገኙ አቶ አርዓያ አስታውሰዋል፡፡

የአፍዴራ አህመድ ኤላ የመንገድ ሥራ ፕሮጀክት በሁለት ኮንትራት ተከፋፍሎ የሚሠራ ሲሆን፣ በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ የሚገኙት የበርሃሌና የአፍዴራ ወረዳዎችን ያገናኛል፡፡

መንገዱ በዋናነት በዳሎል ስምጥ ሸለቆ ውስጥ የሚገኙትን የፖታሺየም አለታማ ጨውና የማግኒዝየም ማዕድናት ለማጓጓዝ ከፍተኛ ጥቅም እንዳለው የገለጹት አቶ አርዓያ፣ ከዋናው መንገድ በተጨማሪም ኤርታሌን ጨምሮ ወደ ሦስት መዳረሻዎች የሚያመሩና 32 ኪሎ ሜትር የሚረዝሙ ተገንጣይ መንገዶች ያሉት ነው፡፡ ይኽም ከፍተኛ የቱሪስት መስህብ የሆነውን ኤርታሌን ለመጎብኘት የሚመጡ ቱሪስቶች ምቾት ተጠብቆ እንዲጓዙ ይረዳል፡፡

መንገዱ ከአዲስ አበባ በስተሰሜን ምሥራቅ 840 ኪሎ ሜትር ላይ ከምትገኘው የአፍዴራ ኢረብቲ አብአላ መንገድ ላይ የሚጀምር ሲሆን፣ 48 ኪሎ ሜትር ከተዘረጋ በኋላ ያበቃል፡፡ የመንገድ ፕሮጀክቱ ከዋናው መንገድ በኩስሩዋድና አይቱራ ቀበሌዎች በኩል ወደ ኤርታሌ እሳተ ገሞራ መዳረሻ የሚወስደውን መንገድ ግንባታ እንደሚያካትትም ታውቋል፡፡

በዕለቱ የኮንትራት ውል የተፈረመበት ሌላው የመንገድ ፕሮጀክት በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የአሶሳ-ዳለቲ ወረዳ ኮንትራት ሁለት የአስፋልት መንገድ ፕሮጀክት ነው፡፡ 69 ኪሎ ሜትር የሚረዝመውን የዚህ መንገድ ግንባታ ለማካሄድ ጨረታውን አሸንፎ ከባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ጋር የውል ስምምነት የተፈራረመው እንይ ኮንስትራክሽን የተባለ አገር በቀል ኮንትራክተር ነው፡፡ እንይ ለመንገዱ ግንባታ አሸናፊ የሆነበት ዋጋ 731.5 ሚሊዮን ብር እንደሆነ ተገልጿል፡፡ እንይ ይህ ፕሮጀክት ሦስተኛው ነው፡፡

እንይ የሚገነባው መንገድ ሰባት ኪሎ ሜትር ስፋት የሚኖረው ሲሆን፣ እያንዳንዳቸው በግራና በቀኝ 1.5 ሜትር ስፋት ያላቸው የመንገድ ትከሻ ሲኖረው ተቋራጩ መንገዱን ገንብቶ ለማጠናቀቅ የሦስት ዓመት የግንባታ ጊዜ እንደተሰጠው ታውቋል፡፡

75.6 ኪሎ ሜትር የሚረዝመውንና በኦሮሚያ ክልል የሚገኘውን የኢተያ - ሮቤ - ሌሩ ኮንትራት አንድ የመንገድ ፕሮጀክትን ለመገንባት አሸናፊ ሆኖ በዕለቱ የውል ስምነት የተፈራረመው የቻይናው ሬልዌይ ቁጥር ሦስት ኮንስትራክሽን ነው፡፡

ኮንትራክተሩ ይህንን መንገድ ለመገንባት የሰጠው ዋጋ 1.32 ቢሊዮን ብር ነው፡፡ ይህ መንገድ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት በሚጀምርበት ወቅት በክልሉ ውስጥ የሚገኙ ዞኖችንና ወረዳዎችን ያስተሳስራል፡፡ ከዚህም ባሻገር የተሽከሪካዎችን የጉዞና የጊዜ ወጪን በከፍተኛ ደረጃ የሚቀነስ ከመሆኑም በተጨማሪ የምርትና የሸቀጥ ልውውጥ ያለምንም እንግልት እንዲከናወን ለማድረግ ያስችላል ተብሎ ታምኖበታል፡፡

ከስምንቱ ፕሮጀክቶች ቀሪዎቹን ሁለቱን ለመገንባት ውለታ የፈረመው ሌላኛው አገር በቀል ኮንትራክተር ፉል ጄኔራል ኮንትራክተር ነው፡፡

ፉል በጨረታ አሸናፊ ሆኖ የተረከባቸው መንገዶች ከባቢሌ - ፊቅ ኮንትራት አንድ የተባለውን 36 ኪሎ ሜትር የመንገድ ፕሮጀክትና 3.81 ርዝማኔ ያለውን የሒዳ - ያሎን የመንገድ ፕሮጀክት ነው፡፡

ፉል የባቢሌ - ፊቅ ኮንትራት አንድ ፕሮጀክትን ለመሥራት አሸናፊ የሆነበት ዋጋ 408.4 ሚሊዮን ብር ነው፡፡ የሒድ - ያሎን መንገድም በ105.5 ሚሊዮን ብር ለመሥራት ተሰማምቷል፡፡ የስምንቱም ፕሮጀክቶች ባለሥልጣን ወክለው አቶ አርዓያ ግርማይ ሲፈርሙ፣ በኮንትራክተሮቹ በኩል ሥራ አስኪያጁ ፈርመዋል፡፡

Standard (Image)

በቡና ዘርፍ የታዩ ድክመቶችና አዳዲስ መትሔዎች

$
0
0

የአገሪቱ ቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ምርት ግብይትን ለማሳደግና ለማዘመን ኃላፊነት ከተሰጣቸው መንግሥታዊ ተቋማት መካከል የቡና እና ሻይ ልማትና ግብይት ባለሥልጣን አንዱ ነው፡፡ በቡና፣ በሻይና በቅመማ ቅመም ምርት ረገድ ዘንድሮ ከፍተኛ የገበያ  ዕድገት እንዳለ ማረጋገጥ መቻሉን ባለሥልጣኑ ይገልጻል፡፡

የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳኒ ረዲ አህመድ እንደገለጹት፣ በድኅረ ምርት አሰባሰብ ወቅት አሁን ያለው መረጃ በትክክል የሚታወቅ ቢሆንም፣ በቅድመ ምርት አሰባሰብ ትንተና መሠረት፣ 26 በመቶ የቡና ምርት ዕድገት መገኘቱ እንደተረጋገጠ አስታውቀዋል፡፡ በዚህም መሠረት 702 ሺሕ ቶን ቡና እንደተመረተ የሚያሳይ ነው፡፡ ይህ መጠን በድኅረ ምርት መረጃ አሰባሰብ ሒደት ወቅት የሚጣራና ከማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ በሚያወጣው መረጃ ተደግፎ የተባለው ዕድገት መገኘቱ የሚጣራ ቢሆንም፣ አሁን ያለው መረጃ የቡና ምርት መጠን ማደጉን ያሳያል ብለዋል፡፡

በኤክስፖርት ረገድም ወደ ውጭ የሚላከውን ምርት መጠን በ30 በመቶ ለማሳደግ መታቀዱን አስታውሰዋል፡፡ ባለፉት አምስት ወራት ውስጥ በቡና፣ በሻይና በቅመማ ቅመም 93,423 ቶን ለመላክ ታቅዶ 77,822 ቶን መላክ እንደተቻለ የባለሥልጣኑ መረጃ ያሳያል፡፡ ከዕቅዱ 83 በመቶውን ማሳካት እንደተቻለ ዳይሬክተሩ ይናገራሉ፡፡

በባለሥልጣኑ ዕቅድ መሠረት፣ በአምስት ወራት ከተላከው ቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ውስጥ ይገኛል ተብሎ የታቀደው ገቢ 350 ሚሊዮን ዶላር ነበር፡፡ ሆኖም 279 ሚሊዮን ዶላር እንደተገኘ አቶ ሳኒ ገልጸዋል፡፡ ይህም የዕቅዱን 80 በመቶ በመሳካት ነው፡፡ በሌላ በኩል በአምስት ወራት ውስጥ ለውጭ ገበያ ይቀርባል ተብሎ የታቀደው የቡና መጠን 88,551 ቶን ቡና ሲሆን፣ መላክ የተቻለው ግን 74,774 ቶን በመሆኑ ከዕቅዱ 86 በመቶ የተፈጸመበት ነው፡፡ የአምስቱ ወራት አፈጻጸም በግርድፉ ሲታይ ባለፈው ዓመት በተመሳሳይ ወቅት ከተላከው አኳያ የ3.8 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል፡፡

በተናጠል የቡና የወጪ ንግድ አፈጻጸም በአምስቱ ወራት ውስጥ ይገኛል ተብሎ የታቀደው 338 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ነበር፡፡ የተገኘው ግን 273 ሚሊዮን ዶላር ነበር፡፡ በአፈጻጸሙም ከ2008 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አኳያ ሲታይ  መጠነኛ ቅናሽ አሳይቷል፡፡

የቡና ኤክስፖርት አፈጻጸም ከቀዳሚው ዓመትም ሆነ ከዘንድሮ ዕቅድ ያነሰበትን ምክንያት ያብራሩት ዳይሬክተሩ፣ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በተደረገ ፍተሻ አራት መሠረታዊ ችግሮች ተለይተዋል ብለዋል፡፡

ለኤክስፖርት አፈጻጸም ዝቅተኛ መሆን ዋነኛ ምክንያት ተደርጎ የተቀመጠው የዓለም ገበያ ዋጋና የአገር ውስጥ ገበያ ዋጋ የሚናበብ አለመሆኑ ነው፡፡ ይህም በኤክስፖርተሮች መካከል ተገቢ ያልሆነ ውድድር መኖሩን ለማየት ያስችላል ያሉት አቶ ሳኒ፣ ሁለተኛው ምክንያት ያሉት ደግሞ ዓምና በተፈጠረው የኤልኒኖ ክስተት ምክንያት የቡና ምርት ዕጥረት መከሰቱን አስረድተዋል፡፡

የአየር ፀባይ ለውጡ በቡና ምርት ላይ ካስከተለው ችግር በተጨማሪ፣ በርካታ ገዥ ኩባንያዎች የሚላክላቸውን የቡና ናሙና በማዘግየትና አዲሱን ምርት በመጠባበቅ ኮንትራት የማዘግየት ችግር መከሰቱ በአፈጻጸሙ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳድሯል ብለዋል፡፡ ላኪዎች የገቡትን ኮንትራት ለማሟላት ያለመንቀሳቀሳቸውም ለቡና የወጪ ንግድ አፈጻጸም ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳርፏል ብለዋል፡፡

ባለሥልጣኑ በ2009 ዓ.ም. 241 ሺሕ ቶን ቡና ኤክስፖርት ለማድረግ ማቀዱን የገለጹት አቶ ሳኒ፣ ከዚህ ምርት 940 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት መታሰቡን ገልጸዋል፡፡

የኤክስፖት ምርት የአገር ውስጥ የቡና አቅርቦት ምጣኔው ሲታይ፣ ከ40 እስከ 45 በመቶ ኤክስፖርት ሲደረግ፣ ከ55 እስከ 60 በመቶው ለአገር ውስጥ ፍጆታ የሚውል ነው፡፡ ከዚህ አንፃር በአቅርቦት ደረጃ በቂ ምርት መኖሩን እንደሚያመላክትና፣ ይህንን ቡና በተቻለ መጠን ጥራቱን ጠብቆ በወቅቱ ኤክስፖርት ማድረግ ይገባል በማለት የአምስት ወር አፈጻጸሙ ተገምግሞ ለመጪዎቹ ወራት የተሻለ እንዲሆን እየተሠራ ነው ተብሏል፡፡

የቡና መጫረቻ ዋጋ ገደብ

እንደ ዳይሬክትሩ ማብራሪያ የታዩትን ማነቆዎች ለመፍታት የዓለም የቡና ዋጋና የአገር ውስጥ የቡና ገበያ ዋጋ ባለመናበቡ ምክንያት የአገር ውስጥ ዋጋ ከፍ ሲል፣ ሲያሻው ዝቅ የሚልበት ሁኔታ በመኖሩ ላኪው አስቀድሞ የሸጠውን ቡና ገዝቶ ለማሟላት እየተቸገረ ይገኛል ተብሏል፡፡ በተደረጉ ግምገማዎች ማወቅ እንደተቻለም ገልጸዋል፡፡ ስለዚህ በላኪዎችና በአቅራቢዎች ጥያቄ መሠረት በኢትዮጵያ ምርት ገበያ፣ የግብይት ሒደት ወቅት ዕለታዊ የዋጋ ገደብ እንዲኖር የሚያደርግ አሠራር ተግባራዊ ለማድረግ ስምምነት ተደርሷል ተብሏል፡፡

ይህ አሠራር ቀደም ብሎ የነበረና በላኪዎች ጥያቄ ምክንያት ቀርቶ የነበረ ሲሆን፣ ዳግመኛ እንዲመለስ በጋራ በመወሰኑ በጥቂት ቀናት ተግባራዊ ይሆናል ብለዋል፡፡

ከጥራት አኳያ በአገሪቱ የጥራት ደረጃ መሠረት፣ ማቀነባበሪያዎች በጥራት አዘጋጅተው ለላኪው የማቅረብ ችግር እንዳለባቸው ያስረዱት ዳይሬከተሩ፣ ከዚህ አኳያ እያንዳንዱ ኢንዱስትሪ የተረከበውን ቡና የአካባቢውን ብራንድና ስያሜ ጠብቆ የጥራት ደረጃ ሳያጓድል አዘጋጅቶ ለላኪው የሚያቀርብበት አሠራር ተዘርገቷል ብለዋል፡፡ ኢንዱስትሪዎቹ ከባለሥልጣኑ ጋር የውል ስምምነት እንዲገቡ መደረጉም ተናግረዋል፡፡ በዚህም መሠረት የቡና ጥራት በሚጓደልበት ጊዜ ቀርበው እንዲያስረዱ፣ የችግሩ መንስዔና መፍትሔ ምን እንደሆነና መፍትሔም ከእነሱ እንዲመነጭ የሚያደርግ አሠራር ከዚህ ቀደም ስላልነበር ችግሮች እየተበራከቱ መምጣታቸውን ገልጸዋል፡፡ ይህ አሠራር የጥራት ችግሩን ለመፍታት እንደሚያስችል ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡

የቡና አቅርቦትን ከማሻሻል አኳያ ባለሥልጣኑ የተለያዩ ዕርምጃዎችን ወስዷል ተብሏል፡፡ በተለይ የምርት ገበያው በየዕለቱ የገበያ ዋጋ ገደብ ማድረግ መጀመሩ ከዕለቱ የገበያ ዋጋ አምስት በመቶ ከፍና አምስት በመቶ ዝቅ እንዲል የሚያስችል ነው፡፡ የተለየ ክስተት ሲፈጠርም የምርት ገበያ ቦርድ እየተወያየ በመወሰን ዋጋ የሚሻሻልበትን አሠራር እንዲዘረጋ ከውሳኔ ላይ መድረሱ የመፍትሔ አቅጣጫ ተደርጓል፡፡

‹‹ይህ ውሳኔ አቅራቢዎች በምናስተላልፈው የገበያ ዋጋ መረጃ ላይ ተመሥርተው ምርታቸው በሚቀጥሉት ቀናት በምን ያህል ዋጋ እንደሚሸጥላቸው ገምተው ትርፍና ኪሳራቸውን አስልተው ምርታቸውን ወደ ምርት ገበያው ሳያቋርጡ የሚያቀርቡበትን አሠራር ያጎናጽፋቸዋል፤›› ብለዋል፡፡

የመጋዘን አገልግሎት

ከቡና ግብይት አኳያ ትችት የሚያስነሳው ሌላው ጉዳይ የመጋዘን አገልግሎት አሰጣጥ ነው፡፡ ቡና ጭነው የሚመጡ ተሽከርካሪዎች ቡና ለማራገፍ የሚወስድባቸው ጊዜ ረዥም መሆኑ ነው፡፡ ይህ የተጓተተ አሠራር ያለአግባብ ወጪ እያስወጣቸው በመሆኑ በርካታ ቅሬታ ሲያስነሳ ነበር፡፡ በምክክሩ ወቅት ይህ ጉዳይ መነሳቱን ያስታወሱት ዳይሬክተሩ፣ ይህ ክፍተት የቡና አቅርቦቱ ላይ ተፅዕኖ እንዳሳረፈ አስታውሰዋል፡፡ ይህንን ቅሬታ ለመፍታት ከውሳኔ ላይ ተደርሷል ይላሉ፡፡ ችግሩን ለመፍታት አቅራቢዎች ቡናቸውን ወደ መጋዘን አገልግሎት ድርጅት ከመጫናቸው በፊት አስቀድመው በማስመዝገብ ወረፋ ሲደርሳቸው አገልግሎቱን እንዲያገኙ የሚያስችል አሠራር እንዲዘረጋ በማድረግ ችግሩን ለመቅረፍ እየተሞከረ እንደሚገኝ አቶ ሳኒ ጠቅሰዋል፡፡ ቡና የጫና ተሽከርካሪ ወደ መጋዘን ካደረሰ በኋላ በምን ያህል ቀንና ሰዓት ውስጥ መስተናገድ እንዳለበት የሚደነግግ የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድ እንዲዘጋጅ ተደርጎ እየተተገበረ እንደሚገኝና በዚህ በኩል ሲቀርቡ የነበሩ ቅሬታዎች ስለመፈታታቸው ከአቶ ሳኒ ረዲ ገለጻ ለመረዳት ተችሏል፡፡

ከመጋዘን አገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ በርካታ ቅሬታዎች ይቀርብባቸው ከነበሩ ጉዳዮች አንዱ በቡና እርጥበት ምክንያት ብዙ መጉላላትና ላልተገባ ወጪ መዳረግን የተመለከተው ነው፡፡ ባለሥልጣኑ ከድርጅቱ አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር ባካሄደው ውይይት መፍትሔዎች መቀመጣቸው ተብራርቷል፡፡ ዓለም አቀፍ የቡና የጥራት ደረጃንና የቡና የእርጥበት መጠንን ታሳቢ ያደረገ የግብይትን ደንብ እየሠራበት እንደሚገኝ ሲገለጽ፣ የእርጥበት መጠኑ 12 በመቶ የሆነ ቡና ርክክብ እንዲደረግበት፣ ከዚያ በላይ እርጥበት ያለው ቡና ግን የመጋዘን ድርጅቱ የእርጥበት ማካካሻ ክብደት በፈቃደኝነት ላይ ተመሥርቶ እየቀነሰ እንዲረከብ ተወስኗል ተብሏል፡፡

የመጋዘን አገልግሎት ድርጅት በሚረከበው ቡና ላይ  በሚሰጠው የጥራት ደረጃ ላይ ቅሬታ ያለው አካል በአጭር ጊዜ እንዲሁም በአነስተኛ ወጪ የሚስተናገድበት አሠራር እንደተፈጠረም ተጠቅሷል፡፡ በድርጅቱ የጥራት ደረጃ አሰጣጥ ላይ ቅሬታ ያለው ላኪ፣ በሦስተኛ ወገን ዳኝነት ይስተናገድ የነበረው አዲስ አበባ ብቻ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ሳኒ፣ ከሁሉም ማዕከላት ቅሬታ የቀረበበት ቡና አዲስ አበባ መጥቶ የጥራት ደረጃውን መሠረት ያደረገው ቅሬታ ታይቶ ምላሽ እስኪሰጠው ድረስ ረዥም ጊዜ የሚወስድ በመሆኑ ለዚህ መፍትሔ የሚሆን ዕርምጃ ወስደናል ይላሉ፡፡

የሦስተኛ ወገን ቡናና ሻይ ባለሥልጣን የቡና ጥራት ሰርተፍኬሽን ማዕከል ቀድሞ በአዲስ አበባ ብቻ ይሸጥ የነበረውን አገልግሎት በጅማ፣ በሐዋሳና በድሬዳዋ እንዲሰጥ ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡ ይህ አገልግሎት በዚህ ወር እንደሚጀመር ይጠበቃል፡፡

 

Standard (Image)

ጉምቱዎቹ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች የተዘከሩበት ዓውድ

$
0
0

በፋይናንስ ኢንዱስትሪ ውስጥ ለየት ያለ ክስተት መታየት ጀምሯል፡፡ ለአገርም ሆነ ለፋይናንስ ኢንዲስትሪው ዘርፍ መልካም ሠርተዋል ለተባሉ ሰዎች ዕውቅና የመስጠት  ጅምሮዎች እየታዩ ነው፡፡

 ሐሙስ ጥር 4 ቀን 2009 ዓ.ም. በአገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች በተለይም በፋይናንስ ኢንዱስትሪው ውስጥ ከሩብ ምዕተ ዓመት በላይ አገልግሎት ሲሰጡ ለቆዩ ሁለት አንጋፋ ባለሙያዎች ዕውቅና ተሰጥቷል፡፡

እንዲህ ያለው ፕሮግራም ከጥቂት ሳምንታት በፊት ለቀድሞው የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥ ዕውቅና ለመስጠት የተዘጋጀውን ፕሮግራም ያስታውሳል፡፡ አቶ ጌታሁን ናና በአገሪቱ የፋይናንስ ኢንዱስትሪ ውስጥ የግል ባንኮች እንዲስፋፉ ያደረጉት ጥረት ዕውቅና ተሰጥቶት በክብር መሸኘታቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ከዚያ ፕሮግራም በኋላ ብዙም ሳይቆይ ሌሎች ባለውለታዎችን የሚያመሠግን ፕሮግራም ከተፍ ብሏል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እንዲህ ባለሟሎችን በአግባቡ የመዘከር ተግባር እንዲለመድ ፍላጎቱን ገልጾ ነበር፡፡ ይኸው መድረክም በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲደገም አድርጓል፡፡

 ከደርግ ውድቀት በኋላ በአገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ክንዋኔዎች ጀርባ ትልቅ ቦታ እንደነበራቸው የሚነገርላቸው ሁለት የቀድሞ የብሔራዊ ባንክ ቦርድ ሰብሳቢዎች ዕውቅና እንዲሰጣቸው ገዥው ባንክ አድርጓል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ተክለወልድ አጥናፉና የሚመሩት አስተዳደር፣ ለ25 ዓመታት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክን በቦርድ አባልነትና በቦርድ ሰብሳቢነት ላገለገሉት አቶ ነዋይ ገብረአብ ዕውቅና ሰጥቷል፡፡ ከአንጋፋው የኢኮኖሚ ባለሙያው ከአቶ ነዋይ ባሻገር፣ ባንኩን በሰብሳቢነት ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ ፋንታዬ ቢፍቱንም በዕውቅና አሰጣጥ ሥነ ሥርዓቱ ተሳታፊ ያደረገ ነበር፡፡ ሁለቱ ጉምቱዎች ከብሔራዊ ባንክ ጋር በነበራቸው የሥራ ግንኙነት  ብቻ ሳይሆን በአገር ደረጃ የሠሯቸው ሥራዎች የተብራሩበትና ለዚህ አገልግሎታቸውም  ዕውቅና የተሰጠበት ፕሮግራም ተስተናግዷል፡፡

 ፕሮግራሙን በማሰናዳት ቀዳሚ የሆነው ብሔራዊ ባንክ ሲሆን ገዥው አቶ ተክለወልድ፣ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የቦርድ ሰብሳቢነትና ከመንግሥት ኃላፊነታቸው በቅርቡ በጡረታ ስለተገለሉት አቶ ነዋይና ለዕውቅና ስላበቃቸው ምክንያትም አብራርተዋል፡፡

ከሩብ ክፍለ ዘመን በላይ የብሔራዊ ባንክ የቦርድ አባልና ሰብሳቢ ሆነው ካበረከቱት አስተዋጽኦ በላይ፣ አገሪቷ ለደረሰችበት ኢኮኖሚያዊ ዕድገት አጋዥ የሆኑ አገራዊ ፖሊሲዎች እንዲቀረጹ በማድረግና በትግበራቸውም ላይ የአቶ ነዋይ አሻራ ከፍተኛ እንደነበር አቶ ተክለወልድ አስረድተዋል፡፡

አቶ ነዋይ ለኢትዮጵያ ማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋት አስተዋጽኦ ካበረከቱ ጥቂት ባለሙያዎች ውስጥ አንዱ ናቸው ያሉት አቶ ተክለወልድ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የነፃ ገበያ ሥርዓት ከጀመረበት 1984 ዓ.ም. ጀምሮ በጦርነት የደቀቀውን ኢኮኖሚ እንዲያንሰራራና ሥር የሰደደው ድህነት እንዲቀንስ በማድረግ ሥራዎች ውስጥ ጎልተው ከሚጠቀሱ ባለሙያዎች ተርታ ይመደባሉ፡፡ የአገሪቱ የዕዳ ጫና እንዲቀንስ፣ የሕዝብ ገቢ እንዲያድግ፣ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት እንዲገባና እንዲስፋፋ በማድረግም ስማቸው ተሞካሽቷዋል፡፡ የአገሪቱን ፈርጀ ብዙ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች የሚመለከቱ ስትራቴጂዎችና ፖሊሲዎችን ከመቅረጽ ጀምሮ እስከ ትግበራቸው ሒደት የላቀ ተሳትፎ በማድረጋቸው፤ ይህም ውጤት በማስገኘቱ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አሁን ላለበት ደረጃ ደርሷል በማለትም ስለ አንጋፋው ባለሙያ መስክረዋል፡፡

አቶ ነዋይ በአገሪቱ የኢኮኖሚ መዋቅር ውስጥ ስላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስክርነት የሰጡት የቀድሞ የብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ለይኩን ብርሃኑ በበኩላቸው፣ ዕዳ ለማስቀነስ ብቻ ሳይሆን፣ የአሪቱን የወደፊት የኢኮኖሚ አቅጣጫ ለማመላከት ብዙ ስለመሥራታቸው በመጥቀስ አቶ ነዋይን በብዙ ገልጸዋቸዋል፡፡

የዕዳ ስረዛ

በወርሃ ግንቦት 1983 ዓ.ም. የደርግ ውድቀት ሲታወጅ፣ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከሚታሰበውም በላይ የተንኮታኮተበት ጊዜ ነበር፡፡ የወቅቱ ፕሬዚዳንት አቶ መለስ ዜናዊ ስለአገሪቱ ኢኮኖሚ ሲገልጹ ደርግ ምንም የተወው ነገር እንዳልነበረ፣ ትቶ የሄደው ባዶ ካዝና ነው የሚለው ንግግራቸው ይታወሳል፡፡

ችግሩ ባዶ ካዝና መረከቡ ሳይሆንና ያለቅጥ የተከማቸው የአገሪቱ የውጭ ብድር ዕዳ ለአዲሱ ሥርዓት ትልቅ ፈተና እንደነበር ሲገለጽ ይታወሳል፡፡ የዕዳው ስሌት ኢትዮጵያ በነበረችበት የዳሸቀ የኢኮኖሚ አቅም ተከፍሎ የሚያልቅ እንዳልነበረ ግልጽ በመሆኑ፣ አንዱ አማራጭ ለአገሪቱ የተለመነውን ያህል ዕዳ እንዲሠረስ መማፀን ነበር፡፡

በደርግ ጊዜ ለጦር መሣሪያና ለሌሎች ግዥዎች የዋለው ብድር ጫፍ ላይ የወጣበት ጊዜ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ተክለወልድ፣ ይህ ዕዳ ካልተቀነሰ አገሪቱን ማልማትም ሆነ ለልማት የሚሆን ገንዘብ ማግኘት ስለማይቻል ይህንን ፕሮግራም ይዞ ተደራድሮና ተወያይቶ ማስቀነስ ትልቁ ተግባር ሆኖ እንደተገኘ ገልጸዋል፡፡ አቶ ተክለወልድ እንዳሉት፣ ከ25 ዓመታት በፊት አገሪቱ የነበረባትን ዕዳ ለማሠረዝ የሚሠራ ግብረ ኃይል ሲቋቋም፣ የዚህ ቡድን አባል በመሆን የተሳተፉት አቶ ነዋይ እንደነበሩ አብራርተዋል፡፡ እንደ አቶ አጥናፉ ገለጻ፣ አቶ ነዋይ በአገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ክዋኔዎች ውስጥ ካሳረፏቸው አሻራዎች መካከል የአገሪቱን ዕዳ ለማሠረዝ ያደጉት ውጤታማና ትልቅ ተግባር የሚጎላ እንደነበር ገልጸዋል፡፡

ለዕዳ ስረዛ በያቅጣጫው ጉዞ ተደርጓል፡፡ በዚህ ‹‹ጉዞ ዕዳ ስረዛ›› መርሃ ግብር ተሳታፊ ከነበሩ አባላትና በዕለቱ ፕሮግራም ላይ ከተገኙት የወቅቱ የሥራ ኃላፊዎች መካከል አንዱ አቶ ሱፊያን አህመድ ነበሩ፡፡

አድካሚ በነበረው የዕዳ ስረዛ ዘመቻ ወቅት በኢትዮጵያ ላይ ዕዳ ከነበራቸው አገሮች አንዷ ሰሜን ኮሪያ እንደበረች አቶ ሱፊያን አስታውሰዋል፡፡ ሰሜን ኮሪያ ከምትከተለው ርዕዮተ ዓለም አኳያ እንዲሁም የኢትዮጵያ መንግሥት ሲቀየር ሸሪኳን ካጣጭው ከዚህች አገር ጋር ዕዳ እንድትቀንስ ለመደራደር መጓዝ የቱን ያህል ከባድ እንደበነር የቀድሞው የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር አቶ ሱፊያን አስታውሰዋል፡፡ አቶ ለይኩንም ከዓለም ባንክና ከዓለም የገንዘብ ድርጅት ጋር የነበውን አታካች ድርድር በአሸናፊነት ለመወጣት የአቶ ነዋይን አስተዋጽኦ ዘክረዋል፡፡

የአበባ ዘርፍና አቶ ፋንታዬ

ኢትዮጵያ ለወጪ ንግድ ከምታቀርባቸው ሸቀጦች ውስጥ አበባ የተካተተው የዛሬ 16 ዓመታት ግድም ነው፡፡ አበባ የአገሪቷ የውጭ ምንዛሪ ማስገኛ ሊሆን እንደሚችል ሲጠነሰስ፣ ሐሳቡንም ተቀብሎ ሥራ ላይ ለማዋል ይደረግ በነበረው ዝግጅት ወቅት ይካሄዱ የነበሩ የሐሳብ ፍጭቶች ይታወሳሉ፡፡ በተለያዩ መድረኮችም ደጋግመው ተንፀባርቀዋል፡፡ ለአበባ ምቹ እንደሆኑ ከታሰቡትና በአዲስ አበባ ዙሪያ ከሚገኙ የኦሮሚያ ልዩ ዞኖች ውስጥ ቦታ ለማግኘት የነበረው ትርምስ በቀላሉ የሚታይ አልነበረም፡፡ አበባ የአገሪቱ የውጭ ምንዛሪ ምንጭ ስለመሆኑ ቀድሞ እምነት ከነበራቸው ጥቂት የመንግሥት ኃላፊዎች መካከል አንዱ አቶ ፋንታዬ ቢፍቱ ነበሩ፡፡

አቶ ፋንታዬ የአበባ ልማት በኢትዮጵያ እንዲጀመር ሐሳቡንም መንግሥት እንዲቀበለው ለማድረግ ሲሞግቱ ቆይተዋል፡፡ ቀስ በቀስም ወደ ተግባር እንዲገባ በማድረጉ ሥራ ውስጥ ትልቅ ቦታ ነበራቸው፡፡

በእርግጥም የአበባ ልማት ዛሬ ላይ ከሚገኙ ከአገሪቱ አሥር ዋና ዋና የወጪ ንግድ ሸቀጦች ውስጥ አንዱ ሆኗል፡፡ ዓመታዊ የውጭ ምንዛሪ ግኝቱም ቢሆን ከ220 ሚሊዮን ዶላር በላይ ሆኗል፡፡ ቀድሞ እንደታሰበውና ተስፋ የተደረገበትን ያህል የውጭ ምንዛሪ ባያስገኝም፣ ለአገሪቱ የውጭ ምንዛሪ ምንጭ በመሆን አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል፡፡

ለአበባ ዘርፍ መጎልበት የአቶ ፋንታዬ አስተዋጽኦ ቀዳሚውን ድርሻ ይይዛል፡፡ አበባንና የአቶ ፋንታዬን ጥረት ወደኋላ መለስ ብለው ያስታወሱት አቶ ተክለወልድ፣ ‹‹አቶ ፋንታዬ የአበባ ልማት እንዲጀመር ብዙ የታገለ፣ በኋላም የተሳካለት ሰው ነው፤›› ብለዋቸዋል፡፡ የብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ተክለወልድ ዛሬ ለደረሱበት ደረጃ መብቃት የአቶ ፋንታዬ አስተዋጽኦ እንደታከለበት ሳይጠቅሱ አላለፉም፡፡ በሽግግሩ መንግሥት ጊዜ በኢኮኖሚ ዘርፎች ውስጥ ለመሥራት ወደ ቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጽሕፈት ቤት በማቅናት ሥራ ቀድመው በመጀመር የሚታወቁት አቶ ነዋይና አቶ ፋንታዬ መሆናቸውም ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ፖሊሲዎች ጀርባ የነበራቸውን ትልቅ ሚና እንደሚሳይ ተነግሮላቸዋል፡፡

በዕለቱ አንጋፋዎቹን ለመዘከር በተጠራው መድረክ ከታደሙ የፋይናንስ ባለሙያዎች መካከል 80ኛ የልደት በዓላቸውን በቅርቡ የሚያከብሩት አቶ ኢየሱስ ወርቅ ዛፉ ሌላኛው ተናጋሪ ነበሩ፡፡

አቶ ኢየሱስ ወርቅ፣ ከአቶ ነዋይና ከአቶ ፋንታዬ ጋር አብረው ተምረዋል፡፡ አብሮ መማር ብቻም ሳይሆን፣ በወቅቱ ይካሄዱ በነበሩ የተማሪዎች ንቅናቄዎች ውስጥ አንዳቸው ፕሬዚዳንት ሌላኛው ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ነዋይ ደግሞ ጸሐፊ ሆነው ስለማገልገላቸውም አስታውሰዋል፡፡ እንዲህ ያለው የዕውቅና መድረክ መልካም ጅምር መሆኑን የገለጹት አቶ ኢየሱስ ወርቅ፣ ዕውቅና የመስጠት ልማዱ በሌሎችም መስኮች ሊቀጥል እንደሚገባ አስታውሰዋል፡፡

በፕሮግራሙ ከኢኮኖሚና ፋይናንስ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ በመንግሥት ኃላፊነት ላይ የነበሩ ባለሥልጣናት የተካፈሉበት ነበር፡፡ አቶ ሱፊያን አህመድን ጨምሮ አዲሱ የብሔራዊ ባንክ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ መኮንን ማንያዘዋልን ጨምሮ በአገሪቱ የፋይናንስ ኢንዱስትሪዎች ውስጥ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ሲሠሩ የነበሩ መሪዎችም  ታድመዋል፡፡ 

Standard (Image)

የካቲት ፐልፕና ወረቀት በ1.9 ቢሊዮን ብር ዘመናዊ ፋብሪካ ሊገነባ ነው

$
0
0

- ፋብሪካው ከ70 ከመቶ በላይ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ይተካል ተብሏል

ወደ ግል ከተዛወረ ሰባት ዓመታት ያስቆጠረው የካቲት ፐልፕና ወረቀት ማምረቻ ድርጅት፣ ከ1.8 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ በአንድ ዓመት ተኩል ጊዜ ውስጥ ግንባታውን አጠናቆ ወደ ሥራ እንደሚያስገባ አስታወቀ፡፡

የየካቲት ወረቀት ሥራዎች እህት ኩባንያ የሆነው የካቲት ፐልፕና ወረቀት ማምረቻ ድርጅት፣ ቻይና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ከተባለው መንግሥታዊ ተቋራጭ ጋር ባደረገው የዲዛይን፣ የግዥ እንዲሁም የግንባታ አጠቃላይ ሥራ ስምምነት መሠረት፣ አዲሱ ማምረቻ ፋብሪካ በዓመት 70 ሺሕ ቶን ልዩ ልዩ ዕቃዎች ማሸጊያ ካርቶኖችንና 15 ሺሕ ቶን ለደብተርና ለልዩ ልዩ ውጤቶች ማምረቻ የሚውል ለስላሳ ወረቀት እንደሚያመርት ይጠበቃል፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታው ዶ/ር ዓለሙ ስሜ ማክሰኞ አመሻሹ ላይ በማሪዮት ኤክሲክቲቭ አማርትመንት ሆቴል በተካሄደው የግንባታ ስምምነት ወቅት እንደተናገሩት፣ በአገሪቱ በየዓመቱ ከ200 ሺሕ ቶን በላይ የወረቀትና የወረቀት ውጤቶች ምርት ፍላጎት አለ፡፡ ይህንን ፍላጎት ለማሟላት ከ2.6 ቢሊዮን ብር ወይም ከ130 ሚሊዮን ዶላር ያላነሰ ገንዘብ ወጭ እንደሚደረግም አብራርተዋል፡፡

ምንም እንኳ በአገሪቱ 120 ሺሕ ቶን ወረቀትና የወረቀት ምርቶች እንደሚመረቱ ቢገለጽም፣ ከፍላጎቱ አኳያ ፍላጎትን ማሟላት እንዳልተቻለ ጠቅሰዋል፡፡ ይልቁንም በአምስት ዓመት ውስጥ የአገሪቱ የወረቀት ምርቶች ፍላጎት መጠን ከ400 ሺሕ ቶን በላይ እንደሚደርስ ይጠበቃል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፣ በአገሪቱ እየተቋቋሙ ያሉት የወረቀት ፋብሪካዎች የአገር ውስጥ ፍላጎትን ከማሟላት አልፈው ወደ ውጭ ኤክስፖርት ማድረግ እንደሚጀምሩ ለሪፖርተር አብራርተዋል፡፡

የየካቲት ወረቀት ሥራዎች የፋብሪካ ግንባታ ፕሮጀክት ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ዓለሙ እንደገለጹት፣ በሦስት ምዕራፎች የተከፋፈለው የፋብሪካው ግንባታ፣ በኦሮሚያ ገላን ከተማ በ50 ሺሕ ካሬ ሜትር ላይ የሚያርፍ ነው፡፡ በመጀመሪያው የፋብሪካው የግንባታ ምዕራፍ፣ 210 ቶን ጥቅል ወረቀት በቀን ማምረት የሚቻልበት ግንባታ ይካሄዳል፡፡

በምዕራፍ ሁለት ግንባታ ደግሞ 45 ቶን ለስላሳ ወረቀት በቀን ማምረት የሚያስችል ይሆናል፡፡ ይህ ደግሞ በያመቱ ወደ አገር ውስጥ የሚገባውን 12 ሺሕ ቶን ደብተር በአገር ውስጥ ለማምረት እንደሚያስችል አቶ ዮናስ ተናግረዋል፡፡ በምዕራፍ ሦስት ለሚገነባው የፐልፕ ማምረቻ መስመር ግን መንግሥት የሸንኮራ አገዳ ተረፈ ምርት የሆነውን ምጣጭ (ባጋስ) በተገቢው መንገድ የማቅረብ ኃላፊነት እንዳለበት አስታውቀዋል፡፡

በአገሪቱ እየተስፋፉ የሚገኙት የስኳር ፋብሪካዎች የባጋስ አቅርቦትን እንደሚያሻሽሉት ጠቅሰው፣ ይህም ሆኖ ተረፈ ምርቱ የሚካሄድበትን የግብይት ሥርዓት ፈር የማስያዝና የግብይት ሥርዓት የመዘርጋት ሚናም የመንግሥት ድርሻ መሆኑን አቶ ዮናስ በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ለታደሙት ለመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚኒስትር ዶ/ር ግርማ አመንቴና ለሌሎችም ባለሥልጣናት ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ከአንድ ዓመት ተኩል በኋላ ዕውን እንደሚሆን የሚጠበቀው ፕሮጀክት፣ ወደ ኬንያ፣ ሱዳን እንዲሁም ወደ ሌሎች ጎረቤት አገሮች በያመቱ ከአሥር ሚሊዮን ዶላር በላይ ዋጋ ያላቸው ምርቶችን እንደሚልክ፣ በአንፃሩም ከ15 ሚሊዮን ዶላር በላይ ያስወጡ የነበሩ ምርቶችንም በአገር ውስጥ በማምረት ለመተካት እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡ ይሁንና በአሁኑ ወቅት 70 ከመቶ ከውጭ በሚመጡ ምርቶች ላይ ተንተርሶ የወረቀትና የወረቀት ምርቶች በማምረት ላይ እንዲገኝ የየካቲት ወረቀት ሥራዎች ድርጅት ሥራ አስኪያጅ አቶ ሐቢብ መሐመድ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ከ2500 ላላነሱ ሠራተኞች ቋሚ የሥራ ዕድል፣ 7000 ለሚደርሱትም መደበኛ ያልሆኑ የሥራ ዕድሎችን ይፈጥራል የተባለው የወረቀትና የወረቀት ውጤቶች ማምረቻ ፋብሪካ በያመቱ ከ2.6 ቢሊዮን ብር ያላነሰ ገቢ እንደሚያስገኝም አቶ ሐቢብ ገልጸዋል፡፡

የካቲት የወረቀትና የፐልፕ ውጤቶች ማምረቻ ድርጅት በ1960ዎቹ መጀመሪያ ሰሞን የተመሠረተ ሲሆን፣ እህት ኩባንያው የካቲት የወረቀት ሥራዎች ድርጅትን ጨምሮ በ2002 ዓ.ም. በ47 ሚሊዮን ብር ወደ ግል ተዛውሯል፡፡ ድርጅቱን ከመንግሥት የገዙት አቶ ጎበዝአየሁ ዘርይሁን እና ወ/ሮ ምሥራቅ አየለ የተባሉ ግለሰቦች ናቸው፡፡ ሁለቱ ባለአክሲዮኖች በትዕዛዙ ኃላፊነቱ የተወሰነ ኩባንያ የተባለ ኩባንያም ማቋቋማቸው ታውቋል፡፡

 

 

 

Standard (Image)

የመድን ኢንዱስትሪውና የገበያ ድርሻ ትንቅንቅ

$
0
0

የፋይናንስ ኢንዱስትሪው ዋነኛ ተዋንያኖች በመሆን የሚጠቀሱት ባንኮች፣ ኢንሹራንሶችና የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት በጥቅል እያሳዩ ያለው ዕድገት በተለያየ መንገድ እየተገለጸ ነው፡፡ በተለይ ባንኮች በአገራዊ ኢኮኖሚ ዕድገት ያሳረፉት አሻራ ጎልቶ ይታያል፡፡ ባንኮች በመጀመሪያው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን የዕቅድ ዘመን ለአገራዊ ኢኮኖሚ ዕድገቱ የነበራቸው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ስለመሆኑ በገሃድ ታይቷል፡፡

የባንክ ኢዱስትሪው በዚህን ያህል ደረጃ የሚገለጽ ቢሆንም፣ የኢንሹራንስ ኢንዱስትሪው ግን የባንክን ያህል ዕድገት ታይቶበታል ማለት አይቻልም፡፡ የኢንዱስትሪው ዓመታዊ ዕድገት የባንክን ያህል አለመሆኑ መረጃዎች ይጠቅሳሉ፡፡

በአሁኑ ወቅት የኢንሹራንስ ኩባንያዎች 17 ደርሰዋል፡፡ እነዚህ ኩባንያዎች በመላ አገሪቱ ከ450 በላይ ቅርንጫፎች ያሏቸው ሲሆን፣ አሁን ባንኮች ከደረሱበት 3,800 ቅርንጫፎች አንፃር ሲታይ አነስተኛ ነው፡፡

የኢንዱስትሪው ዕድገት እምብዛም ነው ከሚባልባቸው በርካታ ምክንያቶች ውስጥ  የኢንዱስትሪው ዋነኛ ሥራ ሆኖ የሚጠቀሰው የዓረቦን አሰባሰብ መጠን ነው፡፡ የኢንሹራንስ ኩባንያ ዓመታዊ የዓረቦን መጠን የኩባንያውን እንቅስቃሴ ማመላከቻና የገበያ ድርሻቸው መለኪያም እንደሆነ ይጠቀሳል፡፡ ከዚህ አንፃር ኩባንያዎቹ ባለፉት አምስት ዓመታት ባደረጉት ጉዞ በዓረቦን አሰባሰብ በአማካይ ያሳዩት ዕድገት ከስምንት በመቶ ያነሰ ነው፡፡

ወደ አምስት ትሪሊዮን ብር ለሚገመት ንብረት የዋስትና ሽፋን የሰጡት እነዚህ ኩባንያዎች፣ በየዓመቱ የሰጡት አዳዲስ የመድን ሽፋን ዕድገት ሲታይም አነስተኛ ነው፡፡ በተለይ በሕይወት ነክ ኢንሹራንስ ዘርፍ ያለው አፈጻጸም እጅግ ዝቅተኛ ነው፡፡ በየዓመቱ የሚሰበሰበው የዓረቦን የሕይወት ኢንሹራንስ ድርሻ ከስድስት በመቶ ያነሰ ነው፡፡  

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዓመታዊ ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት በአገሪቱ ውስጥ ያሉት 17ቱም የኢንሹራንስ ኩባንያዎች በ2007 ላይ የጻፉት የዓረቦን መጠን 5.6 ቢሊዮን ብር ሲሆን፣ በ2008 ዓ.ም. 6.2 ቢሊዮን ብር ደርሷል፡፡ ይህም ቢሆን የሚያመለክተው የተሰበሰበው የዓረቦን መጠን ዕድገቱ አዝጋሚ መሆኑን ነው፡፡ የ2009 በጀት ዓመት የግማሽ በጀት አፈጻጸም የዓረቦን አሰባሰቡ ዕድገት አዝጋሚ መሆኑን ሪፖርቱ አመላክቷል፡፡

2008 እና ኢንሹራንስ ኩባንያዎች

ኩባንያዎች የዓረቦን መጠናቸው ዕድገት ይህንን ያህል ቢሆንም፣ ለካሳ ክፍያ የሚያውሉት ገንዘብ ግን በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ መምጣት እንደ ባንኮች በመቶ ሚሊዮን ብሮች የሚገመት ትርፍ ማስመዝገብ አልቻለም፡፡ ከኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ድርጅት ሌላ የቀሪዎቹ ትርፍ ከ100 ሚሊዮን ብር በታች ናቸው፡፡ ባንኮች ግን ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ወደ ማትረፍ እየደረሱ ናቸው፡፡

በሌላ በኩል ባንኮች በየዓመቱ የትርፍ መጠናቸው ከዓመት ዓመት እየጨመረ ሲመጣ፣ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ግን የትርፋቸው አንዳንዴ ከፍ ሌላ ጊዜ ዝቅ ማለት ይታይበታል፡፡ በተለይ በ2008 በጀት ዓመት ወደ ስድስት የሚሆኑ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ከቀዳሚው በጀት ዓመት ያነሰ ትርፍ አስመዝግበዋል፡፡

አንዱና አሥራ ስድስቱ

በኢንዱስትሪ ውስጥ ካሉት 17 ኩባንያዎች አንዱ የመንግሥት ነው፡፡ ቀሪዎቹ ደግሞ የግል ኢንሹራንስ ኩባንያዎች ሲሆኑ፣ ሁሉም ኩባንያዎች የገበያ ድርሻ በየዓመቱ የሚቀያየር ቢሆንም፣ የመንግሥታዊው የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ኩባንያ የገበያ ድርሻ ከዓመት ዓመት እየቀነሰ መምጣቱን ያሳያል፡፡

በ2009 ግማሽ የበጀት ዓመት የኢንሹራንስ ኩባንያዎቹን አፈጻጸም የሚያሳየው የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት ሕይወት ነክ ካልሆነው ኢንሹራንስ 3.4 ቢሊዮን ብር ዓረቦን ሰብስበዋል፡፡ ይህ የዓረቦን መጠን ከቀደመው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከ150 ሚሊዮን ብር በላይ ብልጫ ያለው ቢሆንም፣ ዕድገቱ ግን አሁንም አነስተኛ  ነው፡፡

በቀደመው ዓመት በመጀመርያ ስድስት ወራት የኢንሹራንስ ኩባንያዎቹ ሰብስበውት የነበረው የዓረቦን መጠን 3.37 ቢሊዮን ብር ነበር፡፡ የኢንሹራንስ ኩባንያዎቹን የተናጠል አፈጻጸም ሲታይም ከ17ቱ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ሁለቱ በ2008 ዓ.ም. የመጀመሪያ ስድስት ወራት የዓረቦን መጠን በዘንድሮው ያገኙት ያነሰ ሲሆን፣ ቀሪዎቹ ከቀደመው ዓመት ብልጫ ያለው ዓረቦን መሰብሰባቸውን መረጃው ያሳያል፡፡ ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች ጋር በንፅፅር ሲታይም ኢንዱስትሪው ያለበት ደረጃ ዝቅተኛ መሆኑን የሚገልጹ ባለሙያዎች አሉ፡፡ በተለይ በሕይወት ኢንሹራንስ ዘርፍ የኢትዮጵያ ድርሻ ኢምንት ነው፡፡

የገበያ ድርሻ

የአገሪቱ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች የገበያ ድርሻው ከዓመት ዓመት ይለዋወጣል፡፡ በተለይ መንግሥታዊው የኢትዮጵያ መድን ድርጅት የገበያ ድርሻ ከዓመት ዓመት እየቀነሰ ስለመምጣቱ እየታየ ነው፡፡ ከአምስት ዓመት በፊት በአገሪቱ የኢንሹራንስ ቢዝነስ ከ50 በመቶ በላይ የነበረው የገበያ ድርሻው እየቀነሰ መሄዱን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

የ2009 የበጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ግርድፍ መረጃ የሚጠቁመው ደግሞ፣ የኢትዮጵያ የመድን ድርጅት የገበያ ድርሻ በ16ቱ የግል ኢንሹራንስ ኩባንያዎች እየተወሰደ ነው፡፡ እንደ መረጃው ከሆነ በበጀት ዓመቱ ሕይወት ነክ ካልሆነ የኢንሹራንስ ዘርፍ በተሰበሰበው ዓረቦን የኩባንያዎቹ የገበያ ድርሻ ሲሰላ፣ የኢትዮጵያ መድን ድርጅት የገበያ ድርሻ ወደ 30 በመቶ ወርዷል፡፡ ሕይወት ነክ ኢንሹራንስ የታከለበት ከጠቅላላ የኢንሹራንስ ዘርፍ የተሰበሰበው ዓረቦን ሲታይም፣ የኢትዮጵያ መድን ድርጅት የገበያ ድርሻ 32 በመቶ መድረሱን ያመለክታል፡፡

የገበያ ድርሻው መውረዱ ብቻ ሳይሆን ከ2009 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ሕይወት ነክ ካልሆነው መድን 1.04 ቢሊዮን ብር በመሰብሰብ ከሁሉም የመድን ድርጅቶች ብልጫ ቢኖረውም፣ ይህ የዓረቦን መጠን አምና በተመሳሳይ ወቅት ሰብስቦት ከነበረው ጋር ሲነፃፀር በ23 በመቶ ቀንሷል፡፡ በ2008 ዓ.ም. የመጀመሪያ ስድስት ወራት የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ሰብስቦ የነበረው የዓረቦን መጠን 1.36 ቢሊዮን ብር ነበር፡፡ በወቅቱ ድርጅቱ ሕይወት ነክ ካልሆነው ኢንሹራንስ በሰበሰበው የዓረቦን መጠን ይዞት የነበረው የገበያ ድርሻ 41.2 በመቶ ሲሆን፣ ዘንድሮ ግን ወደ 30 በመቶ ሊወርድ ችሏል፡፡ በዘንድሮ በጀት ዓመት በስድስት ወራት አፈጻጸሙ በዚህን ያህል ደረጃ የቀነሰ ኩባንያ ባይኖርም፣ አሁንም ትልቁን የገበያ ድርሻ እንደያዘ ነው፡፡

የግል ኢንሹራንስ ኩባንያዎችና የገበያ ድርሻ

በግማሽ በጀት ዓመቱ ሕይወት ነክ ካልሆነ የኢንሹራንስ ዘርፍ የኢትዮጵያ የመድን ድርጅት ድርሻ 30 በመቶ መድረስ፣ የአገሪቱ የኢንሹራንስ ገበያ 70 በመቶውን የግል ኢንሹራንስ ኩባንያዎች እንዲይዙ አስችሏቸዋል፡፡ በስድስት ወሩ ውስጥ ከተሰበሰበው ዓረቦን 2.3 ቢሊዮን ብር የሚሆነው በግል ኢንሹራንስ ኩባንያዎች የተሰበሰበ መሆኑን መረጃው ያሳያል፡፡

በዚህ መረጃ በዓረቦን አሰባሰብ አዋሽ ኢንሹራንስ ከግል ኢንሹራንስ ኩባንያዎች ብልጫ ያለውን ድርሻ መያዙን ያሳያል፡፡ የአዋሽ የገበያ ድርሻ ዘጠኝ በመቶ ነው፡፡ ኩባንያው በቀደመው ሙሉ በጀት ዓመት ከግል ኢንሹራንስ ኩባንያዎች ትልቁን የገበያ ድርሻ ይዞ ማጠናቀቁን ማሳወቁ አይዘነጋም፡፡ በግማሽ በጀት ዓመቱ ሁለተኛውን የገበያ ድርሻ የያዘው አፍሪካ ኢንሹራንስ ሲሆን፣ ናይልና ኒያላ ደግሞ ተከታዮቹን ደረጃዎች ይዘዋል፡፡

እነዚህ አራት የኢንሹራንስ ኩባንያዎች በቀደመው በጀት ዓመት ስድስት ወራት ከሰበሰቡት ዓረቦን በላይ መሰብሰባቸው የገበያ ድርሻቸውን ጠብቀው እንዲጓዙ አድርጓል፡፡

በ2009 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት አዋሽ ኢንሹራንስ 290 ሚሊዮን ብር፣ አፍሪካ ኢንሹራንስ 265 ሚሊዮን ብርና ኒያላ ኢንሹራንስ 238 ሚሊዮን ብር ዓረቦን ሰብስበዋል፡፡ አምና በስድስት ወራት ውስጥ አዋሽ ኢንሹራንስ 245 ሚሊዮን ብር፣ አፍሪካ ኢንሹራንስ 210 ሚሊዮን ብርና ኒያላ ኢንሹራንስ 199 ሚሊዮን ብር ነበር የሰበሰቡት፡፡

ሕይወት ከኢንሹራንስ

በሕይወት ነክ ኢንሹራንስ ዘርፍ በ2009 በጀት ዓመት የተሰበሰበው የዓረቦን መጠን ከቀዳሚው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ብዙም ጭማሪ አላሳየም፡፡

ከሕይወት ኢንሹራንስ ዘርፍ አምና በመጀመርያው ስድስት ወራት የ80 ሚሊዮን ብር በቀጣዩ ስድስት ወራት ደግሞ 205 ሚሊዮን ብር ዓረቦን ተሰብስቧል፡፡ ከዚህ ውስጥ 56 ሚሊዮን ብር የተሰበሰበው በኢትዮጵያ መድን ድርጅት ነው፡፡

በሕይወት ኢንሹራንስ ኩባንያው የሰበሰበው ዓረቦን ከቀዳሚው በጀት ዓመት  ተመሳሳይ ወቅት ከሰበሰበውም በላይ ብልጫ ያለው ሆኗል፡፡

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት በቀዳሚው በጀት ዓመት ከሕይወት ኢንሹራንስ ዘርፍ 49 ሚሊዮን ብር መሰብሰብ ችሏል፡፡ ይህም በሕይወት ኢንሹራንስ አምና በስድስት ወራት ይዞት የነበረውን 26.2 በመቶ የገበያ ድርሻ ዘንድሮ ወደ 29 በመቶ ማሳደግ አስችሎታል፡፡

አብዛኛዎቹ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች የሕይወት ኢንሹራንስ አገልግሎታቸው ዝቅተኛ ነው፡፡ ይበልጥ ትኩረት የሚሰጡት በኢንዱስትሪው ከ94 በመቶ በላይ ዓረቦን ከሚሰበሰብበት ሕይወት ነክ ካልሆነ ኢንሹራንስ ነው፡፡

 

Standard (Image)

ዶ/ር እሌኒ ወጣት የሥራ ሐሳብ አፍላቂዎችን የሚያስተናግድ ተቋም መሠረቱ

$
0
0

የኢት ዮጵያ ምርት ገበያን ከውጥን ጀምሮ በእግሩ ቆሞ እንዲሄድ በማድረጋቸው አንቱታን ያተረፉት የኢኮኖሚ ባለሙያዋ ዶ/ር እሌኒ ገብረመድኅን፣ ወጣት የሥራ ፈጠራ ሐሳብ አፍላቂዎች የሚጠቀሙበትን ተቋም በአዲስ አበባ ቦሌ አካባቢ ይፋ አድርገዋል፡፡

ተቋሙ ‹‹አዲስ ጋራዥ›› የሚል ሥያሜ የተሰጠው ሲሆን፣ ብሉሙን በተባለውና በዶ/ር እሌኒ የተቋቋመ ኩባንያ ነው፡፡ ሐሙስ ምሽት ሥራ የጀመረው አዲስ ጋራዥ፣ የኢንተርፕረነርሺፕ ተነሳሽነት ያላቸው፣ ወደ ሥራ መለወጥ የሚያስችል ሐሳብ እያላቸው ለቢሮ ኪራይ፣ ለጽሕፈት ሥራዎች፣ ለኢንተርኔትና ለመሳሰሉት አገልግሎቶች የሚጠብቃቸውን ወጪ ለመቀነስ የሚያስችል፣ ሐሳባቸው በኢንቨስትሮች ዘንድ ተቀባይነት አግኝቶ ወደ ተግባር መግባት እስኪችል ድረስ ባለው ሒደት ውስጥ ድጋፍ የሚሰጥ ተቋም መሆኑን ዶ/ር እሌኒ ገልጸዋል፡፡

በውጭው ዓለም ለወጣቶች የቢሮና መሰል መገልገያዎችን በዝቅተኛ ገንዘብ እንዲገለገሉ ከማቅረብ ጀምሮ፣ በጋራ እንዲጠቀሙባቸው የሚያስችሉና የወጪ መጋራት አሠራሮችን የሚከተሉ በርካታ ተቋማት አሉ፡፡ ለአብነት ያህል በአሜሪካና ካናዳ ሰፊ የሥራ አድማስ ያለው ኢንተለጀንስ ኦፊስ የሚባለው ኩባንያ አሁን ዶ/ር እሌኒ በኢትዮጵያ ያስተዋወቁትን ዓይነት አሠራር የሚከተል ነው፡፡ እንደ ዶ/ር እሌኒ ከሆነ በአፍሪካ እንዲህ ያለው ‹‹ኢንተርፕረነርሺፕ ኢንኩቤሽን›› እንዲስፋፋ የሚያስችል የሥራ እንቅስቃሴ የሚታየው በኬንያ፣ በናይጄሪያና በደቡብ አፍሪካ ነው፡፡ ኢትዮጵያም ለወጣት የሥራ ሐሳብ ፈጣሪዎችና ጠንሳሾች ዕድሉን በማመቻቸት ከእነዚህ አገሮች ተርታ እንደምትመደብ ይጠበቃል፡፡

በመሆኑም አዲሱ የዶ/ር እሌኒ ተቋም በአዲስ አበባ ልዩ ልዩ መንደሮች የተሰየሙ የመሥሪያ ቦታዎችን ለወጣቶች አሰናድቷል፡፡ ጀሞ፣ መካኒሳ፣ ፒያሳና ሌሎችም ሰፈሮች ለወጣቶቹ ተሰናድተዋል፡፡

ከ29 ዓመት በታች የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ወጣቶች ቅድሚያ ተሰጧቸው ይሳተፉበታል የተባለው አዲስ ጋራዥ ለ30 ያህል ወጣቶች የመሥሪያ ቦታን ጨምሮ፣ የስብሰባ፣ የመመገቢያና የሻይ ቡና አገልግሎቶችን ያካተተ እንደሆነ ታውቋል፡፡ ለስብሳባ ዝግጅቶች እስከ 150 ሰዎች ማስተናገድ የሚችል ቦታ የተዘጋጀው፣ ከቦሌ መድኃኔዓለም ወደ አትላስ በሚወስደው መቲ ሕንፃ ላይ ሲሆን፣ ተቋሙ ሥራ መጀመሩን በማስመልከት በርካታ የውጭ ዲፕሎማቶችን ጨምሮ ከልዩ ልዩ የኢንቨስትመንትና ሌሎች መስኮች የተጋበዙ ሰዎች ታድመዋል፡፡

ከስምንት ዓመት በፊት ዶ/ር እሌኒ የኢትዮጵያ ምርት ገበያን ዕውን ሲያደርጉ፣ በወቅቱ በወጪ ንግድ ዘርፍ የተሰማሩ ሰዎችና የውጭ ቡና ገዥዎች ብዙም አልተቀበሉትም ነበር፡፡ በጊዜ ሒደት የአገሪቱን የምርት ግብይት መስክ ዘመናዊ ለማድረግ ይረዳል የተባለው ማዕከላዊ ገበያ በአሁኑ ወቅት ግን በዓመት ቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ግብይቶችን ማካሄድ የቻለበት አቅም ላይ ደርሷል፡፡

ከኢትዮጵያ ምርት ገበያ ምሥረታ ጀምሮ እስከ ዋና ሥራ አስፈጻሚነት የነበራቸውን ኃላፊነትና ተሳትፎ በመተው ወደ አፍሪካ አገሮች በማቅናት በተለይ በምሥራቅ አፍሪካ የምርት ግብይት ላይ በማተኮር የሚንቀሳቀሰውን እሌኒ ኤክስቼንጅ በመመሥረት ሲንቀሳቀሱ ቆይተዋል፡፡ 

Standard (Image)

ካርታ ሥራዎች ከ100 በላይ ዘመናዊ የሳተላይት ቅየሳ ማጣቀሻ አውታሮችን ሊገነባ ነው

$
0
0

የኢትዮጵያ ካርታ ሥራዎች ኤጀንሲ እስካሁን ሲጠቀምባቸው የቆዩትን አራት የቅየሳ ጣቢያዎች ከማሻሻልና ከመጠገን ባሻገር ከ100 በላይ የቅየሳ መረብ አውታሮችን ለማስፋት የሚያስችሉና ያለማቋረጥ የሚሠሩ የቅየሳ ማጣቀሻ ጣቢያዎችን በመትከል በሳተላይት የተደገፉና ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች የሚውሉ መረጃዎችን ለማቅረብ የሚያስችለው በጀት ማግኘቱን አስታወቀ፡፡

የካርታ ሥራዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሱልጣን መሐመድ ለጋዜጠኞች እንዳብራሩት በመጪዎቹ ጥቂት ዓመታት ውስጥ ለሚተከሉት ከ100 በላይ የቅየሳ መረብ አውታሮች መንግሥት ለሥራው በቂ በጀት መድቧል፡፡ እንደ አቶ ሱልጣን መግለጫ ለአንድ ቅየሳ ጣቢያ ግንባታ እስከ አራት ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ወጪ ይጠይቃል፡፡ በመሆኑም ለመቶዎቹ ጣቢያዎች ቢያንስ ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደሚደረግ ይጠበቃል፡፡

ቀደም ሲል፣ ከዘጠኝ ዓመት በፊት በአሜሪካ መንግሥት ድጋፍ የተተከሉ አራት የቅየሳ ማጣቀሻ ጣቢያዎች በአገሪቱ ተተክለዋል፡፡ በአዲስ አበባ፣ በጂማ፣ በጎንደር እንዲሁም በድሬዳዋ ተተክለው ከቆዩት ውስጥ ከአዲስ አበባው በስተቀር የተቀሩት በኢንተርኔትና በኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ለብዙ ጊዜ አገልግሎታቸው ሲስተጓጎል ቆይቷል፡፡ አቶ ሱልጣንም ይህንን አስረድተዋል፡፡

ጣቢያዎቹ ይህ ነው የሚባል አገልግሎት መስጠት ሳይችሉ መቆየታቸውን በመመልከት ወደ ሙሉ ሥራ በድጋሚ እንዲገቡ፣ ያለመቋረጥ ለ24 ሰዓታት፣ ሳምንቱን ሙሉ እንዲሠሩ ለማድረግ የመልሶ ግንባታ ሥራ እንዲሠራ አሜሪካ ድጋፏን እንደምትሰጥ አረጋግጣለች፡፡ በአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ትብብር ኤጀንሲ (ዩኤስኤአይዲ) ዓለም አቀፍ ንግድ ጽሕፈት ቤት ዳይሬክተር ሰቴፈን ሞሪን፣ ኤጀንሲው በኢትዮጵያ የገጠር መሬት አስተዳደር፣ የይዞታ ማረጋገጥና መሰል ሥራዎችን ከመደገፍ በተጨማሪ ለኢትዮጵያ ካርታ ሥራዎች ኤጀንሲ የአቅም ግንባታና መሰል ድጋፎች እንደሚሰጥ አስታውቀዋል፡፡

በኢትዮጵያ ከ1997 ዓ.ም. ጀምሮ በሦስት ምዕራፎች ለተካሄደውና ከሦስ ዓመት ጀምሮ እስካሁን በመካሄድ ላይ ላለው የገጠር መሬት አስተዳደርና አቅም ግንባታ ሥራዎች አሜሪካ ድጋፍ ስትሰጥ መቆየቷን ያስታወቁት ሞሪን፣ ከ2008 ዓ.ም. ጀምሮ በአምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ በአገሪቱ 30 ሚሊዮን መሬት ለመለካትና የይዞታ ማረጋገጫ ለመስጠት በመንግሥት ለተያዘው ዕቅድም አጋራቸው ድጋፍ እንደምታደርግ ገልጸዋል፡፡

ዘመናዊ የቅየሳ መረብ አውታሩ በአብዛኛው ከመሬት ጋር ለተያያዙ የሳተላይት መረጃዎች ጥንቅርና ትንተና መረጃ የሚሰጥ ሲሆን፣ በአገሪቱ ይገነባሉ የተባሉት ከ100 በላይ የቅየሳ ማጣቀሻ ጣቢያዎች ከ70 እስከ 100 ኪሎ ሜትር ርቀት ክልል ውስጥ እንደሚተከሉ፣ ይህም ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን በመከተል የሚደረግ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡

እ.ኤ.አ. ከ1957 ጀምሮ አሜሪካ ለኢትዮጵያ ካርታ ሥራዎች ድጋፍ ስታደርግ መቆየቷን ያብራሩት፣ በዩኤስኤአይዲ ቺፍኦፍ ፓርቲ የሆኑት ዶ/ር ሰሎሞን በኩረ ናቸው፡፡ እንደ ዶ/ር ሰሎሞን ከሆነ፣ ከ2005 ዓ.ም. ጀምሮ የገጠር መሬት አጠቃቀምና የሕግ ማዕቀፍን፣ የገጠር መሬት አጠቃቀምና ይዞታ ማረጋገጫ ሠርቲፊኬት እንዲሁም የመሬት መልካም አስተዳደርን ጨምሮ በገጠር መሬት ይዞታ፣ አጠቃቀምና አስተዳደር ሥርዓቶች ላይ የሚካሄዱ የምርምርና የጥናት ሥራዎች ከሌሎች ባሻገር በአሜሪካ ሲደገፉ የቆዩ ሥራዎች መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡

እንደ ዶ/ር ሰሎሞን ማብራሪያ፣ መንግሥት በተለይ የገጠር መሬት አጠቃቀምን በምሉዕነት የሚመራ ፖሊሲ እንዲያዘጋጅ አሜሪካ የቴክኒክ ድጋፍ እያደረገች የምትገኝ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ግን በአፋር፣ በደቡብ፣ በትግራይ እንዲሁም በአማራ ክልሎች ዘመናዊ የመሬት መረጃ አያያዝ ሥርዓት እንዲተገበር ድጋፍ ማድረጓንም ገልጸዋል፡፡ 

 

 

Standard (Image)

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሚመራው የላይኛው ሱሉልታ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

$
0
0

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሚመራ የላይኛው ሱሉልታ አሳታፊ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ፕሮጀክት፣ ጥር 10 ቀን 2009 ዓ.ም. በአዲስ ራማዳ ሆቴል ከባለድርሻዎች ጋር በተካሄደ የምክክር ዓውደ ጥናት ይፋ ሆነ፡፡

ፕሮጀክቱ የሱሉልታ ገበሬዎችን ሕይወት ለመቀየርና ዘላቂ ምርታማነትን ለማረጋገጥ፣ ኢኮሲቲ ለመገንባት፣ የደረቅና የፈሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ ሥርዓት ለመፍጠር፣ ማኅበራዊ አገልግሎትን ለማሻሻልና ለማስተካከል ያለመ ነው፡፡

የፕሮጀክቱ ወጪ በዋነኛነት በፈረንሣይ የውኃ ኩባንያ ነስሌ ዎተርስ የሚሸፈን ይሆናል፡፡ ኩባንያው በአማካሪነት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ውኃና መሬት ሀብት ማዕከልን ቀጥሯል፡፡ ነስሌ ዎተርስ ከግንቦት ወር 2008 ዓ.ም. ጀምሮ የአቢሲንያ ውኃን 51 በመቶ ድርሻ መግዛቱ ይታወሳል፡፡ የአቢሲንያ ውኃ መቀመጫ ደግሞ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል ውስጥ የምትገኘው ሱሉልታ ከተማ ነች፡፡

ነስሌ ዎተርስ በዓለም ትልቁ የታሸገ ውኃ አምራች ኩባንያ ነው፡፡ በ33 አገሮች 93 የውኃ አምራች ኩባንያዎች አሉት፡፡ በአፍሪካ ደግሞ በኢትዮጵያ፣ በግብፅ፣ በአልጄሪያ፣ በደቡብ አፍሪካና በናይጄሪያ ፋብሪካዎች አሉት፡፡ በአጠቃላይ በመላው ዓለም 51 የታሸጉ የውኃ ብራንዶች አሉት፡፡

የውኃና መሬት ሀብት ማዕከል የተጎዱ ተፋሰሶችን በማልማትና በማከም ጥሩ ውጤቶችን በማስመዝገብ ልምድ ያለው ተቋም ነው፡፡ እ.ኤ.አ. ከ1980 ጀምሮ ሥራ ላይ የነበረ ቢሆንም፣ እ.ኤ.አ. በ2011 በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሥር ዳግም ተደራጅቷል፡፡ ማዕከሉ በአገር አቀፍ ደረጃ የአየር ሁኔታ፣ የደለል መጠን፣ የውኃ ፍሰት መጠን፣ የመሬት መራቆት፣ ማኅበራዊና ምጣኔ ሀብታዊ ሁኔታዎችን መከታተያ 12 ጣቢያዎች አሉት፡፡

የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጌጤ ዘለቀ፣ ‹‹የአገሪቱ ትልቁ ጂኦስፓሽያል ኢንፎርሜሽን ያለው እኛ ማዕከል ውስጥ ነው፤›› በማለት ለሪፖርተር ገልጸው፣ መረጃዎቹ በነፃ በድረ ገጻቸው ላይ እንደሚገኝም አመልክተዋል፡፡

ፕሮጀክቱ በዓይነቱ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ እንደሆነም ዶ/ር ጌጤ አስገንዝበዋል፡፡ የግል ኩባንያ የአካባቢ ልማትን ለመደገፍ ያሳየው ተነሳሽነት ለሌሎች ምሳሌ መሆን የሚችል እንደሆነም ገልጸዋል፡፡ ‹‹ሱሉልታ በፍጥነት በማደግ ላይ ያለ አካባቢ ቢሆንም፣ የራሱ የመልማት አቅም እንዳለው ሁሉ ተግዳሮቶችም አሉት፡፡ ፕሮጀክቱ የአካባቢው ማኅበረሰብን ኑሮ ለማሻሻል የአየር ንብረት ሁኔታውን ለማሻሻልና ለመጠበቅ ያለመ ነው፡፡ የዚህ ተነሳሽነት አካል በመሆናችን ደስተኛ ነን፤›› በማለት ለተሳታፊዎች ተናግረዋል፡፡ ‹‹ዓላማችን ሱሉልታን የኢትዮጵያ የኢኮሲቲ ሞዴል ማድረግ ነው፤›› ሲሉም ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

የነስሌ ዎተርስ የውጭ ግንኙነትና ማኅበራዊ ኃላፊነት ምክትል ፕሬዚዳንት ሚስተር ሁበርት ጌኒይስ በበኩላቸው፣ ኩባንያቸው በዘላቂ ልማትና አካባቢ ጥበቃ ላይ ሁሌም ፍላጐት እንዳለው አመልክተዋል፡፡ የውኃ ሀብቶች ልማት ላይ በመላው ዓለም በመሳተፍ የኤክስፐርት ልምድ ማዳበሩንም ገልጸዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል የግብርናና የተፈጥሮ ሀብቶች ቢሮ ኃላፊ አቶ ስለሺ ጌታሁን፣ ‹‹ሱሉልታ ከፍተኛ የከተማ መስፋፋት እየታየበት ያለ አካባቢ ነው፡፡ በዚህም ሒደት ቁልፍ የተፈጥሮ ሀብቶች ላይ ጉዳት እየደረሰ ይገኛል፡፡ በተፋሰሱ ላይ እየደረሰ ባለው ጉዳት መሬት እየተራቆተ ነው፡፡ ተገቢ ያልሆነ የደረቅና የፈሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ ሥርዓት፣ የደን ምንጣሮና ጭፍጨፋ፣ ያልተቀናጀ የመሬት ውድድር እንዲሁ ተጨማሪ ጉዳት እያስከተለ ነው፤›› ብለዋል፡፡ ከዚህም እውነታ አንፃር የነስሌ ዎተርስ ኢትዮጵያ ተነሳሽነት ሊመሰገን የሚገባው እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

አቶ ስለሺ ነስሌ ዎተርስ ከሱሉልታ የተፈጥሮ ሀብት ተጠቃሚ መሆኑን በማመልከት፣ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ያነሳሳው ይኼው እውነታ እንደሆነ አስገንዝበዋል፡፡ ‹‹ፕሮጀክቱ የመንግሥት ሙሉ ድጋፍ አለው፡፡ የውኃውን ጥራትና መጠን በመጠበቅና በመጨመር የራሱን ፍላጎት መጠበቅ ይችላል፡፡ በተጨማሪም የአካባቢውን ማኅበረሰብ ኑሮ ለማሻሻል ያለመ ነው፡፡ ኢንቨስተሮችን መሳብ የምንፈልገው የዜጎችን ኑሮ ያሻሽላል ብለን ስለምናስብ ነው፤›› ብለዋል፡፡

እንደ ዶ/ር ጌጤ ገለጻ ፕሮጀክቱ ሁለት ምዕራፎች አሉት፡፡ በመጀመሪያው ምዕራፍ አማካሪ ድርጅቱ የፕሮጀክት ትልመ ሐሳብን መቅረፅ፣ የላይኛው ሱሉልታ ተፋሰስን ዝርዝር የባዮፊዚካልና የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታን ማጥናት፣ እንዲሁም የተፋሰሱን ሀብቶች በአግባቡ ለመጠቀም የሚያስችል ሁሉን አቀፍ የተፋሰስ ልማት ዕቅድ ማዘጋጀት ይጠበቅበታል፡፡ ይህ ምዕራፍ ከጥምቅት ወር 2009 ዓ.ም. ጀምሮ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡ የፕሮጀክቱ ምዕራፍ ሁለት አፈጻጸሙን የሚመለከት ነው፡፡

‹‹ጥናቱን እናከናውናለን፡፡ አፈጻጸሙን ደግሞ እናስተባብራለን፡፡ ፕሮጀክቱ የሚፈጸመው በአካባቢው ኅብረተሰብና ባለሥልጣናት አማካይነት ነው፡፡ ለዚህ የቴክኒክ ዕርዳታን ጨምሮ ሌሎች እገዛዎችን እናደርጋለን፡፡ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎችን መከታተል፣ ማስተባበር፣ ሕዝቡንና ባለሥልጣናቱን ለሥራ የማንቀሳቀስ ኃላፊነት በማዕከሉ ላይ የወደቀ ነው፤›› በማለትም አብራርተዋል፡፡

ነስሌ ዎተርስ የፕሮጀክቱን ጥናት ለማካሄድ 150,000 ዶላር ክፍያ ለማዕከሉ መፈጸሙን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ድርጅቱ ለአፈጻጸሙ የሚያስፈልገውን ገንዘብ በአብዛኛው እንደሚያቀርብ ይጠበቃል፡፡ ይሁንና ዶ/ር ጌጤ የፕሮጀክቱን ባለቤትነት የኦሮሚያ ክልልና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ሊወስዱ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

በምክክር ዓውደ ጥናቱ ከመንግሥት፣ ከግልና መንግሥታዊ ካልሆኑ አካላት የተውጣጡ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት የተለያዩ ግብዓቶችን ሰጥተዋል፡፡   

Standard (Image)

መኪናን ቅንጦት ያደረጉ የመንግሥት ሕጎች

$
0
0

በዱሮው ዘመን፣ ከግማሽ ክፍለ ዘመን ወዲህ ኦፔል፣ ታኖስ፣ ዶጅ፣ ሲትሮይን፣ ሮልስ ሮይስ፣ መርሴዲስና ሌሎችም ባለስም መኪኖችን እያሽከረከሩ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ፈልሰስ ማለት ለዘፈን የሚያበቃ መደነቅን ያተርፍ ነበር፡፡ ‹‹ይሏል ዶጇ ፏፏ...››ን ያስታውሷል፡፡

በበርካቶች የከተማ ነዋሪዎች ዘንድ የግል መኪና ባለቤት መሆን ቅንጦት መሆኑ ካበቃለት ብዙ ዘመን ተኩሷል፡፡ ይበልጡን ደግሞ በአሁኑ ወቅት በሚታየው የትራንስፖርት እጥረትና መንግሥትም በሚከተለው የትራንስፖርት አቅርቦት ሥርዓት ምክንያት ከባድ የትራንስፖርት ችግር በየመንገዱ ይታያል፡፡ በዝናብና በፀሐይ ወራት ትራንስፖርት ፈላጊ ሕዝብ እንደ እባብ ሽንጥ የረዛዘሙ ሠልፎችን ሠርቶ የሚያሳፍረውን መኪና በጉጉት ይጠብቃል፡፡

በዱሮው ዘመን መኪናው ሳይሆን መኪናውን ማሽከርከር የሚችለው፣ ፈቃድ ያለው ሰው እንደነበር ግልጽ ነው፡፡ መኪናው በመንግሥት ሆን ተብሎ በሚጣልበት ታሪፍና ግብር ምክንያት ውድ አልነበረም፡፡ እርግጥ ነው መኪና የሚገዛ ገንዘብ ኖሮት የሚገዛውም ጥቂት ነበር፡፡ ይህም ቢባል ግን በተለይ በንጉሠ ነገሥቱ ዘመን ደመወዝተኛ የሆነ ሰው ለብድር ከመሥሪያ ቤቱ አጽፎ በሦስት ሺሕም አለያም በአምስት ሺሕ ብርም እንደ አቅሙ ዘመን አመጣሽ መኪኖችን ይገዛ እንደነበር በርካቶች ያወጋሉ፡፡ በዚህ ዘመን ግን መኪና ቅንጦት ነው የሚለው ፈሊጥ እንዳለ ነው፡፡

መንግሥት ከአምስት ዓይነት በላይ ታክስ ከውጭ በሚገቡ አዲስም ሆኑ ያገለገሉ መከኖች ላይ ይጥላል፡፡ እንደ መኪናው የፈረስ ጉልበት እየታየም የታክስ ምጣኔው ከፍ ይደረጋል፡፡ በዚህ ምክንያት በዓለም ላይ ሆነ ተብሎ ጥቂት የመኪና ባለንብረቶች እንዲኖሩባት ያደረገች አገር ብትኖር ኢትዮጵያ ነች ማለት ይቻላል፡፡

ይኸው የአገሪቱ ሁኔታ ያስገረመው ኬንያዊው የቢቢሲ ዘጋቢ፣ ኢማኑኤል ኢጉንዛ ‹‹ለመሆኑ በኢትዮጵያ የመኪናን ዋጋ እንዲህ ውድ ያደረገው ምንድን ይሆን?›› ሲል ዘግቧል፡፡ መቶ ሚሊዮን እንደደረሰ ከሚገመተው ከሕዝብ ቁጥር ውስጥ መኪና ያለው ሰው ብዛት 700 ሺሕ ገደማ ብቻ እንደሆነ የመንግሥት መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ይህም ማለት ከእያንዳንዱ አንድ ሺሕ ሰው ውስጥ ሁለቱ ብቻ (ለአኃዝ ሲባል እንጂ ሁለትም አይሞሉም) የመኪና ባለንብረት መሆናቸውን ያሳያል፡፡ ይህ አኃዝ ካቻምና ይፋ ከተደረገው ከድሎይት አማካሪ ኩባንያ ድምዳሜ ጋር የሚያስማማ ነው፡፡ ይህ ኩባንያም ይህንኑ እውነታ ሪፖርት ማድረጉን ዘጋቢው አጣቅሷል፡፡

መንግሥት ባስቀመጠው የታሪፍና የጉምሩክ ቀረጥ ምክንያት፣ አስመጪዎች ለማጓጓዣ፣ ለወደብና ለመሳሰሉትን ወጪዎች ከመሸፈን አልፈው ትርፋቸውን አክለውበት በአዲስ አበባ እየተሸጡ ያሉት ያገለገሉም አዲሶቹም መኪኖች ዋጋቸው አይቀመስ ሆኖ ይገኛል፡፡ ለአንድ ቪትስ መኪና የሚጠየቀው ዋጋ እንደ መኪናው ቀለምና ይዞታ ከ250 ሺሕ ብር በላይ ሆኖ ይገኛል፡፡

ይህም ማለት ከ10 ሺሕ ዶላር በላይ ሆኖ ይገኛል፡፡ በርካታ የጃፓን ያገለገሉ መኪና መሸጫ ድረ ገጾች ግን እነዚህን ጃፓን ሠራሽ መኪኖች ከአንድ ሺሕ ዶላር ወይም ከ23 ሺሕ ብር (በወቅቱ ምንዛሪ) ባነሰ ዋጋ እንደሚሸጧቸው በይፋ ይታወቃል፡፡ ይህ ዋጋ ግን በመንግሥት ዘንድ ተቀባይነት የለውም፡፡ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በዚህ በ23 ሺሕ ብር ወይም በአንድ ሺሕ ዶላር መኪና ገዛሁ ብሎ አስመጪው ደረሰኝ ቢያቀርብለት እንዲሁ እንደማይቀበለው ከሚከተላቸው አሠራሮች መረዳት ይቻላል፡፡

በገቢዎችና በጉምሩክ ባለሥልጣን የታሪፍ ኦፊሰር የሆኑትን አቶ ካሳዬ አየለ እንደጠቀሱት፣ መቶ ከመቶ የሚደርሱ አምስት ዓይነት የቀረጥ ስሌቶች በንግድም ሆነ በግል መኪኖች ላይ ይጣላል፡፡ ይህ ግን ቅድሚያ ተሰጧቸውም ሆነ ከታሪፍ ነፃ ተደርገው የሚገቡትን እንደማይወክል አቶ ካሳዬ ጠቁመዋል፡፡ በተለይም ለሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሉ ተሽከርካሪዎች ቢበዛ ከአሥር ከመቶ ያልበለጠ ቀረጥ እንደሚጣልባቸው የገለጹት አቶ ካሳዬ፣ ሌሎች መኪኖች ግን እንደ የሞተራቸው የጉልበት አቅም ከ60 እስከ 100 ከመቶ ቀረጥ ይጣልባቸዋል ብለዋል፡፡ እንደ ሔኖክ ደምሰው ያሉ መኪና ነጋዴዎች በአገሪቱ የመኪና ንግድ ውስጥ ትልቁ ፈተና ይኸው የመንግሥት አይቀመስ ቀረጥ መሆኑን ሳይገልጹ አላላፉም፡፡

ይህ በመሆኑም በብዙዎች ዘንድ አማራጭ የማይደረጉት አነስተኞቹ ቶዮታ ቪትዝ መኪኖች ከ250 ሺሕ በላይ እንዲወጣባቸው ቢያስገድድም፣ በኬንያ ግን ከዚህ በግማሽ ያነሰ ዋጋ እንደሚጠየቅባቸው የቢቢሲው ዘጋቢ አስታውሷል፡፡

መንግሥት ከውጭ የሚገቡ ተሽከርካሪዎችን በአገር ውስጥ በሚገጣጠሙ ለመተካት ባይሆን እንኳ ከውጭ የሚገቡትን መጠን ለመቀነስ በማሰብ በርካታ የቻይና ኩባንያዎች መገጣጠሚያ ፋብሪካዎችን እንዲመሠርቱ ማበረታቻዎችን በመስጠት ደግፏል፡፡ ይሁንና መገጣጠሚያዎቹ የሚሸጡበት ዋጋም ቢሆን፣ ከሚገመተው በላይ ከፍተኛ ቀረጥ ተጥሎባቸው ከውጭ ከሚገቡት አኳያ ሲታይ ይህ ነው የሚባል የዋጋ ልዩነት እንደማይታይባቸው በርካቶች ይገልጻሉ፡፡

ከዋጋቸው ባሻገር በመኪኖቹ ጥራት፣ በመለዋወጫ አቅርቦትና በመሳሰሉት መስኮች በአገር ውስጥ የሚገጣጠሙት ላይ በርካቶች ዕምነት አጥተው ይታያሉ፡፡ የቢቢሲው ኢማኑኤልም ሆነ ሪፖርተር ከዚህ ቀደም ያነጋገራቸው የሊፋን ሞተርስ ኃላፊዎች በአገሪቱ ያለው ገበያ ብዙም እንዳልተዋጠላቸው፣ መንግሥትም ቢሆን ያገለገሉ መኪኖችን ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ የሚከለክል አሠራር መከተል ሲገባው ያንን ባለማድረጉ እየተቸገሩ እንደሚገኙ ኃላፊዎቹ ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ ከ60 ከመቶ በላይ የቶዮታ ሥሪት አዳዲስና አሮጌ መኪኖች እንደሚሽከረከሩ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ እንደ ቶዮታ ያሉና በሕዝቡ ዘንድ አመኔታ የሚጣልባቸው ሞዴሎች የቱንም ያህል ውድ ቢሆኑ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡበት መጠን እየጨመረ ይገኛል፡፡ ካለፉት ሁለት ዓመታት ይልቅ በ50 ከመቶ ጭማሪ የታየበት የመኪና ቁጥር በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ወደ አገር ውስጥ መግባቱን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ከ110 ሺሕ ያላነሱ መከኖች መግባታቸው ይጠቀሳል፡፡

መንግሥት በተሽከርካሪዎች ላይ የጣለው ቀረጥና ታሪፍ ከገቢ ምንጭነት ባሻገር በትራንስፖርት መስክ የሚታየውን አሸማቃቂ የመጓጓዣ ዕጦትን ለመቀነስ እንዲቻል የሚጥለውን የቀረጥ መጠን እንዲከልስ የሚጥይቁ አካላት እንደሚገልጹት፣ ይህን በማድረግ አቅሙ ያላቸው በርካታ ሰዎች በዚህ መንገድ የትራንስፖርት ችግሩን ለመቅረፍ እንዲችሉ መንግሥት ዕገዛ ማድረግ እንደሚጠበቅበት ይናገራሉ፡፡

ከዚህም ባሻገር ኢትዮጵያ ወደፊት የድንበር ተሻጋሪ፣ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነቶችን ማፅደቅና መተግበር ስትጀምር ከቀረጥ የሚገኘው ገቢ በእጅጉ ሊያሽቆለቁል እንደሚችል በማሰባሰብ ከወዲሁ ሌሎች አማራጮች መታሰብ እንዳለባቸውም ይመክራሉ፡፡ ይሁንና መንግሥት ከታክስና ከቀረጥ ከሚሰበስበው ገቢ ውስጥ ከግማሽ ያላነሰውን ከውጭ ከሚገቡ ዕቃዎች ላይ ከሚጣለው ግብር የሚሰበስብ ሲሆን፣ እንደ ተሸከርካሪ ያሉትና ዛሬም ድረስ የቅንጦት ዕቃዎች ተደርገው በሚታሰቡት ላይ ከፍተኛ ታሪፍ ጥሏል፡፡ 

Standard (Image)
Viewing all 665 articles
Browse latest View live